
ወደ ደሴና ጎንደር እንምጣ፣ ነገ ከሌላው ጊዜ በተለየ አበቦች ለፌደራልና ለክልል ፖሊሶች በሰላማዊ ሰልፈኞች ይበረከታሉ፡፡እኛ ኢትዮጵያዊያን የጦርነት ታሪክ የከበበን በመሆኑ ለወታደር ያለን ፍቅር የተለየ ነው፡፡ዛሬ ድረስ ወታደራዊ ዮኒፎርም የለበሰ ሰው ሲመለከቱ ልባቸው ወከክ የሚልባቸው ቆነጃጅት ቁጥር የትየለሌ ነው፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ግን እንዲህ በስስት የምንመለከተው ወቴ በውስጥ ጉዳይ በአብዛኛው የገዢዎች መገልገያ ሆኖ በእናቱ ልጅ ላይ ቃታ ሲስብ አይኑን አያሽም፡፡ አዛዦቹ ያሉትን ካልተገበረ ምን እንደሚጠብቀው ስለሚያውቅ ድንጋይ ለወረወረ ሁሉ አጠፋውን በጥይት ከማድረግ አያመነታም፡፡ለዚህ አንገት ደፊ ታሪካችን ብዙ ማጣቀሻዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡
የነገው ሰልፍ አበባ የሚበረከትበት ዋነኛ አላማ ፍቅርን ለመስበክ ነው፡፡በወታደሩ፣በፖሊሱ፣በደህንነቱና በመንግስት ታማኝ ላይ የምንመዘው ሰበዝ ቢኖርም ነገ ግን ፍቅርን እንሰጣለን፡፡ምላሹ ምንም ይሁን ምን የአበባው መልዕክት ፍቅር ነው፡፡ የአበባ ቀን እንበለው ይሆን?
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!
አንድነት ኃይል ነው!! አንድነት ፍቅር ነው!! ፍቅር ያሸንፋል!!
#millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ #Gonder #Dessie
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar