ዛሬ ወደ ቢሮየ የ15 ደቂቃ ጉዞ ሳደርግ በአእመሮየ እየተመላለሰ በእንግሊዘኛ ሃሳቡ ይረብሼኝ ጅምሮዋል፡፡ ‹‹Islamic extremism freedom for politics or religion>> የሚል ሃሳብ እያብሰለሰልኩ ቢሮየ ደርሼ በጥዋቱ ስብሰባ ምሃል ወደ አራት ገጽ የሚደርስ ‹‹Islamic extremism freedom for politics or religion in Ethiopian context >> ብየ በእንግሊዘኛ ሃሳቤን አሰፈርኩ ግን አንባቢየ ማነው መረጃየስ ስል ወደ አማረኛ አለዝቤ ከኢንተርኔት መረጃዎች ተናብቤ ይህች የሰላም ምድር እንደ ድሮው ሰላም ትሆን ዘንድ ሃሳቤ አሰፈርኩ፡፡ ራሚደስ ከተባሉ የመጣጥፍ ጽሃፊ ጋር ሃሳቤ ይቀራረባል መጅመሪያ ለኔ የእስልምና “ፅንፈኛ አክራሪነት” ምን ማለት ነው የሚለውን ላይ መግባባት መቅደም ይኖርበታል፡፡ እስላሞቹ ሱሪያቸውን አሳጥረው፣ ፂም አሳድገው ሲሄዱ፣ ሴቶቹ ሲሸፋፈኑ፣ በቀን አምስት ጊዜ ሲሰግዱ፣ የሮመዳን ወር ሲፆሙ፣ መካን ጨምሮ ወደተለያዩ የሀገራችንና የአለማችን ክፍሎች መንፈሳዊ ጉዞ ሲያደርጉ ስንመለከት እከሌ/እከሊት እኮ አክራሪ ሆነ/ች ሲባል መስማቱ እንግዳ አይደለም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አንድ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ቤተሰብ ነጠላውን አገልድሞ ጎህ ሲቀድ ቤተ እምነቱን ተሳልሞ፣ የመላእክትና የፃድቃን መታሰቢያ በአላት ላይ ጧፍ አብርቶ፣ ዳቦ ቆርሶ፣ሰንበትን አክብሮ፣የሁዳዴን፣የሰኔን፣የፍልሰታን ፣የገናን፣የነነዌንና አርብ እሮብ ቀናትን በፆም በፀሎት ሲያሳልፍና እየሩሳሌምን ጨምሮ ወደተለያዩ ገዳማት ሀይማኖትዊ ጉዞ ሲያከናውን ሲታይ እንዴት ያለ ፈሪሀ- እግዚአብሔር ያደረበት፣ ለሀይማኖቱ ቀናኢ የሆነ ቤተሰብ ነው ይባላል፡፡ በሙስሊሙ መነፅር ግን ይህ ቤተሰብ በአክራሪ ኦርቶዶክስነት ሊመሰል ይችል ይሆናል፡፡ እዚህ ጋር ነው ችግሩ፡፡
በተለያዩ የማንነት እሴቶች ዙሪያ የተሰበሰቡ ወገኖች “ሌላውን” የሚመለከቱበት መነፅር ”የራሳቸውን” ከሚመለከቱበት ለየት ማለቱ ነው ችግሩ፡፡ ከዚህ በላይ በተነፃፃሪ የቀረቡት የእስልምና እና የኦርቶዶክስ ክርስትና ሀይማኖታዊ ክንዋኔዎቻቸውን አንዳንዱ በለዘብተኝነት ሲያከናውናቸው አንዳንዱ ደግሞ ከረር አድርጎ ይይዘዋል፡፡ ያከረረው ክፍል የራሱን እምነት አጠንክሮ መያዙ የሀይማኖቱ አጥባቂ እንጂ ፅንፈኛ አክራሪ ሊያስብለው የሚገባ አይመስልም፡፡ የየትኛውም እምነት ተከታይ በመሰለው መልኩ ሀይማኖቱን ቢያጠብቅ የሰው ልጅ መሰረታዊ መብት መሆኑን በዚህ በስልጣኔ ዘመን ለማስረዳት መሞከሩ ከንቱ ልፋት ይሆናል፡፡ የፅንፈኝነት አባዜው የሚመነጨው ከእኔ እምነትና አስተሳሰብ ውጭ ያሉት በሙሉ ትክክል አይደሉም፡፡ ትክክል አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን በወድም በግድም ወደ እኔ እምነት መቀላቀል ይኖርባችኋል፡፡ ሀገሪቱም መተዳደር ያለባት በእኔ ሀይማኖትና የአስተሳሰብ ፍልስፍና እንጂ በሌላ በማናቸውም መንገድ ሊሆን አይችልም፡፡ እምቢ አሻፈረኝ ባዮን ደግሞ ምድራዊ ቅጣት የመስጠት
መለኮታዊ ሀላፊነት አለብን ብሎ የሚያስብ መሰረታዊ የሰው ልጆችን የዜግነት፣ የእምነት፣ የመምረጥ እና የአስተሳሰብ መብቶች ማፈን ሲጀምር ነው፡፡ ኢትዮጵያ በሸሪአ ህግ መተዳደር አለባት የሚል አስተሳሰብ ፅንፈኝነትን ገላጭ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት እንጂ ሌላ የማንም አይደለችም ባዩም ፅንፈኝነትን በትከሻው አዝሎ እየሄደ ነው፡፡ ፅንፈኛ አክራሪነት በሀይማኖት ስብስብ ብቻም አይገለፅም፡፡ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው (በፖለቲካ ስልጣን፣ በንግድ እንቅስቃሴ፣ በሃገር መከላከያና የደህንነት መዋቀር በሙሉ) የእኔ ብሄርና ጉጥ ብቻ ነው የሚለውም የብሔር ፅንፈኛ አክራሪነት በሽታ በሰራ አካላቱ እንደተንሰራፈበት ገላጭ ምልክት ነው፡፡ በመሆኑም የአጥባቂነትን ከፅንፈኛ አክራሪነት ለይቶ ማየቱ ተገቢና አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑ ማስረገጥ ይኖርብናል፡፡
