torsdag 29. august 2013

የሃገራችንን ህልውና የሕዝባችንን ነፃነት እናስመልስ!!!

ለአንድ ህዝብ ሃገር ማለት የመኖር ዋስትናው ተጠብቆ ሳይሸማቀቅ፣ ሳይበደል፣ ፍትህ ሳዩጓደል፣ የዜግነት መብቱ ተጠብቆ የህግ ከለላ አግኝቶ በነፃነት የሚኖርብት ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን ሃገር መሆን ከተሳናት እንሆ ሃያ ሁለት አመት ተቆጠረ፡፡ የደርግ ስርዓትን ተክቶ በትጥቅ ትግል መንበሩን የተቆናጠጠው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ የፖለቲካ ስልጣኑንም ሆነ የኤኮኖሚ አውታሩን በአንድ ብሄር ብቻ አደራጅቶ የተቀረውን ኢትዮጵያዊ እንደ ዜጋ የመኖር መብቱን ገፎ በግዞት ያኖረዋል፡፡

ይህ ፈላጭ ቆራጭ ግፈኛ ብድን ሰብአዊ መብት አለማክብሩ ብቻ ሳይሆን ሃገርን የማፍረስ ጭምር አላማና ተልኮ ስላለው የሚፈልገውን ለማድረግ ማንም ምንም ተቃውሞና ትችት እንዲያቀርብለት አይፈልግም፡፡ ስለሆነም በሃገሪቱ ባለው ህገ -መንግስት፣ ያውም እራሱ ባፀደቀው መሰረት የሚንቅሳቅሱ ኢትዮጵያዊያን የሲቪክ ማህበራት፣ የነፃው መገናኛ ብዙሃን አባላት፣ የዴሞክራሲ ተሟጋቾችን፣ የሰብአዊ መብት ታጋዮችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እነዚህንና ሌላውን ንጹሃን  ዜጎችን ሳይቀር እያዋከበና እያሳደደ ገሚሱን ስም እያወጣ ወህኒ ሲያጉር ከፊሉን ደግሞ በሃገራቸው የመኖር መብት ነስቶ እንዲስደዱ ያደርጋል፡፡

 1997 ዓ.ም በጭላንጭል የታየውን የመደራጀት መብት ተጠቅመው ህዝብን ያደራጁና በኋላም በምርጫው የህዝብ ይሁንታ አግኝተው በካርድ የተመረጡ የፖለቲካ ድርጅቶችን ይህው ፈላጭ ቆራጭ ቡድን በማን አለብኝነት አለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚያውቀውን ውጤት ለውጦ እስካሁን ድረስ ባልመረጠው ህዝብ ጫንቃ ላይ ተፈናጧል፡፡ በወቅቱም ሽንፈቱን ላለመበቀል በመቶዎች  የሚቆጠሩትን በጠራራ ፀሃይ ሲገድል፣ አስር ሺዎችን ወደ ማጎሪያ ማጋዛቸው፣ መደብደባቸው፣የተቀሩት ማሳደዳቸው አለም የሚያቀው እውነታ ነው፡፡ 

ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ ያየውን መከራና ፍዳ ቅን የሆኑ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ምስክር ናቸው፡፡ይህ አምባገነን ቡድን ህዝቡን አፍኖ፣ አሸማቆና አንገት አስደፍቶ የሄደበት የአፈና መዋቅር 2005ዓ.ም ላደረገው የይስሙላ ምርጫ ጉልበት ሆኖት ዘርፎም፣ አታሎም፣አጭበርብሮም 99.6% አሸነፍኩ ሲል መደመጡ ብዙዎችን ያስገረም ጉዳይ ነበር፡፡ 
የህዝብን የነፃነት ጥያቄን ለማፈን በተለይም በሰሜን አፍሪካ ከአረቡ አብዮት ጋር በተያያዘ ህዝብ ይነሳብኛል ብሎ የሰጋው የወያኔ ቡድን የተለያዩ አፋኝ ህጎች ሲያወጣ ከርሟል፡፡ ከዚህም አንዱ የፀረ- አሸባሪ ህግ ነው፡፡በዚህ ህግ ብዙሃን የነፃነት ታጋዮች ከሞት እስከ እድሜ ይፍታህ ተፈዶባቸዋል ፡ ይተቀሩትም የህሊና እስረኞች አሁን ባለንበት ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በየቀኑ የሚገደሉባት፣ የሚደበደቡባት ቶርች የሚደረጉባት ስብእናቸው እየተዋረደ በዘራቸው የሚሰደቡበት በተለያዩ ቦታዎች ታጉረውና ያለፍርድ ተረስተው የሚገኙባት በአጠቃላይ ለፍትህ እና ለነፃነት ለሚታገሉ ንፁሃን ዜጎች የምድር ሲኦል የሆነች ሃገር አርገዋታል፡፡ ገዥው ብድን የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ከሚጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ የህዝብን የማወቅ መብት መገደብና እሱ ከሚለው ውጪ ምንም እንዳይሰማ፣ እንዳያይ አማራጭ የመገናኛ ብዙሃንን ማፈን ትልቅ ስራ አድርጎታል፡፡ ስለዚህም ለአገዛዙ እንዲመቸው ለ90 ሚሊዮን ህዝብ አንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ፣ አንድ ሬድዮና፣ አንድ በሁለት ቋንቋ የሚታተም ጋዜጣ ብቻ በዚህ ዘመን አለም በመረጃ መረብ በተጥለቀለቀችበት ጊዜ ከራሱ ውጪ ለህዝብና ለሃገር ደንታ የሌለው አምባገነን መንግስት ሌሎች አማራጮችን ዘግቷል፡፡ 

ከዚህ ሁሉ የወያኔ አፈናና ግፍ በኋላ ቢዘገይም(ቢረፍድም) በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከተደራጁ ለቁጥር ከሚታክቱ ድርጅቶች ውስጥ የሃገሪቱ ህገ-መንግስት በሚፈቅደው መብታቸውን ተጠቅመው ህዝብን በንቃት በማደራጀት ትግላቸውን እያፋፋሙ ያሉት ሰማያዊ ፓርቲና አንድነት የወያኔ የእግር እሳት እየሆኑ በት እንዳለ ሰሞኑን በተለያዩ የሃገራችን ክልሎች እየሆነ ያለውን እልህ አስጨራሽ ትግል እያየን ነው፡፡ 

ይህ ሲጀመር በሰማያዊ ቀጥሎም በአንድነት ፓርቲ የተጀመረው ፍርሃትን የሰበረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ዘርኛውን የወያኔ ስርዓት ምን ያህል እርቃኑን እንዳስቀረውና ኢትዮጲያን እየመራ ያለው ስርዓት ለህግ ተገዢ እንዳልሆነ ፍንትው አርጎ ያሳየን አጋጣሚ ነው፡፡ የመንግስት ስልጣን ብቻ ሳይሆን በዘረፋ ያካበቱትን ሃብትና ንብረት ለማስጠበቅ ፍጹም ስርዓት በጎደለው መልኩ የእውር ድንብራቸውን የሚወራጩት የወያኔ ካድሬዎች ላለቆቻቸው ለመታመን ንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሱ ያሉት ወከባና እንግልት የስርዓቱን ሃላፊነት የጎደለው ተራ የውንብድና ተግባር ያሳያል፡፡ 

ስለሆነም ሁል ጊዜ ስለበደላችን፣ በሃገራችን ህልውና ላይ እያንዣበበ ስላለው አደጋ ስንተርክና ስንቆዝም አንድም ጠብ የሚል ነገር ሳይገኝ ሁለት አስር አመታት ተቆጠረ፡፡ ጊዜው የተግባር ነው አሁን ያለውን የህዝባችንን ለነፃነቱ፣ ለመብቱ ለትግል መነቃቃት፣ የወያኔና መዝረክረክና በእቅድ ሳየሆን በግምት መዳከርን ከግምት በማስገባት ልዩነታችንን አቻችለን በአንድነት በኢትዮጲያዊ ጥላ ስር ተከልለን ለለውጥ እንነሳ፡፡ ከፍርሃት ድባብ ወጥተን በውስጥም በውጪም ካሉት ጠንካራ ድርጅቶች ጎን በምቆም የሃገራችንን ህልውና የህዝባችንን ነፃንት እናስመልስ፡፡   

ኢትዮጲያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
አሰተያየተ ካለዎት
adugenet2000@gmail.com

onsdag 28. august 2013

የወያኔ መንግስት የግንቦት 7 ቡድን አባላት ናቸው ብሎ የጠረጠራቸው ላይ ክስ መሰረተ

የግንቦት 7 አሸባሪ ቡድን አባላት ናቸው በሚል የተጠረጠሩ 10 ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው ።
ተከሳሾቹ ዘመኑ ካሳ በዕውቄ የግንቦት ሰባት ልዩ ሃይል ታጣቂ ፣ አሸናፊ አካሉ አበራ ፣ ደህናሁን ቤዛ ስመኝ ፣ ምንዳዬ ለማ ፣ አንሙት የኔዋስ አለኽኝ ፣ሳለኝ አሰፋ ወንድምአገኝ ፣ የአማራ ክልል የማረሚያ ቤት ረዳት ሽፍት መሪ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሉዬ ማናዬ ረታ፣ፀጋው ካሳ እንየው ፣ የአለም አካሉ አበራ እና ሙሉ ሲሳይ መቆያ የተባሉ ተጠርጣሪዎች  ናቸው ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት  ከፈረጀውና እራሱን ግንቦት ሰባት እያለ ከሚጠራው ድርጅት አመራሮች ጋር በመገናኘት ለሽብር ስር በጋራ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ነው  የፌዴራሉ አቃቤ ህግ ክስ የመሰረተባቸው ።
የፌዴራሉ አቃቤ ህግ መረጃዎችን ሰብስቦ ነሃሴ 13 ክስ መስርቶባቸው ትላንት በአቃቂ ጊዜያዊ 4ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን፤ተከሳሾቹ ጠበቃ የማቆም አቅም ስለሌላቸው የመንግስት ጠበቃ እንዲቆምላቸው ችሎቱ አዟል።
ችሎቱ  1ኛ ተከሳሽ በሌለበት ክሱ በመቅረቡ በጋዜጣ እንዲጠራ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ክሱን ለመስማትም  ችሎቱ ለህዳር 2 ቀን  2006 ዓመተ ምህረት ቀጠሮ ይዟል ።

