የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት የቁጠባ ፕሮግራም መንግስታዊ በሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንዲከናወን መደረጉ በግል ባንኮች ላይ ከፍተኛ ኪሣራ እያስከተለ እንደሆነና በአጭር ጊዜ የግል ባንክ ዘርፉን ህልውና አደጋ ላይ እንደሚጥል የባንክ ባለሙያዎች ለአዲስ አድማስ ገለፁ፡፡ እስካሁን ከ750ሺህ በላይ ግለሰቦች የቤቶች ልማት ቁጠባ ሂሣብ በንግድ ባንክ እንደከፈቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የግል ባንክ ባለሙያ፤ እሣቸው በሚሠሩበት ባንክ ደንበኛ የነበሩ ግለሠቦች በቤቶች የቁጠባ ፕሮግራም ተሣታፊ ለመሆን ከባንኩ ገንዘብ በማውጣት በመንግስት ባንኮች እያስቀመጡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት ሣምንታትም ባንኩ በዚህ አገልግሎት ተጠምዶ መቆየቱን የተናገሩት ባለሙያው፤ “በእነዚህ ጊዜያትም የባንክ ሂሣብ ለመክፈት ወደ ባንካችን የመጣ ደንበኛ አላጋጠመኝም” ብለዋል፡፡ በባንኩ ያላቸውን ገንዘብ ለማውጣት የሚመጡ ደንበኞች መበራከታቸውንና ይህም ባንኩ ራሱን ለማቋቋም ለዓመታት የደከመበትን ልፋቱ ከንቱ እንደሚያስቀረውና ቀጣይ ህልውናውንም አደጋ ላይ እንደሚጥለው ባለሙያው ይናገራሉ፡፡ ስማቸውና የሚሠሩበት ባንክ እንዲገለፅ ያልፈለጉ ሌላ ባለሙያም፤ በአሁን ሠአት ባንካቸው የውጭ ምንዛሬ እና የሃዋላ አገልግሎቶችን ከመስጠት ባለፈ አዳዲስ የባንክ ሂሣብ የሚከፍቱ ደንበኞች እያስተናገደ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለም የባንኩ ህልውና አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡
የኢዴፓ ሊ/መንበርና ከፍተኛ የባንክ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙሼ ሠሙ በበኩላቸው፤ መንግስት መንግስታዊ በሆነው የንግድ ባንክ በኩል ብቻ ዜጐች እንዲቆጥቡ ማወጁ ከነፃ ገበያ ስርአት ጋር የሚቃረን መሆኑን ገልፀው ይህና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በግል ባንኮች ላይ ከፍተኛ የህልውና አደጋ መጋረጣቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህ አካሄድ ከቀጠለም ያለ ጥርጥር ከሶስት እና አራት አመታት በኋላ የበርካታ የግል ባንኮች ህልውና እስከ መጨረሻው ሊያከትም ይችላል ብለዋል - አቶ ሙሼ፡፡ የቤቶች ልማት ቁጠባ ፕሮግራም ሁለት መሠረታዊ ተፅዕኖዎች አሉት የሚሉት አቶ ሙሼ፤ አንደኛው በግል ባንክ ውስጥ ከሚያስቀምጡ ደንበኞች ገንዘብ ላይ ማበደር አንዱ የባንኮች ተግባር መሆኑን ገልፀው፤ አሁን ግን ይህን ተግባር የሚያከናውኑበት ገንዘብ ወደ መንግስታዊ ባንክ እንዲሸሽ መደረጉን ይናገራሉ፡፡