ከእስልምና እምነት አስተምህሮ መጀመር በፊት ከጣኦትና ክዋክብት አምልኮ ጀምሮ አለማችን ቡዲዝም፣ ጃይኒዝም፣ ሲኪዝም፣ ሂንዱዊዝም፣ የኮንፌሸንና ሌሎች ሀይማኖቶችን ስታስተናግድ ከርማለች፡፡ በተለይ በተለይ በአንድ አምላክ፣ በመላእክቶችና ተፃራሪ ሀይል ሆኖ በሚታመነው ሰይጣን መኖርን እንዲሁም ከሞት በኋላ ስለሚኖር ህይወት የገነትና የገሀነም ፅንስ ሀሳቦችን የሚሰብከው የቀድሞው የፐርሽያ ታዋቂ ገጣሚና ፈላስፋ ዞራስተር (ዛራቱሰቱራ) አስተምህሮ ከእየሱስ ልደት ወደ ሺህ አምስት መቶ አመታት በፊት የነበሩትን ህዝቦች ከማሳመኑና ከማስከተሉም ባለፈ የዞራሰትሪዝም አስተምህሮዎች በአምላክ አህዳዊነት (Monotheism) ላይ መሰረት ባደረጉ ሀይማኖቶች በተለይም ለይሁዳ፣ ክርስትናና እስልምና እምነቶች የአስተሳሰቦች አወቃቀር ሂደት ላይ ማገር ማቀበሉ የማይታበል ሀቅ ነው፡፡ የዞራስትሪዝም ተከታዮችን ማሳደዱና መጽሀፍቶቻቸውንም ማቃጠሉ ከአራተኛው አመተ-አለም ከታላቁ አሌክሳንደር የፐርሽያ ግዛትን መውረር አንስቶ የተከናወነና በመጠኑም አገግሞ የነበረውን የዞራስተሪዝም እሴቶች ከሰባተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ መስፋፋት የጀመሩት የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች እንዳያንሰራራ አድርገው መምታታቸው በታሪክ የተመዘገበ እውነታ ነው፡፡ በግዜው ወደ ህንድ የተሰደዱ የዞራስትሪዝም ተከታዮችና እዛው ኢራን አካባቢ ቀርተው ይኖሩ የነበሩ የእምነቱ ተከታዮች
በድብቅ ካስቀመጧቸው መፅሀፍቶቻቸው መረዳት እንደተቻለው የAhura Mazda (የበጎ መንፈስ) እና የAngra Mainyu (የክፉ መንፈስ) እሳቤዎች ለዛሬው የይሁዳ ኦሪት የክርስትና ወንጌልና የእስልምና ቁርአን የሚጋሩትን መሰረታዊ የሀይማኖቶቹ አስተምህሮዎች ምንጭ ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል፡፡ የይሁድና የክርስትና ሀይማኖቶች ታሪካዊ የአመሰራረት ዳሰሳ ለጊዜው ወደ ጎን አድርገን በዚህ ፅሁፍ ጭብጥ ማጠንጠኛ ስለሆነው የእስልምና ሀይማኖት ጥንሰሳ በወፍ በረር ቅኝት ብናደርግ ይመረጣል፡፡
በዛሬው ሳኡዲ አረቢያ የሚኖሩ የቁረይሻ ጎሳ አባላት ደካማና በሌሎች ሀያል ጎሳዎች ስር ተበታትነው ይኖሩ እንደነበሩና ከመካከላቸው ቁሶይ ቢን ኪላብ የተባለ ጦረኛ በሀይልና በዲፕሎማሲ በመታገዝ የቁራይሽን ጎሳ ማሰባሰቡና በመካከላቸውም የፀና አንድነት እንዲመሰረት መትጋቱ
ይነገርለታል፡፡ የጣኦት ማምለኪያ የነበረ ነው ተብሎ የሚታመነውን መሰረተ ድንጋዮ በሰው ልጅ የመጀመሪያውን ፍጥረት በአዳም የተጣለውና ግንባታውም በገብርኤል ጥቋቁር ድንጋዬች አቅራቢነት፣ በአብርሃምና በልጁ በእስማኤል የተጠናቀቀ ተብሎ የሚታመነው መካ ውስጥ የሚገኘውን ከዕባ ቁሰይ ከተቆጣጠረ በኋላ እራሱን የአከባቢው ንጉስ አድርጎ አነገሰ፡፡ ከቁሰይ ኪላብ አምስት ትውልድ በኋላ የጦር መሪ ፣ዲፕሎማት፣ ነጋዴ፣ ፈላስፋ፣ ህግ አውጭና ተራማጅ የሆነ ሰው ከዚያው ከቁረይሽ ጎሳ ብዙም በሀብት በማይታወቁት ነገር ግን ከተከበሩት የሀሺማይት ንኡስ ጎሳ በ570 ዓ.ም በመካ ከተማ ተወለደ፡፡ ይህ ሰው ገና የእናቱ ማህፀን ውስጥ እንዳለ ወላጅ አባቱን ያጣና የስድስት አመት ህፃን እያለ ደግሞ ወላጅ እናቱን በሞት የተነጠቀ፣ እድገቱም ከአጎቱ ከአቡ-ጣሊብ ጋር ያደረገው መሀመድ ኢብን አብደላ ነው፡፡ በወጣትነቱ “ታማኙ” የሚል ቅፅል የተጎናፀፈው መሀመድ በአከባቢው የተወደደና የተከበረ ነበር፡፡ የቁረይሽ ልዕልት እየተባለች የምትጠራው አንዲት ነጋዴ ዘመዱ ባሏ ሞቶባት የንግድ ስራዋን የሚያካሄድላትና የሚቆጣጠርላት ሁነኛ ሰው ታፈላልግ ነበርና የመሀመድ አጎት አቡ-ጣሊብን ታማክራለች፡፡ እሳቸውም ለንግድ ስራ ወደተለያዩ ስፍራ ሲሄዱ ስከትሉት የነበረውን ታማኙን መሐመድን ያገናኙትና የቁረይሽ ልዕልት፣ የሀሺማይት ዝርያና ሀብታሞ ከድጃ ወጣቱ መሀመድን ለስራ ትቀጥረውና የንግድ ስራውን እስከ ሶርያ እየተጓዘ ማጧጧፍ ይጀምራል፡፡ በስራው ችሎታና በታማኝነቱ የተማረከችው ከድጃ ብዙም ሳይቆይ በእርሷና በመሀመድ መካከል ተመስርቶ የነበረውን የስራ ግንኙነት ወደፍቅር ይለወጥ ዘንድ የጋብቻ ጥያቄ ታቀርባለች፡፡ በግዜው የሀያአምስት ዓመት ወጣት የነበረው መሀመድም የቀረበለትን የጋብቻ ጥያቄ ተቀብሎ የአስራ አምስት አመት ታላቁ ከነበረችውና የክርስትና እምነት ተከታይ ከነበረችው ከከድጃ ጋር በትዳር ተሳስሮ መኖር ጀመረ፡፡ መሀመድ በንግድ ስራው ምክንያት ከተለያዩ የእምነት ተከታዮች በተለይ በመካ ይኖር ከነበሩ የይሁድና የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች ጋር በቅርበት ይገናኝና የሀይማኖት ፍልስፍናዎችን በተመለከተ ክርክሮችን ይከታተል ጀመር፡፡ ፀጥታ ወደሰፈነባቸው ዋሻዎችም እየሄደ በተመስጦ በመፀለይ አምላክን እውነተኛውን መንገድ ያመለክተው ዘንድ አዘውትሮ ይፀልይ ጀመረ፡፡ ከእለታት አንድ ቀን መላአኩ ገብርኤል መቶ የ40 ዓመት ጎልማሳ የነበረው መሀመድ የአላህ መልክተኛ ሆኖ መመረጡን አበሰረው፡፡ በአደባባይ ወጥቶም የእስልምና አስተምህሮዎችን መስበክ ጀመረ፡፡ የክርስትና እምነት ተከታይ የነበረችው ባለቤቱ ከዲጃ እና የአጎቱ ልጅ አሊ አቡ-ጣሊብ ሀይማኖታቸውን ቀይረው ከመጀመሪያዎቹ የእስልምና
ተከታዮች ተርታ ተሰለፉ፡፡
የነብዮ መሀመድ የእስልምና ሀይማኖት የመቀበልም ሆነ የመስበኩ ጉዞ አልጋ በአልጋ እንዳልነበርም ይጠቀሳል፡፡ ለምሳሌ የቁረይሽ ጎሳ አባላትና የበኑ ኡመያ ንዑሰ ጎሳ ቤተሰቦች በጎሳ መሪዎቻቸው አስታከው የመሀመድን ነብይነት በመቃወም አስተምህሮዎችን እንዲያቆም በአጎቱ በአቡ-ጣሊብ ጣልቃ ገብነት ጫና ለመፍጠር መሞከራቸው ይታወሳል፡፡ በመቀጠልም በተለምዶ የሀዘን ዘመን (619-623 ዓ.ም) እየተባለ በሚጠራው የመከራ አመታት የቁረይሽ ጎሳ አባላት የሆኑት በኑ መኸዙምና በኑ አብድ ሻም የተባሉት የንዑስ ጎሳ አባላትም የነብዮ መሀመድ ንዑስ ጎሳ በሆኑት ሀሺማይቶች ላይ
የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የማግለል ዘመቻ ከፈቱባቸው፡፡ ማንም የቁረይሽ ጎሳ ከሀሺሞች ጋር እንዳይገበያይ፣ በጋብቻም እንዳይተሳሰር ታወጀባቸው፡፡ በጊዜው በሀሺዎች ላይ በደረሰው ስር በሰደደ እጦታ የነብዮ መሀመድ የቅርብ ተከታዮች ባለቤቱ ከዲጃንና አጎቱ አቡ ጣሊብን ጨምሮ በሞት ተለዩ፡፡
በመሀመድና በተከታዮቹ በተለይም በሀሸማይቶች የንዑስ ጎሳ አባላት ላይ የተከፈተው ሁሉን አቀፍ ዘመቻ ከፊሉን ከመካ ወደ መዲና እንዲሰደድ ጥቂቶቹን ወደ ኢትዮጵያ ምድር ገብተው በጥገኝነት እንዲኖሩ አስገድዷቸዋል፡፡
ይህ በቁረይሽ ንዑስ ጎሳ አባላት መካከል የነበረው መራኮስ እንደቀጠለ በ 632 ዓ.ም ነብዮ መሀመድ ተተኪውን ሳይሰይም ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡ የነብዮ መሀመድ ተወዳጅ ሚስት የነበረችው የአይሻ አባትና የነብዮ መሀመድ የቅርብ አማካሪው የነበረው አቡበከር ለ ሁለት አመት ከሶስት ወር
ለሚሆን ጊዜ የሀይማኖትና የፖለቲካ አመራሩን ተክቶ ኖረ፡፡ በግዛት ዘመኑ በመላው አረቢያ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ባደረገው ጥረት መሠረት እስከ ሶርያና ኢራቅ ድረስ ወረራ አካሄደ፡፡ የነብዮ መሀመድ ልጅ ፈጡማም አባቴ ትቶልኝ የሞተውን መሬት ከለከለኝ ብላ ቂም የያዘችበት የመጀመሪያው ከሊፍ አቡበከር ከሀሺማይቶች ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባቱ ይታወሳል፡፡ አቡበከር ከመሞቱ በፊት ”ትክክለኛ” የተባልን የቁርአን ቅፅ ያስረከበው የበኑ ኦዲ ንዑስ ጎሳ አባል የሆነው ኡመር ኢብን ኸጣብ 2ተኛው የአላህ መልክተኛ ተተኪ ሆኖ ተሾመ፡፡ ልጁን ሀፍሳን ከነብዮ መሀመድ ጋር በማጋባት የአምቻ ግንኙነት ፈጥሮ የነበረው ኡመር በጋብቻ እንጂ የስጋ ትስስር ከነብዮ መሀመድ ጋር ባለመኖሩ በሀሺማይቶች ሲወረፍ ቢከርምም ከ634 እስከ 644 ዓ.ም የከሊፍነቱን መንበር ይዞ ቆየ፡፡ የግዛት ዘመኑም እስከ ኢራንና ሶርያ ድረስ ጦሩን እየላከ እስላማዊ አስተዳደር አድማሱን አሰፋ፡፡ ኡመር 644 ዓ.ም ከሞተ በኃላ 3ተኛው ከሊፋ ሆኖ የተሾመው ኡስማን ኢብን አፋ የተባለው ከነብዮ መሀመድ ንዑስ ጎሳ ሀሺማይቶች ጋር ከፍተኛ ቁርሾ ውስጥ ገብተው ከነበሩት የኡመያ ንዑስ ጎሳዎች ቤተሰብ የተወለደና በሀብትም እጅግ የከበረ ሰው ነበር፡፡ ኡስማን እስልምናን በመቀበሉ ከባለቤቱ ጋር ሲፋታ ነብዮ መሀመድ ልጁን ሩቂያን ድሮለት ስለነበረ ወደ ኢትዮጵያ መጀመሪያ ከተሰደዱት የነብዮ መሀመድ ተከታዮች ውስጥ ተጠቃሾች ነበሩ፡፡ ወደ መካ ተመልሶ በኖረበት የግዛት ዘመኑ 644 እስከ 656 ዓ.ም ኡስማን የተለያዩ የነበሩትን የቁርአን ቅፆች በመሰብሰብ ማቃጠሉና እስከዛሬም ድረስ ህዝበ-ሙስሊሙ የሚያምንበትን “የተረጋገጠና ትክክለኛው” የሚባለውን ቁርአን ብቻ ከነብዮ መሀመድ ሞት አስራ ስምንት አመት በኃላ እንዲታተም አስደረገ፡፡ በዚህም ተግባሩ እስልምናን ከልተቀበሉት ጋር ብቻም ሳይሆን ከእስልምና ተከታዮችም ጋርም ተጋጨ፡፡ እስከ ኢራቅና ግብፅ ጦሩን ልኮ እስልምናን ማስፋፋቱ ቢሳካለትም በ 656 ዓ.ም መዲና ውስጥ በሰው እጅ ተገድሎ ሞተ፡፡ የነብዮ መሀመድ የቅርብ ዘመድ የሆኑት ሀሺማይቶች የከሊፍነቱ ስልጣን ከነብዮ መሀመድ ጋር የስጋና የደም ትስስር ላላቸው እንጂ ለሌላ ጎሳ አባላት መስጠቱን በፅኑ ይቃወሙ ነበር፡፡ የነብዮ መሀመድ የአጎት ልጅ የሆነውና ከነብዮ ልጅ ፈጡማ ጋር በትዳር የተሳሳረው አሊ የሶስቱንም ከሊፎች ሹመት ሲቃወም ሰንበቶ በስተጨመረሻ ከሊፍነቱን ጨበጠ፡፡ በመካና መዲና ላይ ከነበረው ጠንካራ የኡመያ ተቃውሞ በመሸሽ መቀመጫ ከተማውን ከመዲና ወደ ኢራቅ ኩፋ አዘዋወረ፡፡ ዳሩ ግን ሽኩቿዋችና ጦርነቶች ባላማቆማቸው አሊ በ661 ዓ.ም ኩፋ ኢራቅ ውስጥ በመርዝ ተገደለ፡፡
ይህ በሀሺሞችና በኡመያ ንዑሰ ጎሳ አባላት መካከል የነበረው የጥቅምና የስልጣን ሽኩቻ ስር ሰደዶ ዛሬ ለምናየው የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮችን በሱኒና ሺዓ መስመር አራማጅነት በመከፈል በእስልምና ሀይማኖት ውስጥ የመጀመሪያውን መሰንጠቅ አስከትሎአል፡፡ የኡመያ ሰዋች የሱኒ መስመር