4 ለ 3 በጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ ላይ የተደረገ ክርክር

አንድነት ፓርቲ የጸረ ሽብርተኝነት አዋጁን በህዝብ ድጋፍና ጥያቄ ለማሰረዝ የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ የሚፈለገውን ግብ ለመምታቱ በገዢው ፓርቲ ቁጥጥር ስር የሚገኘው ኢቴቪ በአዋጁ ዙሪያ የፓርቲዎችን አቋም የሚያንጸባርቅ መድረክ ማዘጋጀቱ ማሳያ ነው፡፡ኢህአዴግ ካድሬዎቹ አዋጁን በማንበብ አንድነቶች ለሚያነሱት መከራከሪያ ምላሽ ለመስጠት እንዲችሉ ትዕዛዝ ማውረዱም ሌላኛው የአደባባይ ድል ነው፡፡

በነቢብ የህዝብ በገቢር የኢህአዴግ ልሳን የሆነው ኢቴቪ በአዋጁ ላይ ያላቸውን አቋም እንዲያንጸባርቁ የጋበዛቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ በአቶ በቀለ ነጋዓ፣አንድነት በሃብታሙ አያሌው፣ኢዴፓ በሙሼ ሰሙ፣ሰማያዊ በይልቃል ጌትነት፣ ኢህአዴግ በሽመልስ ከማል፣በጌታቸው ረዳና በኢቴቪው ጋዜጠኛ ተወክለዋል፡፡

ክርክሩ በተራ መቀስ የተቆራረጠ መሆኑ

ኢህአዴግ ከምርጫ 1997 በኋላ በቀጥታ የቴሌቪዥን መስኮት የሚተላለፉ ክርክሮች ፎብያ የተጠናወተው በመሆኑ live debate አይመቸውም፡፡እናም ክርክሩ በቀጥታ አለመተላለፉ ለባለ መቀሶቹ ጥቅሙ ከፍ ያለ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ነው፡፡በሁለት ክፍል የተላለፈው ክርክር በተራ መቀስ መቆረጡን ለመመስከር ሶስተኛ አይን የማያስፈልግበትን አንድ ሁለት ነጥብ ልጥቀስ፡፡ከመሬት ተነስተው የኢህአዴጉ ተወካይ ተቃዋሚዎችን‹‹እንዴት ድራማ ነው ትላላችሁ››በማለት ይወርፏቸው ጀመር፡፡ክርክሩን ስራዬ ብሎ የተከታተለ ሰው እኚህ ሰው ለምን ያልተጻፈ ያነባሉ ብሎ ሊፈላሰፍ ይችላል፡፡ነገሩ ግን መዛባቱን የፈጠረው የሽመልስ ንግግር ሳይሆን ኢቴቪ ነው፡፡ ማለቴ መቀሱ፡፡

ጌታቸው ከዚህ በፊት አብሮኝ በአንድ መድረክ ሰርቷል ያሉትንና አሁን የአሰላለፍ ለውጥ በማድረጉ አንድነትን የተቀላቀለውን ሃብታሙን በነገር ወጋ ሲያደርጉት ታዝቢያለሁ፣ሃብታሙ በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ የሚለው ነገር እንደሚኖር መጠርጠሬ አልቀረምና ተራው ደርሶ የሚለውን ለማድመጥ ጆሮዬን ቀሰርኩ ነገር ግን የሃብታሙ ንግግር ከመሃል እንደጀመረ በሚያሳብቅ መልኩ ለጌቾ ይሰጠዋል ብዬ የጠበቅኩት ምላሽ ሳይቀርብ ቀረ፡፡ሴኮ ቱሬ ክርክሮችን በመቆራረጥ ጥበብ የተካኑ እንደነበሩ በአንድ ወቅት የድሮው ልደቱ (አዲስ ልደቱ እንዳሉ ስለማምን የቀድሞው ለማለት ተገድጃለሁ)ተናግረው እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ሴኮ አሁን ስለሌሉ የኢቴቪ አዲሱ መቀስ ብዙም በቆረጣ ባለመካኑ ቆረጣው አይን ያወጣ ሆኖበታልና አልተሳካም፡፡

ያልተጠየቀ ‹‹መመለስ›› የጆሮ ህመም ይሆን?

ተቃዋሚዎች በአንድነት በሚባል መልኩ አዋጁ ከህገ መንግስቱ እንደሚጋጭ በመግለጽ ጭብጥ ለማስያዝ ሞክረዋል፡፡ሽመልስ እሳት ለብሰውና ከአንድ የህግ ባለሞያ በማይጠበቅ መልኩ እየደጋገሙ‹‹እንትን››እያሉ በሰጡት መልስ ‹‹ተቃዋሚዎች የእኛ አዋጅ የአሜሪካንን ወይም የአውሮፓን ስለማይመስል ህግ ለመሰኘት ብቁ አይደለም ይላሉ››ብለዋል፡፡አዋጁ የሰብዓዊ መብትን ይጋፋል ሲባሉም አራምባ በመርገጥ ‹‹ ለሽብርተኞች በሩን በመዝጋቱ የእኛ ህግ ከሁሉም የተሻለ ነው››ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ያልሰማ ጆሮ የሚሰጠውን መልስ ለማወቅ የሽመልስንና የጌታቸውን ንግግሮች ማድመጥ አቻ የሚገኝለት አይመስለኝም፡፡ለነገሩ በዋናነት የኢህአዴግ ዋነኛ ችግር ምላስ እንጂ ጆሮ የሌለው መሆኑ አይደል፡፡ተቃዋሚዎቹ አዋጁን በተመለከተ ለሚያነሷቸው ውሃ የሚያነሱ መከራከሪያዎች ኢህአዴጋዊያኑ ከተነሳው ሃሳብ ጋር ተያያዥነት የሌለውን ምላሽ መስጠታቸው ሟቹን መለስን በብዙ ነገር እንዳስታውስ አድርጎኝ ነገሩ የወል ችግራቸው መሆኑን ደመደምኩ፡፡

በዚህ አይነት በፖለቲካ ውሳኔ እንዳንረሸን ሰጋሁ

ሽብርተኞችን የመፈረጅ ስልጣን ፓርላማው አልተሰጠውም የሚለው መከራከሪያ በአቶ ሽመልስ አስደንጋጭ መልስ ተሰጥቶታል፡፡ፓርላማው ህግ የማውጣት እንጂ ህግ የመተርጎም ስልጣን የፍርድ ቤቶች በመሆኑ የፍርድ ቤቶችን ስራ ለፍርድ ቤቶች መስጠት ሲገባው ያወጣውን ህግ ለመተርጎም መሄዱ ህገ መንግስታዊ ጥሰት ነው ሲባል ሽመልስ ‹‹ይህ የፖለቲካ ውሳኔ ነው››ብለው አረፉት፡፡በእኛ አገር የፖለቲካ ፣የውድብ፣የቡድን ውሳኔ ምን እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡በፓርላማው ካሉት 547 መቀመጫዎች ኢህአዴግ 545 በመውሰድ ቤቱን ተቆጣጥሯል፡፡በዚህ የአንድ ፓርቲ ጉባዔ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተላለፈ ማለት ምን አይነት ትርጉም እንደሚኖረው ለታዛቢ እንተወው፡፡ደግሞስ የማስረጃ፣የምስክርናየህግ ድንጋጌን የሚፈልግ ትልቅ ጉዳይ እንዴት ፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲይዝ ይደረጋል?ከዚህ በላይ ፍትህን መስቀል ከወዴት ይገኛል?

አወያይ ጋዜጠኛ ወይስ ኳስ አቀባይ?

የኢቴቪው ጋዜጠኛ ስሙን ከኢህአዴግ ተወካዮች ተራ አለማስመዝገቡ ብስጭቴን እንዳናረው መሸሸግ አይኖርብኝም፡፡ከመነሻው ‹‹ኢትዮጵያን የሽብር ስጋት ያሰጋታል ወይስ አያሰጋትም››የሚል ጥያቄ አንስቶ በአገሪቱ የደረሱ ጥቃቶችን በፊልም ማሳየት ምን ሊባል ይችላል?ይህንን ፊልም የሚመለከቱ ሰዎች ከመነሻው የጥያቄው መነሳት አስፈላጊነት ላይታያቸው እንደሚችል መገመት ባይከብድም አወያዮ ፊልሙን ጋብዟል፡፡

ፓርላማው ድርጅቶችን መፈረጁን በተመለከተ ፓርቲዎቹ ሲወያዮ የጋዜጠኛ ማልያ ያጠለቀው አወያይ ጣልቃ ገብቶ ‹‹የኢትዮጵያን ህዝብ ለማስታወስ ያህል ፓርላማው የፈረጀው አልቃይዳ፣አልሻባብ፣ኦነግ፣ኦብነግንና ግንቦት ሰባትን ነው››ብሏል፡፡እንኳን ይህችን ያለ ሰፈሯ የመጣችን ዝንብ ለምናውቅ ሰዎች የጋዜጠኛው ማስታወሻ ግልጽ ናት‹‹ተቃዋሚዎች የሚከራከሩት ለአልቃይዳ ነው››ለማለት ነው፡፡ክርክሩ ግን ፓርላማው ከስልጣኑ ውጪ እየተጓዘ በመሆኑ ነገ ሌሎች ሰላማዊ ፓርቲዎችን ሽብርተኛ በማለት ሊፈርጅ ይችላል የሚል ነበር፡፡አወያዮ ልክ የኢህአዴግ ተወካዮች አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡ ሲሰማውና የማርያም መንገድ ሲያጡ ዘው ብሎ በመግባት መውጫ መንገድ ያመቻቻል፡፡ኳሷ በተቃዋሚዎች እጅ በኢህአዴግ ሜዳ እየተንከባለለች ወደ ጎል ስትደርስ ጋዜጠኛው ፊሽካ ነፍቶ ኳሷ እንድትመለስ ያደርጋል፡፡