ይሄም ብቻ ሳይሆን የግል ባንኮች በብዙ ዓመታት ያፈሯቸውን ነባር ደንበኞችም እንዲያጡ ያደርጋል ብለዋል፡፡ መንግስት የቀረፀው የቤቶች ልማት ፕሮግራም የግል ባንኮች አዳዲስ ደንበኞችን እንዳያፈሩ ማድረጉ ሁለተኛው ተፅዕኖ ነው የሚሉት ባለሙያው፤ በተቃራኒው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አዲዲስ ደንበኞችን እንዲያገኝ ይረዳዋል ብለዋል፡፡ ነባሩም ይሁን አዲስ ደንበኛ ከግል ባንኮች ወጥቶ ወደ መንግስት ባንክ መሄዱ የነፃ ገበያ ስርአት እንዲከስም ከማድረጉ ባሻገር ባንኮችም በህብረተሠቡ ዘንድ ለዘመናት የገነቡትን ጠንካራ እምነት እንዲያጡ ያደርጋል በማለት የግል ባንኮች ላይ የተጋረጠውን አደጋ ባለሙያው አስረድተዋል፡፡ መንግስት የግል ባንኮች ከሚያበድሩት ገንዘብ ላይ 27 በመቶ የህዳሴውን ግድብ ቦንድ እንዲገዙ ማዘዙን ያስታወሡት አቶ ሙሼ፤ የአሁኑ የግል ባንኮችን ያገለለው የቤቶች ቁጠባ ፕሮግራም ሲጨመርበት በባንኮቹ ላይ የሚደርሰው ጉዳት የቱን ያህል እንደሆነ መገመት አያዳግትም ብለዋል፡፡ “መንግስት የግል ባንኮችን ለማጥፋት ታጥቆ መነሣቱ የሚገርመኝ ጉዳይ ነው” ያሉት አቶ ሙሼ፤ በዚህ አካሄድ ከሦስት እና አራት አመት በኋላ የግል ባንኮች ሊጠፉ እንደሚችሉ ምንም ጥያቄ የሚያስነሣ ጉዳይ አይደለም ይላሉ፡፡
ኢህአዴግ ጉልበትና አቅም ያለው የግል ዘርፍ እንዲፈጠር አይፈልግም የሚሉት አቶ ሙሼ፤ በግል ባንኮች ላይ እየደረሠ ያለው ጫናም የዚሁ መገለጫ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህ አባባላቸው ማስረጃ ሲያቀርቡም በቅርቡ የወጣ ጥናት ኢትዮጵያ በመንግስት ኢንቨስትመንት ከአለም 2ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ በግል ኢንቨስትመንት ግን በመጨረሻው ረድፍ ከተዘረዘሩት ሃገራት አንዷ ነች ብለዋል፡፡ አቶ ቡልቻ ደመቅሣ በበኩላቸው፤ ከዚህ በፊትም ከቻይና ለሚመጣ ማንኛውም እቃ በንግድ ባንክ በኩል ብቻ ግብይቱ ይፈፀም የሚል ህግ መፅደቁን አስታውሠው፣ ያሁኑ ሲጨመርበት በእርግጥም የግል ባንክ ዘርፉ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦበታል ብለዋል፡፡ መንግስት በተደጋጋሚ በባንክ አሠራር ውስጥ ጣልቃ መግባቱ ለዘለቄታው የማያዋጣ ተግባር መሆኑን የጠቆሙት አቶ ቡልቻ፤ እንዲህ ማድረጉም አገሪቱን የዓለም ንግድ ድርጅትን ከመሳሰሉ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ማህበራት አባልነት እንዳገለላት በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡
በዳዊት ደመላሽ
lørdag 29. juni 2013
søndag 16. juni 2013
ኢትዮጲያ የማን ናት?
ኢትዮጲያ የማን ናት?