ተከታዮች ሲሆኑ የመሀመድ ስጋ ዘመዶች የሆኑት ሀሺማይቶች ደግሞ የሺዓ መስመር ተከታዮች ሆኑ፡፡ ዛሬ በአብዛኛው የአፍሪካ ምድር ኢትዮጵያን ጨምሮ የምናገኘው የእስልምና መስመር የሱኒ ተከታዮችን ነው፡፡ ይህ የሀይማኖት መስመር ክፍፍል ወደ ፖለቲካውም ሰርጎ ገብቶ በታሪክ ተመዝግበው የሚገኙትን የአባሲድ፣ የኡመያደና ፋቲማያድ አገዛዞችንና በመካከላቸው የነበረውን ረጅም የስልጣን ትግል አስመዝግቦ አልፎአል፡፡ በሂደት በእስልምና ሀይማኖት ውስጥ የተፈጠሩት ክፍፍሎች ባለ ብዙ ዘርፍ እየሆኑ የሱኒና የሺዓ መስመሮችን እያለፈ በራሳቸው በሁለቱ መስመሮች ውስጥም ቅርንጫፎች እየበዙ መጡ፡፡ ለምሳሌ ሱኒዎች እስልምና ሲመሰረት ከነበረው ቅርፅና ይዘት ሳንለውጠው አንዳንድ ጥሩ የሚባሉ ጭማሪዎችን ብናካትትበት አይከፋም የሚሉ አስተሳሰቦችን ማስተናገድ ጀመረ፡፡ በነብዩ መሀመድ ዘመን ያልተደረጉ ነገር ግን በጎ የሆኑ ጭማሪዎች ለምሳሌ የነብዩ መሀመድን የልደት ቀን ማክበር፣ በሀይማኖታቸው ቀናኢ የነበሩ ታዎቂ ሰዎችን በመቃብራቸው ላይ በመቆም ማመስገንና
መዘገር፣ እንደኛው መንዙማ አይነት ሙዚቃዊ ቃና ያለው የምስጋና መዝሙሮችን ማሰማት ወዘተ ከፈጣሪ ጋር የበለጠ የሚያቆራኙ መንገዶች እንጂ ክፋት የላቸውም የሚሉ የሱኒ መስመር ተከታዮች እራሳቸውን ሱፊዎች ብለው ይጠራሉ፡፡
ታዲያ ይህንን አስተሳሰብ የሚቃወሙ የሀይማኖች ሊቃውንቶችም አልጠፋም፡፡ እስልምና በነብዩ መሀመድ ጊዜ ከነበረው አቋም መለወጡ አስፈላጊ አይደለም፡፡ በጎም ሆነ መጥፎ ጭማሪዎችን በሀይማኖቱ ውስጥ ማካተት አያስፈልግም የሚሉ እራሳቸውን ሰለፊ ብለው የሚጠሩ ሱኒዎችም ብቅ
ብቅ ማለታቸው አልቀረም፡፡ ከነዚህም መካከል ገዝፎ የሚታየው ከ 1703-1792 ዓ.ም የኖረው መሀመድ አብዱልዋሀብ ይገኝበታል፡፡ የበኑ ታሚም ንዑሰ ጎሳ አባልና በአሁኗ ሳኡዲ አረቢያ ናጅድ ክልል ውስጥ በምትገኝ ኡያይና መንደር የተወለደው አብዱልዋሀብ አባቱ የሀይማኖት ሊቅ በመሆናቸው ባደረበት ተፅእኖ እሱም እስልምናን ለማጥናት ደቡባዊ ኢራቅ ባስራ ከተማ ድረስ ይሄድ እንደነበር ይነገራል፡፡ በመካ ውስጥ አስተማሪው የነበሩት ኢብን ሁማይዲ የተባሉ አዋቂ አብዱልዋሀብ በትምህርቱ ደካማና ከመምህሩ ጋር ጥሩ መግባባት የሌለው ልጅ ነው ብለው መስክረውበታል፡፡ ከዛም ወደ መዲና ሄዶ በመሀመድ ሀያ አል-ሲደህ መምህርነት ትምህርቱን ተከትሏል፡፡ በዚህም ቆይታው የሰለፊ አስተሳሰብ አፍላቂ ተብሎ የሚታመነው የ 13ተኛው ክ/ዘመን የሀይማኖት ሊቅ ኢብን ታይሚያን አስተምህሮ ያስጨበጡት መምህሩ በእስልምና ውስጥ ስለተካተቱ አዳዲስ ጭማሪዎች ኢ-ትክክለኛነት በአእምሮ እንዲሰርፅ አስተዎፅኦ አድርገውበታል ይባላል፡፡ አብዱልዋሀብ ወደ ባሰራ ሄዶ ሀብታም ሴት አግብቶ ወደ አምስት አመታቶች እዛው ኢራቅ ከቆየ በኋላ ወደ ትውልደ ሀገሩ ሳኡዲ አረቢያ በተለይም ናጅድ ክልል ተመልሷ የሰለፊ አስተሳሰብን ማስተማር ይጀምራል፡፡ በጊዜው በነጃድ ክልል እንግዳ የነበሩ አስተሳሰቦችን መስበክ ቀጥሏል፡፡ ለምሳሌ የቅዱሳንን መዘክር መቆም አለበት፣ መቃብርና ሀውልቶች ላይ ቆሞ መፀለይ ሀጥያት መሆኑን፣ ዝሙት የፈፀመች ሴት በድንጋይ ተወግራ መገደል ይኖርባታል ወዘተ የሚሉ ፅንፈኛ አስተሳሰቦችን ለማስረፅ ሙከራ አድርጎል፡፡ በጊዜው የነበሩ የሀይማኖት አባቶች አብዱልዋሀብ ይህንን ፅንፈኛ ትምህርቱን እንዲያቆም ከማስጠንቀቅ አልፈው አብዱልዋሀብ በተገኘበት
እንዲገደል አዘዙ፡፡
አብዱልዋሀብም ከአሁኗ ሪያድ ከተማ አጠገብ ወደምትገኘው አል-ዲርአያህ ከተማ በመሰደድ ገዥውን መሀመድ ኢብን ሳኡዱን ከለላ ለመነ፡፡ የአል-ሚግሪን ቤተሰብ የሆነው የአል-ዲርአያህ ገዢ መሀመድ ኢብን ሳኡድ ኢብን መሀመድ ኢብን ሚግሪን ካለው ግዛቱን የማስፋፋት ህልም አንፃር
ከመሀመድ አብዱልዋሀብ ጋር በ 1744 ዓ.ም ስምምነት አድርጓል፡፡ በተጨማሪም መሀመድ ኢብን ሳኡድ ልጅ አብዱልአዚዝ የአብዱልዋሀብን ሴት ልጅ እንዲያገባ በማድረግ ግንኙነታቸውን አጠናክረው ኢብን ሳኡድ በመጀመሪያ የናጅድ ክልልን ቀጥሎም መካና መዲናን በማጠቃለል የዛሬዋን ሳኡዲ አረቢያን በቁጥጥር ስር አዋለ፡፡ በዚህ የመስፋፋት ሂደት ውስጥም አብዱልዋሀብ እስልምናን “የማንጻት” ስራ እየሰራ የነ ኢብን ሳኡድ ገዥነትን መለኮታዊ እሴቶች እያጎናፀፈው ኢብን ሳኡድ የመጀመሪያውን የሳኡዲ ግዛት እንዲመሰረት አገዘው፡፡ ከዚያ ጊዜ አንስቶ የተመሰረተችውን አዲሷን አገር በአባቱ በሳኡድ ስም ከመሰየም አልፎ እስከዛሬ ቀን ድረስ የሚፈራረቁት ንጉሳንና ልኡላኖች ከአል-ሚግሪን ቤተሰብ ሳይወጣ ፀንቶ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡ በተዛማጅም የመሀመድ አብዱልዋሀብ ተተኪ ዝርያዎች እስካሁን ድረስ በሳኡዲ አረቢያ ከንጉሳን ቤተሰብ ያልተናነሰ ክብር ይዘው የሀገሪቱን የሀይማኖት ተቋማት በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር አድርገው እያስተዳደሩ ይገኛሉ፡፡ እንግዲህ በዛሬዋ ሳኡዲ አረቢያ የምናየው
የሀይማኖትና የመንግስት ቁርኝት ጋብቻው የተፈፀመው በ1744 ዓ.ም በመሀመድ አብዱልዋሀብና በመሀመድ ኢብን ሳኡድ መካከል መሆኑ ነው፡፡
በ6ኛውና በ7ኛው ክፍለ ዘመን ተከስቶ የኖረው የመጀመሪያው የእስልምና ሰንጥቆች ማለትም ሺዓና ሱኒ ወደ ኢትዮጵያ አለመዛመቱን አውስተናል፡፡ ዳሩ ግን በ 18ኛው ክፍለ ዘመን በሳኡዲ አረብያ የተከሰተው ሁለተኛው የሱኒ ተከታዮች ስንጠቃ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ ተፅእኖ ማሳረፍ