በእስካሁኑ ክርክር ለበቀለና ለሃብታሙ ኮፊያዬን አወልቃለሁ    

ክርክሩ ነገ ምሽት እንደሚለጥቅ ኢቴቪ ቃል ገብቷል፡፡የመጨረሻው ክርክር ቀርቦ ፋይሉ ከመዘጋቱ በፊት በግሌ ባደረግኩት ዳሰሳ የመጀመሪያው ምሽት የክርክር ኮከብ አቶ በቀለ ነግዓ የሁለተኛው ምሽት ፈርጥ ደግሞ ሃብታሙ አያሌው ነበር፡፡ሙሼ ረጋ ብሎ የሚያነሳቸው ነጥቦች ቦታ ሊሰጣቸው የሚገባቸው እንደሆኑ ይሰማኛል፡፡

በቀለ ዘና እና ረጋ ብለው የሚወረውሯቸው ቃላቶች ድንጋይ ሆነው  በኢህአዴግ ላይ የሚያርፉ ቢሆኑ አቶ በረከት ስምኦን በሁለት ምርጫዎች ወግ እንደጠቀሰው ናዳ ሆነው ኢህአዴግን ከመንበሩ ባፈናቀሉት ነበር፡፡ ሃብታሙ ታሊባንን እንደ አገር በመውሰድና የጸረ ሽብርተኝነትን የምንቃወመው››በማለት ከመናገሩ ውጪ ነጥብ በነጥብ ያነሳቸው ሃሳቦች የሚጣል ነገር አልነበራቸውም፡፡ እንግዲህ ደግሞ ለነገው የነገ ሰው ይበለን፡፡

tirsdag 27. august 2013

ኢህዴግ ነሐሴ 26 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አደረገ


ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጽያ ሃይማኖቶች ተቋማት ጉባዔ ዛሬ ከቀትር በሁዋላ በአ/አ አምባሳደር ቲያትር አካባቢ በሚገኘው ጽ/ቤቱ
ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አክራሪነትን ለመቃወም የፊታችን እሁድ ነሃሴ 26 ቀን በመስቀል አደባባይ ሰልፍ
መጥራቱን አስታወቀ፡፡

በሰልፉ በርካታ ሰው እንዲገኝ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ለመንግስት ሰራተኞች፣ ለፓርቲ አባላት፣ ለሴቶች ሊግ፣ ለወጣቶች ሊግ እንዲሁም በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራት አባሎችና በኮብል ስቶን የሰለጠኑ ወጣቶች የግዳጅ መመሪያ ተላልፏል፡፡

ጥሪ የደረሰቸው ሁሉ በሰልፉ ላይ ለመገኘት ቀደም ብለው በፊርማቸው ያረጋግጣሉ።

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጽያ ሃይማኖቶች ተቋማት ጉባዔ ዛሬ 
ከዚህም በለይ በሰልፉ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትም እንዲሳተፉ መንግስት ጫና በማድረግ ላይ እንደሆነ በቤተ ከህነትና ባኢስልምና ገዸዮች ያሉ ምንጮች ጠቁመዋል።በዕለቱ ሰማያዊ ፓርቲ ሁለተኛ ሰልፉን በመስቀል አደባባይ ለማድረግ በይፋ ለአስተዳደሩ አሳውቆ ምላሽ እየተጠባበቀ የሚገኝ ሲሆን ምናልባት የሃይማኖት ተቋማቱ ሰልፍ ለማካሄድ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ የሰማያዊ ሰልፍ በዕለቱ ላይፈቀድ ይችላል የሚል ግምት አሳድሮአል፡፡

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኃይማኖቶች ተቋማት ጉባዔ ጋር በመተባበር “ኃይማኖቶች አብሮ የመኖር እሴት በማጎልበትና ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌዎችን በማክበር የሀገራችንን ሕዳሴ ጉዞ ለማሳካት እንረባረባለን” በሚል መሪ

ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ ከነገ ነሐሴ 21–23/2005 ዓ/ም የሚቆይ ጉባዔ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ያካሂዳል፡፡ ይህ ጉባዔ ከተዘጋ በኃላ በተለይ የሕዝበ ሙስሊሙን የመብት ጥያቄ ከአክራሪነት ጋር አስተሳስሮ የሚያወግዝ ሰልፍ ነሐሴ 26 ይካሄዳል፡፡


ከሃይማኖት ተቋማት በተጨማሪ የተለያዩ የግል ድርጅቶች በተለይም የጅምናስቲክ፣ የማርሻል አርትና የቴኳንዶ ስልጠና የሚሰጡ ድርጅቶች ሰልጣኞች ተማሪዎቻቸውን በሰልፉ ይዘው እንዲገኙ በየወረዳው አስተዳዳሪዎች ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል፡፡

ከየክፍለ ከተማው አስከ አስር ሺ ሰው እንዲሳተፍበት በተላለፈው መመሪያ መሰረት የወረዳ ቢሮዎች ኮታውን ለመሙላት ይሄን ሳምንት ሙሉ ጊዜያቸውን ለዚሁ ስራ በመስጠት ከፍተኛ የቅስቀሳ እና የግደጅ ስራ ለመስራት ተዘጋጅተዋል፡፡

መንግስት በክልል ከተሞች ሲያካሄደው እንደነበረው ሁሉ ለዚህ ሰልፍም ከፍተኛ ባጀት መመደቡ ታውቋል።

mandag 26. august 2013

ሳያጡ እየተራቡ ያሉ ዜጎች ጩኸትና የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን

በወገን በለጠ
ይህችን የተራቡና የዕለት ጉርስ ሳያጡ እንዲራቡ የተፈረደባቸውን የዋና ከተማችን ዋና ከተመኞች የተማፅኖ ደብዳቤ በጋዜጣችሁ ላይ አስፍራችሁ የጌቶቻችንን ቢሮ፣ በርና ልቦና እንድታንኳኩልን ብሎም ርህራሔያቸውን እንዲያሳዩንና እንዲታደጉን ታደርጉልን ዘንድ የእናንተንም አዘኔታና እገዛ እንማፀናለን፡፡
የተማፅኖ ደብዳቤያችን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የዘቀጠና የማን አለብኝነት ሕገወጥ ተግባር ዙሪያ የምታጠነጥን ብትሆንም፣ እንደሌላው ጊዜ ሁሉ መብራት ጠፍቶብን የአርሴና የማንቼ ጨዋታ አመለጠን ወይም የሞስኮ የአትሌቲክስ ውድድር ሳናየው አለፈ፣ የእሑድ መዝናኛ ፕሮግራምን ማየት አልቻልንም ወዘተ ሳይሆን፣ መልካም አስተዳደር ሰፍኗል፣ የተዘረጋው የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ከሚጠበቀው በላይ ውጤት አምጥቷል፣ ሙስናን አከርካሪውን ለመምታት እየሠራን ነው፣ በዚህም የሕዝብ ጥያቄ ምላሽ እያገኘ ነው እየተባለ በሚደሰኩርበት አገርና ከተማ በመልካም አስተዳደር ዕጦት በገዘፈና ይፋ በሆነ የሙስና አሠራር በማን አለብኝነትና በጥቅም በታወረ አመራር ምክንያት፣ በመቶዎችና በሺሕዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ጦማቸውን እንዲያድሩ እየተፈረደባቸው ስለሆነ ይህንን መልዕክታችንን አስፍሩልን፡፡
ምንም ቢቸግረው ጅብ አይበላም አፈር፣
ደሞዝ ተቀብሎ ደጃች ውቤ ሠፈር፤
እና ሌሎችም በርካታ ግጥሞች የተገጠሙላት ደጃች ውቤ ሠፈር በፊት ገጽታዋ ዛሬም እንደ ጥንቱ ቢራዋን ገችራ ውስኪዋን ደርድራ ዘመነኞችን እያስተናገደች ቢሆንም፣ በጀርባዋ ግን በዘመን ጉዞ ዕርጅና ተጭኗት በመሠረተ ልማት ግንባታ ዕጦት ተደቁሳ፣ በመልካም አስተዳደር ዕጦት እያነባች ድሆቿን በውስጧ ታቅፋ ዛሬም አለች ፡፡
ከአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ከሚገኘው የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ/ባለሥልጣን ፊት ለፊት ተነስቶ እስከ አዲሱ የአፍንጮ በር ድልድይ ባለው አውራ መንገድ ግራና ቀኝ የተደረደሩትን ግሮሰሪዎችና ቡና ቤቶች፣ እንዲሁም ጥቂት ሥጋ ቤቶችን ጨምሮ ከጀርባ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የሚኖሩባቸው መንደሮች መጠሪያ ጥንትም ሆነ ዛሬ ደጃች ውቤ ሠፈር ነው፡፡
በእነዚህ መንደሮች በመቶዎች የሚቆጠሩ ለመንግሥት ተቀጥረው በደመወዝ የሚተዳደሩና በየወሩ ከሚያገኙት ደመወዝ ላይ ከአንድ አራተኛ የማያንስ ገቢያቸውን ሕጋዊና ዜግነታዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ግብር በትክክል የሚከፍሉ፣ ለአገራዊ የልማት አጀንዳዎች ማስፈጸሚያዎች ከዕለት ጉርሳቸው ቀንሰው ድርሻቸውን የሚወጡና የተወጡ ወገኖች፣ እንዲሁም ፀሐይ ወጥታ እስክትጠልቅ የዕለት እንጀራቸውን ለማግኘት ሲባዝኑ የሚውሉ ምስኪን ዜጎች ይኖራሉ፡፡
በዋናው መንገድ ፊት ለፊት በተደረደሩት መሸታ ቤቶች ቀንም ማታም ይጠጣል፣ ይበላል፣ ይዘፈናል፣ ይጨፈራል፡፡ የእግረኛ መተላለፊያ መንገዶች በቆርቆሮ፣ በብረትና በሸራ ታጥረው መሸታ ይመሸትባቸዋል፣ ዳንኪራ ይረገጥባቸዋል፡፡
የቀዘቀዘ ቢራ እንዳይታጣ፣ የውስኪ መጠጫ በረዶ እንዳይጠፋ፣ የሙዚቃው ቃና እንዳይደበዝዝ ኤሌክትሪክ እንዳይቋረጥ አንዳንድ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ነቅተውና ተግተው ይሠራሉ፡፡ ድንገት በአጋጣሚ ቢጠፋም ከአንዱ ባለግሮሰሪ ባለቤት በግል ስልካቸው ላይ ተደውሎ ይነገራቸዋል፡፡ በአስቸኳይና በሽሚያ መጥተው ይሠራሉ፡፡ በሚቀርብላቸው እጅ መንሻ ቢራና ውስኪ ተንበሽብሸው በቀጣይም ተመሳሳይ ችግር ቢያጋጥም ‹‹እጃችሁ ላይ ነን፤›› ብለው ይሸኛሉ፡፡ ምን ችግር አለ?
የደጃች ውቤ ሠፈር የፊት ለፊት ገጽታና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ፈጣንና የተቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጥ ይህን ሲመስል፣ ከጀርባ ያሉት ነዋሪዎች ግን ለቀናት ብሎም ለሳምንታት በየተራ በኤሌክትሪክ ዕጦት ይሰቃያሉ፡፡
ይህ ችግር ከጊዜ ጊዜ ይሻሻላል በሚል ተስፋና ከኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ክፍል በማያልቅና በየጊዜው እየተቀያየረ የሚሰጥ መግለጫን በማመን፣ በእርግጥም በኃይል አቅርቦት ዕጥረት ወይም በመስመሮች አሮጌ መሆንና ኃይልን የመሸከም አቅም ብቃት ማነስ ይሆናል በማለት ስንሸነገል ብንኖርም፣ ይህ አለመሆኑን በግልጽ ስለተረዳንና ከሠራተኞቻቸውም ስለተነገረን ችግሩም ከዕለት ዕለት ከወር ወር እየባሰና እየጨመረ በመምጣቱ፣ ጌቶቻችን ብሶታችንን ቢሰሙ ብለን ይህንን አቤቱታ አቅርበናል፡፡
እነሆ ጎን ለጎን ባሉና ፊትና ኋላ በሚገኙ ቤቶች መካካል ልዩነት በማድረግና የኤሌክትሪክ ኃይል በማጥፋት እንዲሠራላችሁ ከፈለጋችሁ ገንዘብ አዋጥታችሁ ስጡንና እንሠራላችኋለን ማለት ከተደረሰ፣ የሕዝብ ንቀትና ማናለብኝነት በድሆች ላይ በደል እየተፈጸመ ነው፡፡
በዚህ በያዝነው ወር ብቻ በተደጋጋሚ ለቀናትና ለሳምንት ለዘለቀ ጊዜ መብራት በማጥፋታቸው እንዲሠሩልን በተደጋጋሚ የተለያዩ የሰሜን አዲስ አበባ የኮርፖሬሽኑ መሥሪያ ቤቶች በመገኘት (ራስ ደስታ አካባቢ፣ ሰሜን ማዘጋጃ ቤት በታች፣ ቸርችል ጎዳና፣ አንበሳ ፋርማሲ ፊት ለፊት) በሚገኙ ቢሮዎች ብናመለክትም ሆነ ብንጮህ ሰሚ አጥተን በጨለማ ተውጠን እንገኛለን፡፡
ጌቶቻችን ሆይ !
ረሃብ ቀን ይሰጣል? የዘንድሮስ ኢኮኖሚ ደሃን ዳቦውን ያስጥላል? እናንተ ግን እየተራብን የእናንተን ርህራሔና መልካም ፈቃድ የሚገኝበት ቀንን እንድንጠብቅ፣ ሰላሳ ቀናት ለፍተንና ባዝነን ባገኘናት ጥቂት ገንዘብ የሸመትናትን እህል እንበላለን ብለን አቡክተን መጋገሪያ አጥተን ተበላሽቶ እንዲደፋ፣ ሊትሩን በአሥራዎችና በሃያዎች በሚቆጠር ብር ገዝተን ሕፃናት ልጆቻችን እንመግባለን ብለን ያስቀመጥነውን ወተት ማፍላትና መስጠት አቅቶን እንዲደፋ፣ ወይም ጥሬውን ጠጥተው ለበሽታ እንዲዳረጉ እያደረጋችሁ ነው፡፡ ዕድሜ ለእናንተ ሳይተርፈን እየደፋን ነው፡፡
አዛውንቶች በዚያ ጎርበጥባጣና በፈራረሰ መንገድ እየመረጡ እንዳይራመዱ እንኳን በጨለማ እንድንዋጥ አድርጋችሁ ቁጥራቸው ከሦስት ያላነሱ አዛውንቶች ወድቀው እንዲሰበሩ ምክንያት ሆናችኋልና በመልካም ተግባራችሁ ተደሰቱ፡፡ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡
የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ረሃብ ቀን አይሰጥምና በእንጨት በከሰል ወይም በጋዝ ለመጠቀም አቅማችን አልፈቀደምና እባካችሁ ተለመኑን፡፡
በእርግጥ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር አጋጥሞናል የምትሉም ከሆነ ውስኪው ሠፈር ብቅ ስትሉ የኛንም ችግር እንድትፈቱልን ስንጠይቃችሁ ብልሽቱ የት ቦታ ነው? አሳዩን እያላችሁ አትመፀደቁብን፡፡ እናንተ እንጂ እኛ የኤሌክትሪክ ባለሙያዎች አይደለንምና፡፡ ቢያንስ የቢራና የውስኪ ግብዣ ለመታደም በመንግሥት መኪና ስትመላለሱና በግብር ስም ከእኛ የተሰበሰበውን ገንዘብ በትርፍ ሰዓት ስም ሳትሠሩ ሲከፈላችሁ ኃፍረት ይሰማችሁ፡፡
አለበለዚያም መልካም ፈቃዳችሁ ሆኖልን ኤሌክትሪክ የምታጠፉበትንና የምታበሩበትን ቀን በቅድሚያ ንገሩንና ቁርጣችንን አውቀን በፕሮግራም እንራብ፡፡ ያቦካነው ሊጥና የጣድነውን ሽሮ እየራበን ሳይተርፈን እንድንደፋ አታስገድዱን፡፡
ትልልቆቹ ጌቶቻችን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፣ አቶ ዓለማየሁ ተገኑና አቶ ምህረት ደበበ መብራት ጠፍቶባችሁ እንደማያውቅ አንድ ሺሕ ጊዜ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ጉዳቱንም አታውቁትም፡፡ ረሃብንም የምታውቁ አይመስለኝም (እንደሌሎቹ ከበረሃ አልመጣችሁምና)፡፡ እግዚአብሔርን እንደምታውቁ ግን አውቃለሁና ስለአግዚአብሔር ብላችሁ ምን እየተሠራ ነው ብላችሁ ጠይቁ፡፡ ሕዝባችሁንም በእኩል ዓይን አስተዳድሩ፡፡ የደሃ ጩኸት ይሰማችሁ፡፡
የመለስ መልካም አስተዳደር፣ ደሃ ተኮር ልማትና ዕድገት የተቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጥ፣ ከሙስና የፀዳና ሙስናን የማይሸከም ኅብረተሰብ የመፍጠር ራዕይ የሚሳካው በመዝሙርና በመፈክር ሳይሆን፣ የዜጎችን ቁልፍ ችግሮች በመፍታት ጭምር መሆኑን ተገንዝባችሁ እባካችሁ ጓዳችሁን ፈትሹና መፍትሔ ስጡ፡፡ በተለይ አቶ ምህረት የቅርብ ኃላፊ ነዎትና ዝቅ ብለው አሠራሮችን ይፈትሹ ያስፈትሹ፡፡ ለመሆኑ የኤሌክትሪክ አደጋ ደርሶ እንኳን ጥሪ ለማድረግ ለኮፖሬሽኑ ብንደውል ለአደጋ ማሳወቂያ የተመደቡት ስልኮች የማይነሱና ምላሽ የማይሰጥ መሆኑን ያውቃሉ? እስኪ የሰሜን ቅርንጫፍ ቢሮዎችን ስልክ ይሞክሩ፡፡ ወይም ጊዜ ከሌለዎት ሌሎች ባልደረቦችዎ ሞክረው ውጤቱን ይንገርዎት፡፡ የቴሌ ችግር እንዳይባል ስልኩ ይሠራል፡፡
የሰሜን አዲስ አበባ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች እስቲ በግንባር ቀርበን ያስመዘገብነውን ተመልከቱ፡፡ መቼ ነው? ችግሩ ምንድን ነው? ለምን አልተሠራም? ብላችሁ ጠይቁ፡፡ የሕዝብን አደራ ተወጡ፣ የወገን ችግር ይግባችሁ፡፡
በተረፈ ይህንን ጻፉ ብላችሁ በእኔም ሆነ በጎረቤቶቼ ላይ ተጨማሪ የረሃብ ቅጣት እንደማትጥሉብን ተስፋ እያደረግኩና ቢደረግም ትልልቆቹ ጌቶቻችን እንደሚታደጉን ተስፋ እያደረግሁ በዚሁ ላብቃ፡፡
የራበው ሰው እንኳን ብዙ አያወራም ችግሩ ቢፀናብን ነውና ይቀርታችሁ አይለየን፡፡ ይልቁንስ ሳምንት አካባቢ የጠፋውን መብራት አብሩልንና እንጀራችንን ጋግረን ሽሯችንን አሙቀን እንብላ፡፡ ወዳጆቻችሁና ጓደኞቻችሁም የኛን ማላዘን ሳይሰሙ ያላበው ቢራ ይጠጡ፤ ውስኪ በበረዶ ያንቆርቁሩ፡፡ አንዳንዶቹ ሠራተኛዎቻችሁም የእኛን ሳንቲም መቀላወጥ ትተው የቢራና ውስኪ ቅልውጡ ላይ ይበርቱ፡፡ ‹‹ዘለለ ዕለትነ›› ብለን የዕለት ጉርሳችንን እንዳይነሳን ፈጣሪን እየለመንን የምንኖር እንጂ፣ ለእናንተ እጅ መንሻ ለመስጠት አቅም ያለን አይደለንምና፡፡
እኛ እንራብ፤
ለእናንተ ሰላም ይሁን፡፡

onsdag 21. august 2013

ዋስትናችን እርቅ ብቻ ነው!

“እኛ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና ዋ!!'' ኦባንግ

እሳት ሲነሳ የመጀመሪያው ተግባር እሳቱን በፍጥነት ማጥፋት ለሚችለው የእሳት አደጋ ብርጌድ መደወል ሲሆን፣ ቀጣዩ ተግባር እሳቱ በተነሳበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ነፍስ አትርፈው እሳቱን በተገኘው መንገድ ለማጥፋት መረባረብ ነው። ይህ የተለመደው ተግባር ዛሬ በኢትዮጵያ ስለመስራቱ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክትር ስጋት አላቸው። እናም “እኛ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና ዋ!!” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ጥሪ ያሰማሉ።

“አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እሳቱ ፊትና መልክ ይዞ ሲቀጣጠል አላነውም እንጂ በርካታ የማቀጣጠያ ቅመሞች ተዘጋጅተውለት ለመንደድ በዝግጅት ላይ ነው። መንደዱ የማይቀረው ይህ እሳት ቢነሳ የሚያጠፋው የለም” የሚሉት አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ ጥላቻው በሰፈር ደረጃ ከርሯል ይላሉ። በየመንደሩ ህዝብ እንዲቧደን ተደርጓል። ሚና ለይቷል። አገር የሚመራው መንግሥትም ችግሩን ከመፍታትና አገሪቱን ከስጋት ከማላቀቅ “ጥሪ አይቀበልም” በሚል የሃይል ርምጃ መምረጡ ነገሮችን ይበልጥ እንዳወሳሰበ ይናገራሉ።

በየአቅጣጫው ያሉ ወገኖች ቆም ብለው ሊደበቁት ከማይችሉት ከህሊናቸው ጋር ሊነጋገሩ እንደሚገባ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ግብጾች ግብጾችን ገደሉ፣ ገና ቀውሱ ይቀጥላል። ይህ እጅግ ዘግናኝ የሆነው ቀውስ እኛ ዘንድ ሳይደርስ ወደ እርቅ እናምራ። ለእውነተኛ እርቅ ጊዜው አሁን ነው” በማለት አንገብጋቢ ያሉትን ጥሪ ያስተላልፋሉ።

“ላለፉት 22 ዓመታት ኢትዮጵያ ላይ ከየአቅጣጫው የተረጨው መርዛማ ፖለቲካና፣ ሰብአዊነት የጎደለው አስተዳደራዊ መዋቅር የፈጠረው ውጥረት ወደ መፈረካከስ እየነዳን ነው” በማለት የስጋቱን መጠን የሚጠቁሙት አቶ ኦባንግ ፣ በግብጽ የተፈጠረው ቀውስ በሃይል ሊቆም የማይችልበት ደረጃ ሲደርስ ምዕራባዊያንም ሆኑ አሜሪካ የሃዘን መግለጫ ከማውጣት የዘለለ ስራ አለመስራታቸው ለኢትዮጵያዊያን ታላቅ ትምህርት ሊሆን እንደሚገባ ያሰምሩበታል።

በሩዋንዳ ለቁጥር የሚያዳግቱ ሰዎች አልቀዋል። በኮሶቮ ህዝብ ተጨፍጭፏል። ዳርፉር ንጹሃን የጥይት ራት ሆነዋል። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሃያላን መንግስታትና “ድርጅቶቻቸው” በእነዚህ አገራት ውስጥ ነበሩ። እያወቁት ነው የሆነው። ግን ጉዳዩ የጥቅም ችግር ስለማይፈጥርባቸው አገራቱ በደም ጎርፍ ሲታጠቡ በዝምታ ተመልክተው እንደነበር ያስታወሱት አቶ ኦባንግ፣ “ሶሪያ ስትፈርስ፣ ከ100 ሺህ ሰው በላይ ሲያልቅና አሁንም እያለቀ ባለበት ሁኔታ እልቂቱን ማስቆም እየቻሉ ዝምታን መርጠዋል” በማለት አቶ ኦባንግ ከነዚህ አገሮች፣ በተለይም “አሁን ግብጽ ላይ በተፈጠረው ችግር ካልደነገጥንና ለሚቀርበው የእርቅ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የማንዘጋጅ ከሆነ አደጋው የከፋ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ጥያቄው የስልጣን ሳይሆን አገሪቱ ላይ ያንዣበበውን የሞት አደጋ የመግፈፍ አንደሆነ፣ ይህ አሁን ያንዣበበው የቀውስ ደመና ባስቸኳይ ካልተገፈፈ መከራው የሁሉም ወገን እንደሚሆን ጥርጥር እንደማያሻው የጠቆሙት አቶ ኦባንግ “ንጹህ ልብናና ንጹህ ህሊና ያላችሁ ውጡ፣ ለእውነተኛ እርቅ እንስራ፣ አገሪቱንም እናድን፣ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና እኛው አገራችንን በማስቀደም እንታደጋት” ሲሉ ከወትሮው በተለየ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በምርጫ ፕሬዚዳንት ሆነው በዓመጽ መፈንቅለ መንግሥት የተደረገባቸው ፕሬዚዳንት ሙርሲን የሚደግፉ የሙስሊም egyptወንድማማች ፓርቲ ደጋፊዎች ላይ የሃይል ርምጃ ከመወሰዱ በፊት በግብጽ ይህ ችግር ሊደርስ እንደሚችል የወተወቱ ነበሩ። ፕሬዚዳንት ሙርሲ ከስልጣን የተወገዱበት አግባብ ቀውስ ሊያስነሳ እንደሚችል ቢነገርም ሰሚ ባለማግኘቱ ቀውሱ ግብጻዊያንን እርስ በርስ አጋደለ። ግብጾች ግብጾችን ጨፈጨፉ። እስከ ሁለት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች የተገደሉበት ይህ ቀውስ እንዴት ሊቆም እንደሚችል ፍንጭ የለም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ የሰዓት እላፊ፣ ግድያና እስር ዓመጹን ሊገታው አልቻለም። ይልቁኑም መሳሪያ የታጠቁ ተቃዋሚዎች ግብጽን በጥይት እያመሷት ነው። እየገደሉም ነው።

søndag 18. august 2013

ሁሉም የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ ኣይደለም (አብርሃ ደስታ – ከትግራይ)

የትግራይ ህዝብና ህወሓት! (በአብርሃ ደስታ – ከትግራይ)

abraha desta
እውነት ነው። የህወሓት መሪዎች የትጥቅ ትግሉ ጀመሩት። ደርግ ዓማፅያኑ ለማጥፋትና ትግራይን ለመቆጣጠር የሃይል እርምጃ መውሰድ ጀመረ። ትግራይ የጦርነት ኣውድማ ሆነች። የትግራይ ገበሬዎች በሰላም የእርሻ ስራቸው ማከናወን ኣቃታቸው። የደርግ ወታደሮች ገበሬዎቹን ማስፈራራት፣ ሴቶችን መድፈር፣ ወጣቶችን በግደል (በጥርጣሬ) ተያያዙት።

በደርግ ኣሰራር የተማረረው የትግራይ ገበሬ ጫካ ገባ። እዛው ጫካ ከህወሓቶች ጋር ተቀላቀለ። ኣብዛኛው ታጋይ (ገበሬ ወይ ኣርሶ ኣደር) ደርግን ለመታገል ጠመንጃ ያነሳው በደርግ ስርዓት በነበረ ጥሩ ያልሆነ የሰለማዊ ሰዎች ኣያያዝ እንጂ እንደሚነገረን እንዳልሆነ እንዲታወቅልኝ። በዚ ምክንያት በትግራይ ከኣንድ ቤተሰብ ቢያንስ ኣንድ ታጋይ (የተሰዋም በህይወት ያለም) ነበር (ኣለ)።

ነገር ግን ሁሉም የትግራይ ተወላጅ የህወሓት ደጋፊ ኣይደለም። ምሳሌዎችን ልጥቀስ።

ምሳሌ ኣንድ

የትግራይ ኣርሶ ኣደር የታገለበት ዓላማና የመሪዎቹ ለየቅል ነበር። በ1983 ዓም የህወሓት መሪዎች ኣራት ኪሎ ቤተ መንግስት ከገቡ በኋላ የመሪዎቹ ዓላማ ለታጋይ ገበሬዎቹ ግልፅ ሆነ። በታጋዮቹና መሪዎች የዓላማ ልዩነት ግልፅ ሆነ። ታጋይ ገበሬዎቹ ጥያቄ ኣስነሱ። ጥያቂያቸው ምን ነበር??? ስድስት ጥያቄዎች:

(1) የኤርትራ ረፈረንደም (ነፃነት ወይ ባርነት የሚል ኣማራጭ) ስሕተት ነው፤ ለሀገር ኣንድነት መስራት ሲጠበቅብን ምንሊክ የሰራው ስሕተት እየደገምን ነው (ኃይለስላሴ እንኳ ለማስተካከል ሞክሮ ነበር)።