June 13, 2013
እንደሚታወቀው በአንድ ሃገር የኤኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ክንውኖች የቀን ተቀን ለውጥ ውስጥ የህብረተሰብ ተሳትፎ(አስተዋጾ) ጉልህ ሚና አለው፡፡ እንዲሁም በሂደትቱ ውስጥ የሚያጋጥሙ አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ጉዳዮችም ይሁኑ ወይም በተቃራኒው የሚከሰት ተፈጥሯዊም ሆነ በመልካም አስተዳድር ችግር ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች ከህብረተሰብ ጫንቃ ላይ አይወርድም፡፡ ይህ ስለሚታወቅ ሃላፊነት የሚሰማቸው፣ ለሃገርና ለሕዝብ ታማኝ የሆኑ፣ በሕዝብ ይሁንታ ስልጣን የያዙ መንግስታት ያላቸው ሃገሮች በየትኛውም ሃገራዊ እንቅስቃሴ ላይ ሕዝባቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ በማድረግ በቤሔራዊ ስሜት የታነፀ በሃገሩ ጉዳይ የማያመነታ ህብረተሰብ ይገነባሉ፡፡ የእንደኛ አይነቶቹ የሃገርና የሕዝብ ፍቅር የሌላቸው አምባገነን መሪዎች ግን እንኳን የሃገርህ ጉዳይ ያገባሀል ብለው ሊያሳትፉት ቀርቶ የሕዝብን የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ተፈጥሮዊ መብቱን ገፈው ሃገሪቱን የቁም እስር ቤት አርገዋታል፡፡
በሕዝብ ላይ የሚፈፅሙትን ኢሰብአዊ የሆነ የመብት ጥሰትን የተቃወመ፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ ሃገር ሲቸበቸብ ኢትዮጲያ የኢትዮጲያዊያን ነች ብለው የተቃወሙትን፣ የእምነት ነፃነታቸውን አናስነካም ብለው በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን የጠየቁና በሌላም ሃገራው ጉዳይ ላይ እንደ ዜጋ ይመለከተናል ያሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይ የተማረውን ክፍል ስም እያወጡ በየማጎሪያው በእስር በማሰቃየትና ገሚሱንም በማሳደድ ኢትዮጲያ የምንላትን የሁላችን የሆነች ታላቅ ሃገር በሞኖፖል በመቆጣጠር የአንድ ግለኛ ቡድን የግል ሃብት አረገዋታል፡፡
ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ለሃገርና ለሕዝብ የተሻለ ሃሳብ አለን የሚሉትን የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎችን ጨምሮ የሞያ ስነምግባራቸውን ጠብቀው አምባገነኑ ስርዓት በሕዝብና በሃገር ላይ የሚፈፅመውን ግፍና በደል በብእራቸው ያጋለጡ ጋዜጠኞችን በጅምላ ለሱ የሚመቸውን ስም እያወጣለቸው በየማጎሪያ ካምፑ የወረወራቸው እጅግ ብዙ የህሊና እስረኞች አሉ፡፡ ከህፃን ልጁ ተለይቶ በእስር የሚማቅቀው እስክንድር ነጋ፣ እውነት በመፃፏ ከነህመሟ በእስር የምትማቅቀው እርዮት አለሙ፣ በዘረኛው ቡድን ላይ የሰላ ሂስ በማቅረቡ በአሸባሪነት ተፈርጆ በእስር የሚሰቃየው ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ እንዲሁም በቀለ ገርባና ኦልባና ሌሊሳን ጨምሮ ብዙ ምርጥ የሃገር ልጆች በዚህ ዘረኛ ቡድን ግፍ እየተፈፀመባችው ይገኛሉ፡፡
ለዚህ ሁሉ በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚደርሰው እንግልትና መዋከብ ምንም እንኳን የመንግስትን እርካብ የተቆናጠጡት ገዢዎቻችን ከተፈጥሮ ባህሪያቸው አንፃር የፈለጉትን ያሻቸውን ቢያደርጉም በየግዜው በህዝብ ላይ የሚያደረሱትን ሰቆቃ የየሰሞኑ መነጋገሪያ ከማደረግ በዘለለ ህዝብ እንደ ህዝብ በደል በቃኝ፣ ግፍ በቃኝ፣ መሰደድ በቃኝ፣ መታሰርና መገረፍ በቃኝ፣ ከሃብትና ከቀዬ መፈናቀል በቃኝ ብሎ በተለይ በሃገር ቤት ያለው የበደሉ ገፈት ቀማሽ የሆነው ወገን ለለውጥ ጥግ ድረስ ለትግል አልተዋቀረም፡፡ ሃገርና ህዝብን ከዚህ እኩይ ስርዓት መታደግን ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ የሚተው አይደለም የልቁኑም ወያኔን ለመታገል ቆርጠው ከሚሰሩ የህዝብ ሃይሎችን በመቀላቀል ትግሉ የሚጠይቀንን ሁሉ የምንሆንበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡
ኢትዮጲያ የነማን፣ የማን እንደሆነች ማወቅ የሚቸግርበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ ጥቂት ዘረኛ ቡድኖችና ሆድ አደሮች የነገሱባትና ፈላጭ ቆራጭ ሆነው የቅንጦት ኑሮ የሚኖሩባት፣ ብዙሃኑ ለሃገርና ለዳር ድንበሩ መከበር ከጥንት ጀምሮ አጥንቱን ከስክሶ ደሙን አፍስሶ ባቆያት ሃገር ላይ የበይ ተመልካች ሆኖ በርሃብና በእርዛት በሚኖርባት ሃገር ናት፡፡
እናም ይህ ዘረኛ የወያኔ ስርዓት እንዲያበቃለትና ዘመን እንዳይሻገር እነሱ እንደሚሉን ጥቂቶች(ኢምንቶች) ሳንሆን እልፍ አእላፍ ሆነን ለነፃነታችን፣ ለሃገራችን አንድነትና ለወደቀው ክብራችን ብለን በአንድነት እንነሳ፡፡ ኢትዮጲያ የኛ የብዙሃን እንጂ የጥቂት ዘረኛ ቡድን መፈንጫ አትሁን!!!!!!!!!!
ኢትዮጲያን እግዚሀብሔር የባርክ!!!!
torsdag 6. juni 2013
በወይዘሮ አዜብ መስፍን ላይ ምርመራ እንዲደርግ ግፊቱ ጨምራል
በወይዘሮ አዜብ መስፍን ላይ ምርመራ እንዲደርግ ግፊቱ ጨምራል
እነመላኩ ፋንታን ተከትሎ በአዜብ መስፍን ላይ የሚቀርቡ የሙስና አቤቱታዎች ጨምረዋል::
የሙስና ኮሚሽን በአቶ ገብረዋህድ ቤት ባደረገው ፍተሻ እንዲሁም ከኣሁን ቀደም በመርማሪ ደህንነቶች ክትትል በተደረገ የስልክ ጠለፋ የቀድሞ ሟች ጠ/ሚ ባለቤት እና በአለም ትልቁ የሙስና አባት ኤፈርት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከአቶ ገብረዋህድ ባለቤት እና እህት ጋር በከፍተኛ ደረጃ የቢዝነስ ስራ ይሰሩ እንደነበር እና ከታሰሩት ባለስልጣናት እና ባለሃብቶች ጋር የንግድ አጋርነት እንዳላት አረጋግጧል::ይህንን የሚጠቁሙ ሰነዶች እና ከተለያዩ ወገኖች የሚቀርቡ ጥቆማዎች እና አቤቱታዎች ምርመራው ወደ አዜብ መስፍን አምርቶ ለጥያቄ እንደምትፈለግ ፍንጭ እየሰጠ ነው ሲሉ የሙስና ኮሚጽሽን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::
በሰላማዊ ሠልፉ ሰማያዊ ፓርቲና መንግሥት እየተወዛገቡ ነው
በሰላማዊ ሠልፉ ሰማያዊ ፓርቲና መንግሥት እየተወዛገቡ ነው

ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድ ወር በፊት በጠራውና ባለፈው እሑድ የተደረገውን ሰላማዊ ሠልፍ መንግሥት ሲያወግዝ፣ ሰላማዊ ፓርቲ ደግሞ የመንግሥት ውግዘት በተቃውሞ የተነሳውን ሕዝብ ከማሸማቀቅ ባለፈ የሕግ ድጋፍ እንደሌለው እየገለጸ ነው፡፡
“ይህ መንግሥት አይመጥነንም” የ“ምርቃና” መግለጫ ለኢህአዴግ ድንጋጤ
“ይህ መንግሥት አይመጥነንም” የ“ምርቃና” መግለጫ ለኢህአዴግ ድንጋጤ

ሰሞኑን ኢትዮጵያ የዓለም መገናኛ አጀንዳ ሆናለች። ለዘመናት እጇን ኢትዮጵያ ላይ ተክላ የኖረችው ግብጽ የምትዝተው ዛቻና፣ በቅርቡ ተቋቁሞ ታላቅ ታሪክ በማስመዝገቡ የተረጋገጠለት ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ አጀንዳዎቹ ናቸው።
Abonner på:
Innlegg (Atom)