አልቀረም፡፡ በኢትዮጵያ በተለይም በቤጃ ህዝቦች መስፋፋትና በአክሱም ስርወ- መንግስት ላይ ከደረሱት ጫና ጀምሮ እስከ መካከለኛው ክፍለ ዘመን የአፄዎችና የሙስሊም ኤምሬቶችና ሱልጣሜቶች መካከል በነበረው ታሪካዊ ቁርቁስ አሸናፊ ሆኖ የወጣው የአፄዎች አገዛዝ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ሲያሳርፍ የነበረው ጫና በታሪክ ተመዝግቦ የሚገኝ ሀቅ ነው፡፡ እስልምናም ልክ እንደ ክርስትናው ከአረቡ አለም በተለይም ከሳኡዲ አረቢያ ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ የነብዩ መሀመድ ተከታዮች አማካኝነት ከኢትዮጵያውያን ጋር ትውውቅ ፈጥሮ በመቀጠል የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን እምነቱን ተቀብለው በሂደት እስልምና በሀገሪቷ በተለያዩ አቅጣጫዎች መስፋፋቱ ይነገራል፡፡ ይህንን ታሪካዊ ሀቅ በማዛባት
የእስልምና እምነት ተከታይ መጤ እንደሆነና አልፎ ተርፎ መሬት ባለቤት መሆን እንደማይችል አፄዎቹ እስከማወጅ ደረሱ፡፡ ሙስሊሞቹ የሀይማኖት በአላትን እንደ ብሄራዊ በአላት ተቆጥሮላቸው ማክበር የጀመሩት እንኳን ደርግ የአፄ ሀይለስላሴን መንግስት ገርስሶ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር
ካቋቋመ በኋላ መሆኑን የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡
በዚህ ጫና ስር የነበረውን የኢትዮጵያ ሙስሊም ትንሽም ብትሆን እስትንፋስ ያገኘው በ1936-41 ዓ.ም በነበረው የጣልያን ቀኝ ግዥዎች ቆይታ ጊዜ እንደነበር ይነገራል፡፡ ሙስሊሞቹ ቤተ-መስጂድ እንዲገነቡ፣ እምነታቸውን በይፋ እንዲያራምዱ አልሮ ተርፎም ወደተለያዩ ሀገራት እየሄዱ የሀይማኖት
ትምህርት እንዲቀስሙ ተፈቀደላቸው፡፡ በዚህ መሰረት በተለይም በኢትዮጵያ የእስልምና ማእከልነት በምትታወቀው ሀረር ከተማ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የሀይማኖቱ አዋቂዎች የእድሉ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ሼክ ዩሱፍ አብዱራህማን እና ሼህ አብደላ መሀመድ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሼክ ዩሱፍ ከመካ እና መዲና ትምህርታቸውን ሲመለሱ በስለፊ አስተምህሮ ተጠምቀው እንደነበር ይነገራል፡፡ በሀረር የሚገኙትን የመድረሳ / የሀይማኖት ት/ቤቶች በሳኡዲ ከቀሰሙት የወሃቢ (የአብዱልዋሃብ ተከታዮች አስተምህሮ) አጥባቂ እስልምና መንፈስ እንዲዋቀሩ አድርገዋል ይባላል፡፡ ይህ አቋማቸው ከአፄ ሀ/ስላሴ ጆሮ ድረሶ ኖሮ በግዴታ ከሀገር ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ሼህ አብደላ መሀመድ የእስልምናና ክርስትና ሀይማኖት ተቻችሎ መኖርን የሚሰብኩ፣ በጎ ጭማሬዎችን እንደ ቁዱሳንን መዘከር አይነቶች አይከፋም ባይ የሱኒ ክፍል የሆነው የሱፊ አስተምህሮትን የሚሰብኩ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡ ምናልባትም በሁለቱ ሼኮች መካከል የአስተሳሰብ ብቻም ሳይሆን የወደ ቤተመንግስቱ ባለ ሟልነት የመቅረብ ፍክክር ሳይኖር የቀረ አይመስልም፡፡ ምክንያቱም ፅንፈኛ አክራሪ ተብለው ከሀገር የተሰደዱት ሼህ ዩሱፍ ጃንሆይ ወደሀገር እንዲመለሱ ፈቅዶውላቸው እንዲያውም የመጀመሪያው ቅዱስ ቁርአን ወደ አማርኛ ሲተረጎም የበላይ ተቆጣጣሪ ሆነው ሲሾሙ ለዘብተኛ ናቸው፣ መቻቻልን ይሰብካሉ የተባሉት ሼህ አብደላ በተራቸው ከሀገር እንዲሰደዱ ተደርገው እስከ እለተ ሞታቸው ኑራቸውን በቤሩት አድርገው ነበር፡፡
የሁለቱ ሼኮች የመዲናና የቤሩት አስተምህሮት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በተለይም ሀረሮች በሰለፊና በሱፊ መስመር እንዲሰነጠቁ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ ግን የሰለፊና ሱፊ ሰንጥቆች በኢትዪጵያን ሙስሊሞች ብቻም ሳይሆን በፌደራል መንግስት በኩልም “አስቸኳይ እና አንገብጋቢ” ጉዳዬች ከሚባሉት ፈይሎች መካከል የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮን፣ የደህንነት መ/ቤቱንና የፌደራል ጉዳዮች ሀላፊዎች ጠረጴዛን ማጨናነቅ መጀመራቸው ይነገራል፡፡ የሰለፊ ተከታዮች ሀይማኖትን አጥብቆ የመያዝና እምነታዊ ተግባራትን ወደነበረበት በመመለስ ላለፉት 1400 ዓመታት ላላነሰ የተከናወኑት ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካ ለውጦችን ላለመቀበል ቆርጠው የተነሱ ይመስላሉ፡፡ ለምሳሌ በሳኡዲ አረቢያ እና በጎረቤት ሱዳን የምናየው ሃይማኖታዊ የፖለቲካ አስተዳደር ሴት ልጅን መኪና መንዳትና ሱሪ መልበስ ከመከልከል ጀምሮ ጥፋት አጠፋ የሚባሉትን ዜጎች ከእጅ መቁረጥ እስከ አንገት መቅላት ድረስ የሚሄድ በሰው ልጆች አእምሮ እድገት አብረው እየጎለበቱ የመጡትን መሠረታዊ የሰው ልጆች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ያላገናዘበ እርምጃ ሊወሰዱ ይታያሉ፡፡
በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንደሚባለው ይህ የሰለፊዎች አክራሪ አካሄድ አልበቃ ብሎ የሰለፊ ፅንፈኛነት በተለይም ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ እያበበና እየተስፋፋ መምጣት ጀመረ፡፡ የአሜሪካ መንግስት እንደ ቢንላደን ያሉትን ፅንፈኛ የሰለፊያ ተከታዮች በመደገፍና በማስታጠቅ አፍጋኒስታን
ውስጥ የሶቨየት ህብረት ጦር ለማስመታት ሲጠቀምባቸው መቆየቱ ፅንፈኛ የሰለፊ አስተሳሰብ እንዲጎለብት በር መክፈቱ አይካድም፡፡ ከሶቨየት መንኮታኮት በኋላ ግን የአሜሪካ መንግስት በአረቡ አለም በተለይም ነዳጅ አምራች በሆኑት ሀገራት ላይ የሚያደርሰውን ምዝበራ መቃወም በጀመሩት አክራሪ ሰለፊያዎች ላይ ፊቱን ማዞር ጀመር፡፡ ከኮሚኒዝም ሞት በኋላ ሌላኛው የአለም ጠላት የእስልምና አክራሪነት መሆኑን አሜሪካ አወጀች፡፡ የነፍስ አባት የነበረችለትን የአፍጋኒስታን የሙጃሂደን እንቅስቃሴ ማሽመድመድ ቀጠለች፡፡ ይህም በቀድሞ ወዳጆች መካከል የተከሰተ ቁርሾ አምርሮ ለሴፕቴምበር 2001 የኒውየርክ መንትያ ህንጻዎች ፍንዳታ አደረሰን፡፡
ከዚህ በኋላ አሜሪካ ሳኡዲ አረቢያን ጨምሮ አለምን ከጎኗ አሰልፋ በአክራሪ እስልምና ስም ጡንቻቸው ያጎለበተችላቸውን ሙጃሂዲኖች ብቻም ሳይሆን የአሜሪካንን የአለም አውራነት ለመቀበል ሲያንገራግሩ የቆዩ ሀገራትንም ማሽመድመድ ቀጠለች፡፡ ይህ የፖለቲካ አሰላለፍ ለውጥም ለሰለፊያ
አክራሪዎች ዕድል በመስጠቱ ብዙ ወጣቶችን በሀይማኖት ስም ለመመልመል ሰፊ በር ከፈተላቸው፡፡ ሰለፊዎችም እጃቸው ከአፍጋኒስታንና ፓኪስታን አልፎ የአረቢያን ምድር አቋርጦ ምስራቅና ሰሜን አፍሪካ ማድረስ ቻሉ፡፡ እነ አል-ኢትሃድና አል-ሸባብን የመሳሰሉት ጀሃዲስት ድርጅቶች በኢትዮጵያ
ምስራቃዊ በር በኩል ተንሰራፍተው መንቀሳቀስ ተያያዙት፡፡ ሌላው ቀርቶ የሰለፊያ አስተምህሮ እምብርት ለሆነች ሳኡዲ አረቢያም የጀሃዲስት ሰለፊያዎች እንቅስቃሴ ከፍተኛ ስጋት ፈጠረ፡፡ በሳኡዲ አረቢያ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታዎች መስማት ከጀመሩ ሰንበትበት ብሏል፡፡
በዚህ መሰረት ሶማሊያ ላይ የተንሰራፈው የጀሃዲስት ሰለፊያዎች እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ ስጋት እንደሚሆን መተንበዩ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ይህንን ስጋት ግን ከሲ.አይ.ኤ ወይም ከሞሳድ በሚገኙ መረጃዎች ብቻ እንደወረደ ተቀብሎ ሞቀድሾ ድረስ ገብቶ መግጠሙ ተጋቢነቱ ብዙ ሊያነጋግር ይችል
ይሆናል፡፡ የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ ስጋቷን በይፋ ከመናገር አልፋ ጦሯን እስከ መቋዲሾ ላከች፡፡ የጀሃዲስት ሰለፊያዎች ጥርስ ውስጥ ያስገባት አንድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል መገመቱ አይከፋም፡፡ በዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ ነው በቴላቪቭ ዩኒቨርስቲ የአፍሪካና የመካለኛ ምስራቅ ጥናት አዋቂ የተባሉት ፕሮፌሰር ሀጋይ ኤርሊግ በጥናት የተደገፈ ያሉትን የሰለፊያ እንቅስቃሴ አደገኛነት ለኢትዮጵያ መንግስት ማስጠንቀቅ የጀመሩት፡፡ እንደ ፕሮፌሰሩ ገለፃ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከወዲሁ በለዘብተኛው የሱፊ መስመር ማደራጀትና በአንክሮ መቆጣጠር ካልተቻለ የአክራሪ ሰለፊያዎች
እንቅስቃሴ ሰለባ ሊሆን እንደሚችል በማስገንዘብ ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ-ሙስሊም የሰለፊያ መስመር ውስጥ ከገባ አደጋው ለሀገሪቷ ብቻም ሳይሆን ለጠቅላላ ለአፍሪቃ ቀንድ እንደሚሆን በአፅንኦት ያስረዱት፡፡
ከሶማሊያ አል-ሸባብ ሀይሎች ሊሰነዘር የሚችለው የመልስ ምት የሚያስበረግገው የኢትዮጵያ መንግስት፣ አንዳንድ በኢትዮጵያ ምስራቃዊው የሶማሌና ምዕራባዊው የኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ተከሰቱ የሚባሉ እስላማዊ ጽንፈኛ ድርጊቶች ጋር የነፕሮፌሰር ሀጋይን ጥናታዊ ማስጠንቀቂያ በማዳመር ስጋቱ
እንዳለበት በይፋ እስከማሳወቅና መፍትሄ የተባሉትን አማራጮች ከኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሁኔታ ጋር ሳያዛምዱ እንደወረደ ተቀብሎ እንቅስቃሴ ጀመረ፡፡ ዋነኛ አማራጭ ተብሎ የተያዘው ወደ ቤሩት ተሰደው ኑሮአቸውን እዛው ከከተሙት የሼክ አብደላ አል-ሀረሪ አስተምህሮ በዘመቻ መልክ