(2) የባህር በር (ወደብ) ያስፈልገናል። ሁሉም ነገር ለሻዕቢያ መስጠትና ኣገልጋይ መሆን በታሪክ ተጠያቂዎች ያደርገናል።

(3) የተታገልንበት ዓላማ መንገዱ እየሳተ ነው። ዓላማችን ስልጣን መያዝ ብቻ ኣልነበረም፤ ዲሞክራሲ ማስፈን ነው።

(4) ሙስና እየተስፋፋ ነው፣ ትግላችንና መስዋእትነቻን በኣሉታዊ መልኩ ይጎደዋል።

(5) የደርግ መሪዎች እንጂ ሁሉም የደርግ ወታደሮች ጠላቶቻችን ኣይደሉም፤ በመከላከያ ሰራዊታችን ይጠቃለሉ፣ ብዙ የሰለጠኑና የሀገር ሃብት ፈሰስ የተደረገባቸው ናቸው።

(6) ሻዕቢያ ሊወረን እየተዘጋጀ ነው፤ ወታደራዊ ዓቅሙ እየገነባ ነው። እኛ ደግሞ ሀገራዊ መከላከያ ሰራዊት ይኑረን።
የሚሉ ጥያቄዎች ተነሱ። ነገር ግን ጥያቄዎቹ ወድያው ሻዕቢያ ጀሮ ደረሱ። የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ ኣፈዎርቂ ከመለስ ዜናዊ ጋር ተነጋገሩበት። እንደዉጤቱም በ1985 ዓም ከ32, 000 በላይ የሚሆኑ የህወሓት ታጋዮች (ጥያቄ ያነሱ) እንዲባረሩ ተደረገ።

እንኳን የትግራይ ህዝብ በሙሉ፣ ህወሓት የታጋዮቹ ድጋፍ የለውም። መረጃ ስለሌለን ግን ሁሉም የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ ኣድርገን እናስባለን።

ምሳሌ ሁለት

ሑመራ ኣከባቢ ነው፣ ልዩ ስሙ ማይካድራ። ኣንድ የድሮ ታጋይ ሴት ሦስት ልጆች ብቻዋ ታሳድጋለች። የማይካድራ ህዝብ (እንደሌላው ሁሉ) በመለስ ሞት ምክንያት የሓዘን ሰልፍ እንዲያደርግ በካድሬዎች ታዘዋል። ሴትየዋ በሓዘን ሰልፉ ኣልተገኘችም። በፖሊስ ተይዛ እንድትታሰር ተደረገ (የታሰሩ ብዙ ናቸው ግን ይቺ ሴት መረጥኩኝ)። በፖሊስ ለምን እንዳልተገኘች ተጠየቀች።

ሴትየው: ስራ ስለበዛብኝ ነው ያልመጣሁት

ፖሊስ: ስራ ቢበዛብሽስ??? ስራ ከመለስ ይበልጣል?

ሴትየው: እኔ ኮ ብቻየን ሦስት ልጆች ኣሳድጋለሁ።
ፖሊስ: እና?
ሴትየው: እናማ ስራ ይበልጥብኛል። ደሞኮ ሞት ብርቅ ኣይደለም። መስዋእትነት ኮ እናውቀዋለን። ባሌን ታውቀዋለህ። ታጋይ ነበር። ድሮ ተሰውተዋል። ልጆቹ ማሳደግ ኣይችልም። የኔና የተሰዋው ባለቤቴ ሓላፊነት ተሸክሜ ልጆቻችን ለማሳደግ ሌት ተቀን መስራት ኣለብኝ። መለስ ከሞተ እናንተ ቅበሩት።

ፖሊስ: ኣንቺ ራስሽ ታጋይ ነበርሽ። ባልሽም ተሰውተዋል። መለስ ደግሞ የሰማእታት ኣርኣያ ነው። ስለዚ ልታዝኚለት ይገባል።

ሴትየው: መለስ ከምወደው ባሌ ኣይበልጥብኝም። ኣሳዛኝ መስዋእት ኮ ጫካ ዉስጥ ተሰውተው ያለቀባሪ ተጥለው የቀሩ፣ ሬሳቸው የጅብና ኣሞራ ሲሳይ የሆነ፣ (ኣብ ፈቀዶ ጎቦታትን ሽንጥሮታትን ዝተረፉ) እንጂ ……. መለስ ኮ ብዙ ነገር ኣይተዋል። ኣሁን ደግሞ በክብር፣ በስርዓት እያረፈ ነው። ባሌኮ የቀብር ስነስርዓት ኣልተደረገለትም። ምን ታካብዳላቹ?! በመለስ ሞት ግን ባሌና የትግል ጓደኞቼ (ስውኣት ብፆተይ) ኣስታውሼ ኣዝኛለሁ።

ሴትዮዋ ተፈታች። እኛ ግን የትግራይ ህዝብ በስርዓቱ ደስተኛ ይመስለናል። ዉስጡ እየነደደ ነው።

ምሳሌ ሦስት

በትግራይ ሓውዜን ኣከባቢ ነው። ኣንድ ኣብሮ ኣደጌ (ጓደኛየ) ኣስታወስኩ። ኣብረን እንማር ነበር (እስከ ስድስተኛ ክፍል)። ከስድስተኛ ክፍል በላይ ትምህርቱ መቀጠል ኣልቻለም። የልጁ ኣባት የህወሓት ታጋይ ነበር፤ ተሰውተዋል። ከኣያቶቹ ጋር ይኖራል። ኣያቶቹ ሦስት ልጆች ነበሯቸው። ሁሉም ተሰውተዋል። የቀራቸው የልጅ ልጃቸው (እሱ ብቻ) ነው።

ከሁለት ዓመት በፊት ልጁ ከመንግስት የወሰደውን ብድር መመለስ ስላልቻለ ወደ ሑመራ ኣከባቢ ይጠፋል። ኣያቶቹ ይታሰራሉ።

መታሰራቸው ሰምቶ መጣ። ብዙ ነገር ደረሰበት። የጣብያ (ቀበሌ) ካድሬዎቹ ተቃወማቸው። ካድሬዎቹ ኣስተዳዳሪዎችም ኣባቱ የተሰዋበት ዓላማ ተቃወመ ብለው የኣከባቢው ሰዎች ከነሱ ቤተሰብ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳያደርጉ ተነገራቸው። (ያ ሦስት ልጆች የተሰውበት ቤተሰብ እንዲገለል ተደረገ)። በኣሁኑ ሰዓት ግን ይሄን የማግለል ስትራተጂ እየተውት ይገኛሉ።

ምሳሌ ኣራት

በትግራይ ኣስተማሪዎች በገዢው ፓርቲ የሚደርሳቸው ኣስተዳደራዊና ኢኮኖሚያዊ በደል በመቃወም የተለያዩ እርምጃዎች የሚወስዱበት ኣጋጣሚ ኣለ። ተደጋጋሚ የስራ ማቆም ኣድማ ይደረጋል። ኣንዳንዴም የመምህርነት ስራው ጠቅልሎ የመተው ነገር ኣለ። ለምሳሌ ትግራይ ምስራቃዊ ዞን የመማር ማስተማር ሂደቱ ተስተጓጉሏል። ነጋሽ ኣከባቢ በሚገኝ ኣንድ ትምህርትቤት ሁሉንም ኣስተማሪዎች (ዳይሬክተሩ ጨምሮ) ትምህርትቤቱ ዘግተው ጠፍተዋል። ግን የሚዘግበው ሰው የለም።

ምሳሌ ኣምስት

በኣንዳንድ ኢትዮዽያውያን የትግራይ ተወላጆች የኢህኣዴግ መንግስት በመደገፍ ኢትዮዽያውያንን ይበድላሉ ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ብዙዎች ይህንን እንደሚቃወሙ እንዴት ልንገራቹ?

ዓረና ትግራይ ፓርቲ በሺዎች የሚቆጠሩ ኣባላት እንዳሉት ሰምቻለሁ። እነዚህ ታድያ ህወሓት የሚቃወሙ ኣይደሉምን? ዴምህት የተባለ ኣማፂ ቡድን 60 ሺ ወታደሮች እንዳሉት ይነገራል። 60 ሺው ትክክል ላይሆን ይችላል። ግን ከ 20-25 ሺ ወታደር እንደሚኖረው ግን ይገመታል። እንዚህ ሁሉ የትግራይ ተወላጆች ናቸው።

በ1997/98 ዓም ከሻዕቢያ ሬድዮ በሰማሁት መረጃ መሰረት (ቃለ መጠይቅ ሲደረግባቸው) ብዙዎቹ የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት ኣባላት ነበሩ። ወደ ኤርትራ የገቡበት ምክንያት ሲያስረዱ በ1997 ና98 በነበረ የህዝብ ዓመፅ የተወሰደ እርምጃ በመቃወም ነበር። ስለዚ ሁሉም የትግራይ ህዝብ ገዢው ስርዓት ይደግፋል ብሎ ማሰብ ስሕተት ነው።

በሌላ በኩል ስናየው ደግሞ ስራ ነው። ኣንድ ሰው ስራ ፈልጎ ወደ ፖሊስነት ወይ ውትድርና ሊገባ ይችላል። የእንጀራ ጉዳይ ነው። ከገባ ታድያ (ደመወዙን ለማግኘት) የታዘዘውን መስራት ኣለበት። ካልሰራ ይባረራል፤ ከተባረረ መኖር ኣይችልም (ሌላ ስራ እስካላገኘ ድረስ)። ስለዚ ጠንክሮ ቢሰራ ኣይደንቀኝም።

ባጠቃላይ የትግራይ ህዝብ በሙሉ የህወሓት ደጋፊ ነው ማለት ኣይቻልም። ብዙ የሚቃወም ኣለ። ብዙ የሚጨቆን ኣለ። በትግራይ የሌለው ጭቆናን የሚያጋልጥ ነው። በሌሎች ኣከባቢዎች (ከትግራይ ውጭ) ሰው ሲታሰር ወይ ሲገደል የሚናገርለት ወይ የሚጮህለት ወገን ኣለው። በትግራይ ግን የለም። ኣንዱ ሲታፈን ሌላው ኣብሮ ዝም ይላል። ይሄ ነው ልዩነቱ እንጂ በትግራይ ጭቆና ስለሌለ ኣይደለም።