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የማጥመቁ ስራ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ጃንሆይ ሼክ አብደላን ከኢትዮጵያ ሲያባርሯቸው ለሀገር ደህንነት አስጊ ናቸው ተብሎ ቢሆኑም በቤሩት ቆይታቸው ግን ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውን መሳ ለመሳ የሚሆኑ የቤሩት የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮችን አቻችሎ የሚያኖር ፣ለዘብተኛና ተራማጅ የሆነ የሱፊ እስልምና አስተምህሮ በመስበክ የታወቁ ነበሩ፡፡ የሳቸው ተከታዮች ከሀይማኖታዊ ተቋምነታቸው ባለፈ በፓርላማ የፖለቲካ ወንበር እስከ መያዝ የደረሱ በተለምዶ አል-አህባሽ ማለትም የሀበሻው ተከታዮች በመባል እስከመታወቅ የደረሱ ናቸው፡፡ ተራማጅ የሆነ የሱፊ መስመርን መከተላቸውና መስበካቸው ብዙውን የአውሮፓ ሀገራት መንግስታትን ልብ ማሸነፍ እንዳስቻላቸው ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስትንም ልብ መሳባቸው አይቀሬ ነው፡፡ ችግሩ ያለው ግን እዚህ ላይ አልነበረም፡፡ የአህባሽን አስተምሮ በቀጥታ በማውረድ ህዝበ-ሙስሊሙን በአንድ የአስተሳሰብ መስመር ውስጥ ለመጠርነፍ ከመሞከሩ በፊት አስፈላጊ ጥናቶች አለማካሄዳቸው ላይ ይመስላል ችግሩ፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ስም ወጥቶላቸው የሱፊ ተከታዮች ናቸው ተብለው ባይነገርላቸውም ቅሉ የዘመናት ሀይማኖታዊ ክንዋኔዎቻቸው ሁሉ የሚያሳዩት በለዘብተኛው ሱፊ መስመር ውስጥ መሆናቸውን ነው፡፡ ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር አብረው መኖር እንዳለባቸው እነ ሼክ አባድርን፣ እነ ሼክ አብዱልቃድር ጀይላኔንና ሼክ ሁሴን መዘከር ፣የነብዩ መሀመድን የልደት ቀን ማክበር ፣ ሴቶቻቸው ሱሪ መልበስና መኪና መንዳት እንደሚፈቀድላቸው ለማስተማር መሞከሩ ከንቱ ልፋት ያሰኛል፡፡
ምንም አይነት ጥንቃቄ ሳይደረግለት ወደ ህዝብ እንዲወርድ የተሞከረው የአህባሽ አስተምህሮ ከላይ ከጠቀስናቸው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አስቀድመው ያከናውኑት የነበሩትን ማህበራዊና ኃይማኖታዊ ክንዋኔዎች ለህዝቡ ለማስተማር ከመዳዳት ይልቅ የአህባሽ አስተምህሮ በውስጡ ያዘለው
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በቀላሉ ሊገዙት የማይቻላቸው አስተሳሰቦች ላይ ነበር አትኩሮት መስጠት የሚገባው፡፡ የሶላት አሰጋገድ፣ የቂብላ አቅጣጫ፣ የወለድ ጉዳይ፣ የሴቶች ሃይማኖታዊ ተቋማት ላይ ሊኖራቸው ስለሚገቡ ድርሻዎች ወዘተ በህዝበ-ሙስሊሙ ዘንድ ትንሽ ግር የሚያሰኙ አስተሳሰቦችን ትኩረት ተደርጎባቸው በምን መልኩና ሁኔታ ወደ ህዝብ መውረድ እንዳለባቸው ጥናት ሳይደረግ በጅምላ እንዲዘረገፉ ተደረጉ፡፡ ይህ ድርጊት ምናልባትም በኢትዮጵያ አስቀድሞ ሰርፆ ገብቶ ሊሆን ለሚችለው የሰለፊያ እንቅስቃሴ በር በመክፈት ህብረተሰቡ አህባሽ አስተምህሮን ገና ምንነቱን በወግ ሳያጤነው እዲገፋውና አልፎ ተርፎም አል-አህባሽ እስልምናን ለመበረዝ ሆን ተብሎ በእስራኤሎች የተፈበረከ ነው ለሚለው የማጥላላት ዘመቻ ሰለባ ሆነ፡፡ በተያያዥነትም በየትኛውም የእምነት ተቋማት ውስጥ ሲከሰት በሚችል በተለምዶ ከሚንቀሳቀሱት (ነባር አባቶች) እና በተማረው አዲስ ትውልድ መካከል በሚፈጠር “እኔ አውቃለሁ” ፉክክር ሰለባ ለመሆንም በቃ፡፡ኢኮኖሚያዊ የጥቅም ጉዳይም እንዳለበት በሰፊው
ይነገራል፡፡ የዛሬ 60 ዓመት ገዳማ በሀረር የተከሰተው የሼክ የሱፍና የሼክ አብደላ ክስና ፉክክር ከሁለት ትውልድ በኃላ የአስተሳሰብ፣ የጥቅምና የስልጣን ሹኩቻን ደራርቦ በድጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ነው፡፡
በመጅሊስም ሆነ በአወሊያ የትምህርት ተቋም ካለው የሰለፊና የሱፊ የአስተሳሰብ ልዩነቶች በተጨማሪ የመጅሊሱን ስልጣን ለመቆጣጠርና አወሊያን ጨምሮ ሌሎች እስላማዊ ተቋማት ከተለያዩ የአረብና የሙስሊም ሀገራት፣ ተቋማትና ግለሰቦች ፈሰስ የሚደረገውን ከፍተኛ መጠን ያለው የእርዳታ
ገንዘብ የመቆጣጠር አላማን ያነገበ ህዝብ- ሙስሊሙን ግን በአስተሳሰብ መስመሮች የሚለይ ከዛም እልፍ የክርስቲያኑን ወገን የሚያስደነብር አሉባልታዎችና አልፎ ተርፎም ድርጊቶች ሲከናወኑ ማስተዋል ተጀምሯል፡፡ በመንግስት በኩልም ከጀሀዲስት ሰለፊዎች በተጨማሪ የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎች በሀይማኖታዊ መብት ጠያቂዎች ጀርባ ሀገሪቷ ላይ ሁከት የመፍጠር አላማ አላቸው በማለት መወነጃጀል ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ በተለይም በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ቀደም ተብሎ በኦብነግና ኦነግ ደጋፊነታቸው የሚታሙ አካባቢዎች አሁን ደግሞ በሰለፊያ ጽንፈኛ አክራሪነት ከመከሰሳቸውም ባሸገር አንዳንዴም መጎሸማቸው አልቀረም፡፡ በተያያዥ የሰሞኑ የአወሊያና የአንዋር መስጊድ የህዝበ-ሙስሊሙ የመብት ጥያቄ የተባሉ ትዕይንቶች በኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪ ከተባሉ ተቃዋሚ የፓለቲካ ድርጅቶች ጋር እየተያያዙ ሲከሰሱ ተሰምቷል፡፡