በመጨረሻም

እንደው ሁሉንም ትተን፣ የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ቢደግፍ (ከህወሓት ጎን ቢቆም) ችግሩ ምንድነው? ኣንድ ህዝብ የፈለገውን የመደገፍ ወይ የመቃወም መብቱ የተጠበቀ ነው። የትግራይ ህዝብ ህወሓትን (በፍላጎቱ ኣይደግፍም እንጂ) ቢደገፍ ደስተኛ ነኝ። ምክንያቱ ‘ለምን ህወሓትን ትደግፋለህ?’ ሊባል ኣይገባም። ሌሎች ህዝቦች ህወሓትን የመቃወም መብት ያላቸው ያህል የትግራይ ህዝብም የመደገፍ መብት ኣለው።

ስለዚ (1) ሁሉንም የትግራይ ህዝብ (ብዙዎች እንደሚያስቡት) የህወሓት ደጋፊ ኣለመሆኑ እንዲታወቅ። (2) የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ይደግፋል ብሎ መውቀስም ተገቢ ኣይደለም



http://ethioforum.org/

torsdag 15. august 2013

ሰበር ዜና፤ ኢህአዴግ ከከፍተኛ አበል ጋር ፀረ አንድነት ፓርቲ ስልጠና አዘጋጀ

አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ ለማስተጓጎል ከፍተኛ አበል በመክፈል ለአባላቱ ስልጠና ማዘጋጀቱን ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡
አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ህዝባዊ ተቀባይነት ማግኘቱንና በስኬት መቀጠሉን ተከትሎ ኢህአዴግ “አንድነት ፓርቲንና ንቅናቄውን እንዴት ማስቆም ይቻላል” በሚል በከፍተኛ አመራሮቹ ውይይት ካደረገ በኋላ በመላ ሀገሪቱ ፀረ አንድነት ፓርቲ ስልጠና “ጠንካራ” ላላቸው አባላቱ ለመስጠት መዘጋጀቱን የሚገልፁት ምንጮቹ “ለስልጠናው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ተመድቧል፤ ኢቲቪና የክልል ሬዲዮ ጣቢያዎችና የመንግስት ጋዜጦች አንድነት ፓርቲ የሸሪአ ህግን በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ ከሚንቀሳቀሱ ሽብርተኞች ጋር እየሰራ ነው የሚል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እንዲከፍቱ ጥብቅ መመሪያ ደርሷቸዋል፡፡” በማለት ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ምንጮቹ አክለውም “ኢህአዴግ ከየቀበሌው እየመረጠ ስልጠና የሚሰጣቸው አባላቱ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችንና አባላትን በማሸማቀቅ፣በማስፈራራት፣ በቤተሰቦቻቸውና በሃይማኖት አባቶቻቸው በኩልም ከፖለቲካ እንዲወጡ ተፅዕኖ እንዲደርስባቸው የተቻላቸውን እንዲያደርጉ የሚያበቃ ነው” ብለዋል፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንዳረጋገጡት የዚሁ ስልጠና አካል የሆነ ስልጠና ከነገ ጀምሮ በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ከየቀበሌው ለተውጣጡ ከ200 በላይ ለሚሆኑ የኢህአዴግ አባላት ለሁለት ቀን ይሰጣል፡፡

ምንጭ ፍኖተ ነጻነት

በኖርዌይ “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” ድጋፍ አሰባሳቢ ጊዜያዊ ግብረ ኃይል መግለጫ

August 14, 2013
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን እንደ ወያኔ ዘመን የተዋረዱበት የተናቁበትና የተበደሉበት ጊዜ የለም።በአሁኑ ወቅት አገሪቱና ህዝቧ ከፊታቸው የተጋረጠው ችግር የመሰረታዊ የዲሞክራሲና የሰብኣዊ መብቶች አለመከበር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሕልውና ጥያቄና ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቀጠልና ያለመቀጠል ጉዳይ ሆኖዋል።
የትጥቅ ትግልም በኢትዮጵያ የወቅቱ የፖለቲካ ሁናቴ እንደ አንድ ምናልባትም እንደ ብቸኛ የትግል አማራጭ እየሆነ ከመጣ ውሎ አድሯል።
“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የወያኔ ግፍና በደል በአንገፈገፋቸው በሃገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች፣ ምሁራንና በተለያዩ ዜጎች የተመሰረተ ድርጅት ነው። የዚህ ኃይል ራዕይ ደግሞ ሕዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን፣የዜጎች መብቶች፣አገራዊ አንድነት፣ደህንነትንና ጥቅም እንዲከበሩና ጠንካራ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትገነባ መስዋዕትነትን በመክፈል አስተዋጾ ማድረግ ነው።Ginbot 7 Popular Force (G7PF) is established by freedom-loving Ethiopians
“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” ወያኔን በኃይል ለማስወገድ ፣ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር በአገሪቱ እንዲኖር ማስቻል እና ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነፃ ጠንካራና ብቃት ያላቸው ህገ-መንግስታዊ የመከላከያ፣ የፖሊስ፣የደህንነት ተቋማት እንዲኖሩ አስተዋጽዎ ማድረግን እንደ  አንድ ግብ ይዞ የተነሳ ኃይል ነው።
“በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” ውስጥ የተመቻቸ ኑሮአቸውን፣ቤተሰቦቻቸውን እና የሚወዱትን አገርና የሰለጠኑበትን ሙያ እርግፍ አድርገው በመተው ትእግስትን የሚፈታተን መከራና እንግልት የሚበዛበትን የትጥቅ ትግል የተቀላቀሉ በርካታ ምሁራን ይገኙበታል። ይህም ከዚህ በፊት በስፋት የሚታወቀውን “ያልተማረውን ዜጋ ወደ ጦር ግንባር” የመላክና የመስክ ላይ ትግሉም በትምህርት ላይ የተመሰረተ አመራር የማጣት ችግርን የቀረፈ እና ታጋዩ ህብረተሰብ በዕውቀት ላይ በመመርኮዝ “ለምንና ለማን ነው የምታገለውና የምሰዋው” ጥያቄን በሚገባና በጥልቀት የተገነዘበ ኃይል ነው።“በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” ውስጥ የተመቻቸ ኑሮአቸውን፣ቤተሰቦቻቸውን እና የሚወዱትን አገርና የሰለጠኑበትን ሙያ እርግፍ አድርገው በመተው ትእግስትን የሚፈታተን መከራና እንግልት የሚበዛበትን የትጥቅ ትግል የተቀላቀሉ በርካታ ምሁራን ይገኙበታል። ይህም ከዚህ በፊት በስፋት የሚታወቀውን “ያልተማረውን ዜጋ ወደ ጦር ግንባር” የመላክና የመስክ ላይ ትግሉም በትምህርት ላይ የተመሰረተ አመራር የማጣት ችግርን የቀረፈ እና ታጋዩ ህብረተሰብ በዕውቀት ላይ በመመርኮዝ “ለምንና ለማን ነው የምታገለውና የምሰዋው” ጥያቄን በሚገባና በጥልቀት የተገነዘበ ኃይል ነው።
ይህንን ለኢትዮጵያና ሕዝቧ መልካም ራዕይ አንግቦ የተነሳ ሠራዊት በተቻለ ሁሉ መደገፍና ደጀንነታችንን ማረጋገጥ የውዴታ ግዴታችን መሆኑን የተገነዘብን በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን አንድ ግዜያዊ  የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረኃይል በማቋቋም ከፍተኛ እንቅስቃሴ ጀምረናል።
በግብረኃይሉ መርሃግብር መሰረት መስከረም 28 ቀን 2013 (እ.ኤ.አ) “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” አመራር ተወካዮች በሚገኙበት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በኦስሎ ከተማ ተዘጋጅቷል።
በፕሮግራሙ ላይ ውይይት፣ የገቢ ማሰባሰቢያና የመዝናኛ መርሃግብሮች ተካተዋል። በመሆኑም ነፃነት ለኢትዮጵያ ሃገራችንና ለሕዝቧ ከዚያም በላይ ለእኔ ስብዕና ያስፈልገኛል ብለን የምናምን ሁሉ በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ደጀንነታችንን “ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል”  እንድናሳይ ጥሪያችንን በትህትና እናቀርባለን።
ነፃነት፣ ፍትህ፣እኩልነትና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኖራለች !!!
በኖርዌይ “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል”  ድጋፍ አሰባሳቢ ግዜያዊ ኮሚቴ
ኦገስት 14፣ 2013 ኖርዌይ፣ ኦስሎ
የፌስ ቡክ ኢቬንቱን እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል

torsdag 8. august 2013

ለተለያዩ ስልጠናዎች ወደ ደቡብ ኮርያ ከመጡት 59 ኢትዮጵያዊያን መካከል 38 ጥገኝነት ጠየቁ

August 8, 2013
Ethiopian Asylum Seekers in Korea
ሰበር ዜና፣ ከስምንት ወር በፊት ለተለያዩ ስልጠናዎች ወደ ደቡብ ኮርያ ከመጡት 59 ኢትዮጵያዊያን መካከል 38 ኢትዮጵያዊያን የኮርያን መንግስት ጥገኝነት ጠየቁ። ከነዚህ ኢትዮጵያዊያን መካከል ኣንዳንዶቹ በሲቪል ሰርቪስ፣ በባንክ ፣ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ በተለያዩ ፋብሪካዎችና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ የሚሰሩ ነበሩ። ጥገኝነት ከጠየቁት መካከል ኣንዱ የኣዲስ ኣበባ ፖሊስ ባልደረባ መሆኑም ታውቋል።
እነዚህ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ላለፉት ስምንት ወራት በኮርያ መንግስት የተዘጋጀላቸውን ስልጠናዎች ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን የሙያ ስልጠናውን ከጨረሱ በሁዋላ ጥገኝነት ለመጠየቅ መወሰናቸውን ኣሳውቀዋል። ጥገኝነት ለመጠየቅ ያበቃቸውን ነገር ሲገልጹ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰባዊ መብት ጥሰት በመቃወም፣ በግላቸው በሚሰሩባቸው መስሪያ ቤቶች የመንግስት ኣካላት ባደረሱባቸው በደል ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
እነዚህ ወገኖች በኣሁኑ ሰኣት ፒናን በተሰኘ የመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ሲሆን በኮርያ ቆይታቸው ሃገራቸውን ከኣምባገነን ኣገዛዝ ለማላቀቅ ከሚታገሉ ሃቀኛ ድርጅቶች ጋር ኣብረው በቆራጥነት ለመታገል መወሰናቸውን በኣንድ ድምጽ ገልጸዋል። ስለተሰጣቸው ስልጠና የኮርያን መንግስት ኣመስግነው ወደፊት ለሚያደርጉት የነጻነት ትግል የኮርያ መንግስት ድጋፍ እንደማይለያቸው ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ተጨማሪ መረጃ ለሚሹ ወገኖች ከጥገኝነት ጠያቂዎቹ መካከል የቡድኑን ተወካዩች በስልክ መግኘት ይቻላል።
ሲሳይ ወልደግብሬል 821059503443 ቶማስ ኣሻሜ 821059506511 ኣልዓዛር ስዩም 821059503443
ከኣክብሮት ጋር ገለታው ዘለቀ
Ethiopian Asylum Seekers in Korea 1

በምድረ – ኢትዮጵያ ያለው አሸባሪ ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው!!

የወያኔ አገዛዝ ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ ያወጣው የእብሪት ማስፋራሪያና ዛቻ ቀለም ሳይደርቅ ያ የለመዱ እጁ አሁንም በንጹሃን ወገኖቻችን ደም ተጨማልቋል። የወያኔ እብሪት የሰው ልጅ ሊሸከም የሚችለውን ለከት አልፏል። አንድ አመት ከመንፈቅ ሙሉ ጠጠር ሳይወረውር መብቴን፣ ስብእናዬን፣ መሰረታዊ መብቴንና ነጻነቴን ብሎ ህገ-መንግስት እየጠቀሰ አቤት ስሙን ያለ ህዝብ በምን መለኪያ አሸባሪ ሊሆን ይችላል? ለመሆኑ ህፃን፤ሽማግሌ፤ ወንድና ሴት ሳይለይ ያገኘዉን በሙሉ በጥይት የሚቆላዉ ወያኔ ነዉ ወይስ መብቴንና ነጻነቴን አክብሩልኝ ብሎ በትእግስትና በጨዋነት የጠየቀ ህዝብ ነዉ ሽብርተኛ መባል ያለበት መልሱን ወያኔን በጭፍኑ የሚደግፉትን ጨምሮ ህሊና ላለው ዜጋ ሁሉ እንተዋለን።

ዋናው ጥያቄ መሆን ያለበት ይህንን እብሪትና እብጠት እንዴትና መቼ እናቁመው የሚለው ነው። ወያኔ የፈሪ አክራሪ ነው። ታገሱኝ፣ አፈግፍጉልኝ፣ አክብሩኝ እያለም እንኳን ከጭካኔ የሚያቆም ህሊና በሌላቸው ደነዞችና ጨካኞች የተሞላ ዘረኛ ተቋም ነው። ዛሬ የሚቀማጠሉበትን ስልጣንና ምቾት ይነካብናል፣ እንቅልፍ ይነሳናል ያሉትን የህዝብ ትንፋሽን ሁሉ ፀጥ ለማድረግ መወሰናቸውን ካየን ከሰማን ውለን አድረናል። በወያኔ መንደርና አገዛዝ በገዛ ሀገራችን ቀና ብለን መሄድ፣ በትውልድ መንደርና ቀያችን መኖር፣ በዜግነታችን የሚገባንን መሰረታዊ ጥያቄ ማንሳት ሽብርተኞች አሰኝቶ በጥይት የሚያስቆላና በወህኒ የሚያሰበስብ ወንጀልና ሀጢያት ከሆነ ዉሎ አድሯል። ህግና ህገ-መንግስቱ ተብዬዉ የተጻፈበትን ወረቀት ያህል እንኳን ዋጋ ካጣ ሰንበትበት ብሏል።

ሰሞኑን ኮልፌ ዉስጥ በንጹሃን የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ ወያኔ የፈጸመው ግፍ የሚዘገንን ጭካኔ ይሁን እንጂ ከወያኔ አረመኔዎች የማንጠብቀው አይደለም። ወያኔ እያሸበረን አሸባሪ ሲለን፣ እየገደለ ገደሉ ሲለን፣ በክብር ስንለምነው እያዋረደን እንደ ህዝብ ሳይሆን እንደ መንጋ እየተቆጣጠረ ሊገዛን ቆርጧል። ወያኔ ከሰዉነት ደረጃ ወጥተን ወደ እንስሳነት ተለዉጠን ሃይማኖታችንን ጭምር እሱ መርጦልን፣ ልማትና እድገትን ከእኔ ዉጭ ከሌላ አትጠብቁ እያለበረሃብ እያለቅን ጠገብን እያልን አጎንብሰን እንድንኖር ይፈልጋል። ባለፈዉ ሳምንት ያሰራጨዉ የማስፈራሪያ መግለጫና ፀረ-ሽብርተኛ የሚለው ህግ አላማም ይሄዉ ነው። ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ መሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፤ ወጣቶችን ባጠቃላይ ሰላማዊ ታጋዮች፣ የኢትዮጵያን እስር ቤቶች የሞሉት ይህንን የወያኔን ፀረ ህዝብና ፀረ አገር ድርጊትና አላማ ስተቃወሙ ብቻ ነው።

ለወያኔ ግፍና በግፈኝነቱ እንዲቀጥል በከፊል ተጠያቂዎች የሆንን የዚች ሀገር ዜጎች ሁሉ አስተዋጽኦ አላደረግንም ማለት አይቻልም። ነግ በኔ ማለት አቅቶን ዛሬ አንዱን ሲያጠቃ፣ ሲገድልና ሲያስር ሌሎቻችን ዝም እያልን በየተራ ለመጠቃትና ለመዋረድ ተመችተነዋል። ሙስሊሙ ሲጠቃ ክርስቲያኑ ተመልካች ይሆናል። ክርስቲያኑ ሲጠቃ ሙስሊሙ ይመለከታል። ኦሮሞው ሲቀጠቀጥ አማራው ይመለከታል። አማራው ሲወገር ኦሮሞው ቆሞ ያያል። በሌላ አነጋገር ሁላችንም በቃ ብለን በአንድ ላይ መነሳት አቅቶናል። ወያኔ ትላንት ላፈሰሰው ደም ሂሳብ ስላልከፈለ ነው ደግሞና ደጋግሞ ደማችንን የሚያፈሰው። አንድ ሆነን ከመታገልና ከመነሳት ውጭ አማራጭ እንደሌለን የዘነጋነው ይመስላል። አንድ ሆነን የተነሳን እለት ወያኔ ምን ያህል ኢምንት ሃይል እንደሆነ ማየት አቅቶናል።

ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥቃትንና ውርደትን መሸከም፣ መስማትና ማየት፣ መሰደድና መታሰር፣ መንገላታቱ ያንገፈገፈህ ወገን ሁሉ፤ ስለ ሀገርህ፣ ስለማንነትህ ህልውና ስትል አንድ ሆነህ ለመነሳት ጊዜው አሁን ነው፤ ፈርጣማ ክንድህን የምታሳይበት፣ የአበውን እምቢና አልገዛም ባይነት ለዘረኛው ወያኔ የምታሳይበት ጊዜ ዛሬ ነዉ እንላለን፤ እኛ የወያኔን ማንነት በቅጡ የተረዳን የግንቦት 7 ንቅናቄ ልጆችህ።

በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለው አሸባሪ ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው!! ከወያኔ ውጭ አለምአቀፍም ሆነ ሀገረኛ አሸባሪ በሀገር ውስጥ የለም። ወያኔ አሸባሪ የሚለን አለም አቀፋዊ ልመናው እንዳይቆም ብቻ ነው። ሊበላን የፈለገው አሞራ ስለሆንን ብቻ ነው ጅግራ የሚለን።

ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሀገራችን ህዝብ ሁሉ በአንድነት የነጻነት አሞራዎች እንድንሆን ዛሬም ጥሪውን በድጋሜ ያቀርባል። ሽብርተኛው ወያኔ፣ ህግ፣ ሰበአዊነት፣ ስልጡን ፖለቲካ ቀርቶ ተራ ይሉኝታ የሌለው፣ በልቼ ልሙት ወይም እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ብሎ የቆረጠ ዘረኛ ቡድን ነውና ልናስወግደው የግድ ይለናል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ ፖሊስ ጥቃት እየፈጸመ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ ፖሊስ ጥቃት እየፈጸመ እንደሆነ ሰማሁ!
በአዲስ አበባ ስታድየም አመታዊውን የኢድ በዓል አክብረው እግረመንገዳቸውንም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ሲገልፁ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በፖሊስ የድብደባ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ እየሰማሁ ነው፡፡
በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች እንዲሁም በሌሎች ክልሎች ከኢድ በዓል ጋር ተየያይዞ የተሰማውን ተቃውሞ ለምን አሰማችሁ ያለው መንግስት ርምጃዎችን እየወሰደ ነው፡፡
ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በዛሬው ተቃውሟቸው ባለፈው ወቅት አንድ ግለሰብ አሮጌ ባንዲራ ሲያውለበለበ  እያሳየ የድምጻችን ይሰማ አባላት ባንዲራ እንዳቃጠሉ አድርጎ ሲዘግብ የነበረውን የመንግስት ሚዲያ ዘገባ ፉርሽ በሚያደርግ መልኩ በባንዲራ አጊጠው ነበር የወጡት፡፡
መንግስት ጥቃት እየፈጸመ ለው ለምን ባንዲራ ያዛችሁ ብሎ ይሁን፣ ለምን አላህ አክበር አላችሁ ብሎ ይሁን፣ ለምን ድምጻችን ይሰማ አላችሁ ብሎ ይሁን ለማጣራት ያደረኩት ሙከራ የለም… ብቻ ወገኖቻችን በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ መከራ እያዩ ነው፡፡