በዚህ መሰረት በኢትዮጵያውያን የሱኒ እስልምና ተከታዮች ዘንድ ጠንከር ያለ ተፅዕኖ እየፈጠረ የሚገኘው የሰለፊና ሱፊ አስተሳሰብ ውዥንብር ሳይሆን የመንግስት ጥናት የጎደለው አቀራረብ እና ለተፈጠሩት አለመግባበቶች እየተወሰደ ያለው የሀይል እርምጃ ይመስላል፡፡ በአወሊያና አንዋር መስኪዶች ተቋውሞቸው ሲያቀርቡ የነበሩት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሙስሊም ማህበረሰብ ከክርስቲያኑ ወገናችን ጋር አብረን አንኖርም፣ እንደ አል-ሸባብ ሰለፊዎች ያመነዘረች ሴት በድንጋይ ትወገር፣ ጫት ይዞ የተገኘ አንገቱ ይቆረጥ ወዘተ የሚል ፅንፈኛ አስተሳሰብ ሲያስተጋቡ የተሰሙ አይመስልም፡፡ መጅሊሱ ከሀይማኖት ተቋሙነቱ በዘለለ የፖለቲካ መሳሪያ መሆኑ ሰልችቶናልና ይውረድልን፣ የመጅሊስ አባላትን በቀበሌ ሳይሆን በቤተ-መስጅድ መምረጥ ይኖርብናል፣ መንግስት እያሰፈፈ ያለው የአህባሽ አስተምህሮ የማንቀበለው አስተሳሰቦች አዝሏል ብሎ መቃወምና የመብት ጥያቄ
ማንሳት ሁሉንም በደፈናው በአክራሪ ፅንፈኛ የሰለፊያ ጅሃዲስት ተከታይነት መክሰሱ ከሚያመጣው ፈይዳ ይልቅ ህብረተሰቡን በተቃራኒው ወደ ፅንፈኛነት የሚጋብዝ ይመስላል፡፡
በመሆኑም የመብት ጥያቄዎችን፣ የሰለፊና ሱፊ አስተሳሰብ እንቅስቃሴዎችን፣ ፖለቲካዊ ተቃውሞን፣ የፖለቲከኞች በሀይማኖት ሰርጎ መግባትን፣ የሀይማኖት አጥባቂነትንና ፅንፈኛ አክራሪነትን፣ በህብረተሰቦች መካከል በነበሩ ታሪካዊ ቁርሾ የሚከሰቱ አንዳንድ አረመኒያዊ ድርጊቶችን
ወዘተ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ (ሙስሊሙን ጨምሮ) የምር ስጋት ከሆነው ፅንፈኛ የሰለፊያ እንቅስቃሴ ለይቶ ማየት መቅደም ይኖርበታል፡፡ ለዘብተኛ የሱፊ ተከታይ የሆኑትን የአል-አህባሽ አስተምህሮ እንደወረድ ህዝቡ ላይ ከመጫን ይልቅ እንደማንኛውም የእምነት አራማጆች ከሌላው ባላነሰ ወይም ባልበለጠ መልኩ መብታቸው ተከብሮ እንዲንቀሳቀሱ መፍቀዱ ብሎም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ዜጋ የሱኒና የሺዓ እንዲሁም የሰለፊ ሱኒና የሱፊ ሱኒ የአስተምህሮ መስመሮችን የመከተል ሙሉ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ፅንፈኛ የሰለፊ አስተሳሰቦች የህዝበ-ሙስሊሙን አእምሮ እንዳይጠልፉት መጠንቀቅ ለጊዜው በቂ እርምጃዎች ሊሆኑ በተገባ፡፡ የፖለቲካ ተቋውሞን ለመከላከል ወይንም ከአንዳንድ ወቅታዊ ሁኔታዎች የህብረተሰቡን አእምሮ ዘወር ለማድረግ ተብሎ ብቻ በህዝበ-ሙስሊሙ መካከል እንዲሁም በሙስሊሙና በክርስቲያኑ ህብረተሰብ መካከል ዘላቂ ልዩነትና ስጋቶች የሚፈጥሩ የማዋከቢያ ውንጀላዎች ለዘመናት የቆየውን የኢትዮጵያውያን እሴቶች ከመሸርሸሩም ባሻገር የተፈራው የሀገር ና የህዝብ ድህነት ጉዳይንም የምር ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ውጤቶች ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ከወዲሁ መገመቱና ማንኛውም እርምጃ በጥናት የተደገፈና ፍጹም ኃላፊነት የተሞላበት ማድረጉ ብልህነት ብቻም ሳይሆን ከታሪከ ተጠያቂነትም እንደሚያድን አውቆ መንቀሳቀሱ ተገቢ ይሆናል፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በ1990ዎቹ አካባቢ የተከሰተውን የክርስቲያኖች መከፋፈል ማሰብ ግድ ይለናል፡፡ ለዘመናት በመንግስታዊ ሃይማኖት ውስጥ የኖረችው ኢትዩጵያ ኦርቶዶክስን መቃውም ቀርቶ በህዝበ ሙስሊም ጎረቤቶቻችን ከግንባር ጉንጫቸው የመሰቀል ጥቁራት ተነቅሰውማል፡፡ አሁን ክርስቲያን ይሁኑ አደለም ግን ተጽኖው ምን ያል ስር ሰዶ ነበር ነው፡፡ያኔ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት አገሪቱን ለመስፋፋት ሲታትር በቤተክርስቲያኖች ጎዋሮ ስር ነበር፡፡ ይፋ ለመሆን በአንድ ምኩራብ ሁለት የተለየ አስተሳሰብ አስተናግዶዋል፡፡ ግን ነጻነታቸውን በሰላም ምድር የራሳቸውን የክርስቶስ ስብክት በራሳቸው ቤተ እምንት መሩ ስውም ወደ ወደደው አመራ፡፡ እናም ሙስሊም ኢትየጵያውያንም እንደየ አሰተሳሰባቸው እምነታቸውን በመስጊዳቸው ቢያደርጉ ስማቸው በሌላ አይለወጥም ፡፡ ይቀጥላል….
አትዩጵያውያን መዋደዳችን ለዘላለም ይኑር!!!
By Ayele Addis

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar