onsdag 11. juni 2014

ቅድመ-ውህደቱና ልዩ ገጠመኞቹ

une11/2014
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት በተካሄደው የግማሽ ቀን ስነ-ስርዓት ተከናውኗል። በስነስርዓቱ ላይ በርካታ ታዋቂ ሰዎች፣ ፖለቲከኞች፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና ዲፕሎማቶች ተገኝተው ነበር

የቅድመ-ውህደቱ አጠቃላይ ይዘት
የውህደቱ የፊርማ ስነ-ስርዓት በተካሄደበት ወቅት የሁለቱ ፓርቲ አመራሮች ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል። የሁለቱም መሪዎች ንግግር ውህደቱ ከመዘግየቱ በስተቀር አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ከቅድመ ውህደት ስነ-ስርዓት ፊርማው በኋላ ለጋዜጠኞች አጠር ያለ ጋዜጣዊ መግለጫ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ስለነበር በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ ጋዜጠኞች ለሁለቱ ፓርቲ መሪዎች ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር።
ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል በቀጣይ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ የሚመሰረተው ፓርቲ ስያሜ ምን ይሆናል የሚል ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ስያሜው የሁለቱን ፓርቲዎች ስያሜ ባቆራኘ መልኩ አዲስ ስም ይወጣል ብለዋል። ስያሜው የሚፀድቀው በአዲሱ ውህድ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ መሆኑንም አስረድተዋል።
በተመሳሳይ ሌሎች ፓርቲዎችን ታሳትፋላችሁ? ለሚለው የጋዜጠኞች ጥያቄ መኢአድና አንድነት በመዋቅር ጥንካሬና በአባላት ብዛት በአንፃራዊ ደረጃ ከሌሎች ፓርቲዎች የተሻሉ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ይህ ብቻ በቂ ባለመሆኑ ሌሎች ፓርቲዎች እንዲገቡበት በማድረግ ኢህአዴግን የሚፎከር አብይ ብሔራዊ ፓርቲ ለማቋቋም መታሰቡን ገልፀዋል። የአሁኑም የአንድነትና የመኢአድ ቅድመ-ውህደት እንደ ውህደት ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።
በተጨማሪም በአንድ ወር ውጥ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ አዲሱን ውህድ ፓርቲ ለመፍጠር የአቅም ጉዳይ በጋዜጠኞች ተነስቶ የነበረ ሲሆን፤ “ችግራችን የአመራር እና ድርጅታዊ አቅምን የማንቀሳቀስ እንጂ የአቅም አይደለም። አባላቶች በከፊልም ቢሆን የራሳቸውን ወጪ በመሸፈን ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የሁላችንንም ፍላጎት እናሳካለን” ሲሉ ኢንጂነር ግዛቸው መልሰዋል። በቅርቡም የሁለቱም ፓርቲዎች ብሔራዊ ም/ቤት የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ በመሰየም ሁኔታውን ያፋጥናል ብለዋል። አዲሱ ውህድ ፓርቲም ከሁለቱ ፓርቲዎች የተውጣጣ 400 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ይኖሩታል ብለዋል።
ቀደም ሲል በመኢአድ በኩል “አንድነት ከመድረክ ካልወጣ ውህደቱ አይሳካም” የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለተነሳው ጥያቄ ጉዳዩ በሕግ ባለሙያዎች ታይቶ በመድረክም ሆነ አዲስ በሚፈጠረው ውህድ ፓርቲ ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ እንደሌለ መረጋገጡ፣ አንድነት ከመኢአድ ጋር ውህደት በሚፈፅምበት ወቅት ሕጋዊ ሰውነቱን ወዲያውኑ ስለሚያጣ ከመድረክ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ወዲያውኑ የሚቋረጥ በመሆኑ ችግር እንደማይፈጠር ተረጋግጧል ሲሉ ኢንጂነር ግዛቸው ተናግረዋል።
ሌላው ከጋዜጠኞች የቀረበው ጥያቄ፤ ቅድመ ውህደቱ የተሳካው በፓርቲዎቹ አመራሮች ሳይሆን፤ በሽማግሌዎች ግፊት ስለሆነ ምን ያህል ዘላቂነት ይኖረዋል የሚል ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኢንጂነር ግዛቸው፤ በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል የውህደት ፍላጎት መንፀባረቅ የጀመረው ከአራት ዓመት በፊት መሆኑን አስታውሰው፤ ለመዋሐድ ፍላጎቱ የመጣው ከአባሉና ከአመራሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፤ ነገር ግን ሽማግሌዎቹ የመጡት በመጨረሻ ውህደቱ እንዲፋጠን ድጋፍ ለማድረግ ነው ብለዋል።
አቶ አበባው መሐሪ (የመኢአድ ሊቀመንበር) በበኩላቸው አንድነት ከመድረክ ጋር ስላለው ግንኙነት ሲመልሱ፤ እስካሁን ድረስ ውህደቱን ሲያጓትት የቆየው የአንድነትና የመድረክ ግንኙነት የጠራ ባለመሆኑ ነው ብለዋል። መኢአድ ከአንድነት ጋር ሲዋሐድ ይሄው ችግር ወደ ውህዱ ፓርቲ እንዳይሄድ በመፍራት ጥያቄው በመኢአድ በኩል መነሳቱን ገልፀዋል። ሆኖም ችግሩን የሚያጠና ሁለት ገለልተኛ የሕግ ባለሙያዎች ተመድበው የመድረክና የአንድነት እንዲሁም የመኢአድ ከምርጫ ቦርድ ሕግና ደንብ ጋር ታይቶ በመጨረሻ ወደ ውህዱ ፓርቲ ሊተላለፍ የሚችለው የገንዘብና የንብረት እንጂ የፖለቲካ ባለመሆኑ በዚሁ በመተማመን የቅድመ-ውህደት ሰነዱ ሊፈረም መብቃቱን ተናግረዋል።
ሽማግሌዎቹ በአደራዳሪነት ይሳተፉ እንደነበር የጠቀሱት አቶ አበባው፤ የሽማግሌዎቹ በጎ አስተዋፅኦ ቢኖርም፤ አሁን ግን ሁለቱ ፓርቲዎች ድርድሩን በራሳቸው የጨረሱት መሆኑን ገልፀዋል።
በተጨማሪነት ከጋዜጠኞቹ የቀረበው ጥያቄ ፓርቲዎቹ የውስጥ ችግራቸውን ሳይፈቱ ወደ ቅድመ-ውህደት ፊርማ ለምን መጡ? የቅድመ-ውህደት ፊርማው ከማካሄዱ በፊት በር ላይ ቅሬታ ሲያሰሙ የነበሩ ወገኖች ነበሩ ለሚለው ጥያቄ፤ አቶ አበባው ሲመልሱ በዚህ ወቅት ፓርቲዎቹ በውስጥ ችግር ላይ አለመሆናቸውን ይልቁኑ ቅድመ ውህደቱን እንዳይፈረም ሁከት የፈጠሩት የመኢአድ አባላት ሳይሆኑ የአዲስ አበባ የኢህአዴግ አባላት ናቸው ብለዋል። “የኢህአዴግ አባል የመኢአድን የውስጥ ችግር ይፈታ የማለት መብት የለውም” ሲሉ በመግለፅ ጉዳዩ ፓርቲዎቹን ውህደት እንዳይፈፅሙ በመንግስት በኩል የተቀናጀ ጥረት መኖሩን የሚያመለክት ከመሆኑም በላይ ኢህአዴግ ጠንካራ ፓርቲ እንዳይፈጠርና በሕዝባችን ላይ የጭቆና ቀንበር ጭኖ ለመቀጠል መፈለጉን የሚያመላክት ነው ብለዋል።
ፓርቲዎቹ ከሚያደርጉት ውህደት ጎን ለጎን በ2007ቱ ምርጫ የሚኖራቸው ተሳትፎና ለዚያም የሚሆን ስትራቴጂ ምን እንደሆነ ከጋዜጠኞች ተጠይቀው የነበረ ሲሆን፤ ምርጫውን በተመለከተ የውህዱ ፓርቲ የሚወስነው እንደሆነ ኢንጂነር ግዛቸው ጠቅሰው፤ በአጠቃላይ ሁለቱም ፓርቲዎች የምርጫ ፓርቲዎች እንደመሆናቸውና በሰላማዊ ትግል የሚያምኑ በመሆኑ ምንጊዜም ለምርጫ ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል። በአንድነት ፓርቲ በኩል አማራጭ ፖሊሲ የምርጫ ስትራቴጂ፣ ማኒፌስቶ፣ ማዘጋጀት ዕጩዎችንና ታዛቢዎችን እየፈተሸ መሆኑንና በመኢአድም በኩል ይሄው ጉዳይ ስለሚኖር የሁለቱንም አጣምረን እንቀጥላለን ብለዋል። በምርጫ መሳተፍ፣ አለመሳተፉ ግን ወደፊት እንደሚወሰንና የዴሞክራሲ ተቋማቱ ነፃ መሆንና መጠናከር ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።
በጋዜጠኞች ከተነሱ ሌሎች ጥያቄዎች መካከል ከፓርቲዎች ውህደት በኋላ አንጃዎች የመፈጠር ሁኔታዎች ስለሚስተዋል ለዚህ ችግር የተቀመጠ ስትራቴጂ አላችሁ ወይ የሚል ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኢንጂነር ግዛቸው፤ ውህደቱን ተከትሎ አንጃ መውጣቱ ፓርቲዎቹን እንደማያሳስባቸው ነገር ግን የሚወጣው አንጃ ስርዓት አልበኛ ሲሆን ነው ችግሩ ብለዋል። አንጃ የሚወጣ ከሆነም ሁለቱ ፓርቲዎች በተቀመጠው መዋቅር በዴሞክራሲያዊና በሰለጠነ መንገድ መወጣት ይቻላል። ነገር ግን በስርዓት አልበኝነት ቢሮ በመውረር ከኢህአዴግ ጋር በመገናኘት መሰናክል የመፍጠሩ አካሄድ አንጃ መፍጠር አይደለም ብለዋል።
“ውህደቱ አልተስማማኝም የሚል ቡድን ካለ መብቱ ነው። ሌላ ፓርቲ ማቋቋም ይችላል። የሰለጠነ ፖለቲካ ለማካሄድ የጉልበት፣ የመደባደብና ከባህል ውጪ የሆነ ነገር ሲሆን ግን ያሳፍራል” ሲሉ ኢንጂነሩ የገለፁ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ከዚህ አንፃር በአንድነት በኩል የሚያሰጋ ነገር የለም ብለዋል።
ውህደቱ በመዘግየቱ እንደተቋም ሁለቱን ፓርቲዎች በፍጥነት ባለመስራታቸው ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ሁለቱም አመራሮች ገልፀዋል። በተለይ አቶ አበባው መሐሪ ውህደቱ ለምን ዘገየ ለሚለው የጋዜጠኞቹ ጥያቄ ሲመልሱ፤ የፓርቲዎችን መዋቅርና የፖለቲካ ፕሮግራም በማጣጣም ሂደት እንጂ ከግል ፍላጎት አለመመቸት ጋር የተያያዘ አይደለም ብለዋል። በአጠቃላይ ከአንድ ወር በኋላ በሚጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ከመኢአድ 200 ከአንድነት 200 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት አዲስ ውህድ ፓርቲ ይፈጠራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቅድመ-ውህደቱ ልዩ ገጠመኞች
የቅድመ-ውህደት ስነ-ስርዓቱን ልዩ ካደረጉት አጋጣሚዎች መካከል የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኢዴፓ) አመራር አባል የሆኑት አቶ ሞሼ ሰሙ በፕሮግራሙ ላይ መገኘት አንዱ ነበር። የእሳቸው በቦታው መገኘት ከምርጫ 97 በኋላ ከፖለቲካ ልዩነት ባሻገር በግለሰብ ደረጃ የተፈጠረውን መቃቃር ሊያለዝብ የሚችል ጥሩ ጅምር እንደሆነም እየተገለፀ ነው። የአንድነትም ሆኑ የመኢአድ የፓርቲ አመራር አባላት ለአቶ ሞሼ ሰሙ ያሳዩት አዎንታዊ አቀባበል በዕለቱ የነበሩ ጋዜጠኞችን ትኩረት ስቦ ነበር። አብዛኛዎቹ የአንድነትና የመኢአድ አመራሮች አቶ ሞሼን ያገኙዋቸው ከምርጫ 97 በኋላ መሆኑን በአድናቆት ሲናገሩ ታይተዋል።
አቶ ሞሼ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰፊ የፖለቲካ ተሳትፎ እያሳዩ የመጡ ፖለቲከኛ ናቸው። በገዢው ፓርቲ ፖሊሲዎች ላይ ከሚያነሱዋቸው የሰሉ ትችቶች ባሻገር ለሀገሪቱ ፕሬስ መጠናከር የሚሰጡዋቸው ገዢ ኀሳቦች በመስኩ ባለሙያዎችና አጋሮቻቸው ጭምር እውቅና እየተሰጠው ነው። አቶ ሞሼ በሰኔ አንዱ የመኢአድና የአንድነት የቅድመ ውህደት ስምምነት ስነ-ስርዓት ላይ በድፍረት በመገኘታቸውም በኢዴፓ እና በሌሎች ተቃዋሚዎች መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን ያለመተማመን ስሜት በመጠኑም ቢሆን እንዲለዝብ ምክንያት ሊሆን ይችላል ብሎ መገመት ይቻላል።
ሌላው በዕለቱ ስነ-ስርዓት ላይ ከታዩ አወዛጋቢ ጉዳዮች መካከል ሊጠቀስ የሚገባው የቅድመ ውህደት ስምምነቱን ለመረበሽ የተደረገው ጥረት ነው። የውህደቱን ስነ-ስርዓት ለማወክ የተደረገው ጥረት እንደ ሀገር የሚያሳፍር፣ እንደ ዜጋም የሚያሳዝን ነው።
ከአስተባባሪዎቹ ገለፃ መረዳት እንደሚቻለው የውህደት ስምምነቱ እንዳይካሄድ በር በመደብደብና ፀያፍ ቃል በመናገር ሲበጠብጡ የነበሩት ሦስት ግለሰቦች ነበሩ። በእርግጥ ስነ-ስርዓቱ ወደሚከናወንበት ስፍራ እንዲገቡ የተፈለገው አስቀድመው የተጠሩ እና ለዚያም ልዩ ባጅ ያደረጉ ብቻ ነበሩ። ሆኖም የተወሰኑ ሰዎች “ልግባ፣ አትገባም” የሚል ውዝግብ በሩ ላይ ይስተዋል ነበር። በመጨረሻም ውዝግቡ ተባብሶ በር እስከመገንጠልና ድንጋይ እስከመወራወር ተደረሰ። በመሀሉም በተወረወረ ድንጋይ በመኢአድና በአንድነት ከፍተኛ አመራሮች ላይ የጥርስ መውለቅ አደጋ በመድረሱ ሁኔታውን አሳዛኝ ትዕይንት አድርጎታል። በዕለቱም ስብሰባውን ከረበሹ ሦስት ሰዎች መካከል አንዱ የኢህአዴግ አባል መሆኑ ተገልጿል፡፡
በቅርቡ ሃያ ሦስተኛው የግንቦት ሃያ በዓል ሲከበር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከተናገሩዋቸው በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ለሀገሪቱ መድበለ ፓርቲ መዳበርና ለተቃና የምርጫ ስርዓት ከተቀመጡ ሕጎችና አሰራሮች ባሻገር ኢህአዴግ አባላቱን በስነ-ምግባር በማነፅ ተከታታይ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን፣ በሂደቱም የሚያጠፉ አባላቱን ለመቆጣጠር ከድርጅቱ የማንንም ምክር ሳይፈልግ በራሱ የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድ መግለፃቸው አይዘነጋም።  

mandag 9. juni 2014

የሕዳሴ አብዮት አተገባበር!

June 9/2014
(ተመስገን ደሳለኝ)

  ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተከታታይ ባቀረብኳቸው ጽሑፎች ገዥው-ግንባር የመረጠው ስሁት መንገድ፣ ኢትዮጵያችንን ለሳልሳዊው አብዮት እያዘጋጃት መሆኑን ማውሳቴ ይታወሳል፡፡ ይህ የለወጥ መስመርም “የሕዳሴ አብዮት” የሚል ስያሜ ኖሮት፣ ሁሉን አሳታፊ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ንቅናቄ በመፍጠር አገሪቱን በዳግም ውልደት ለማንፃት ብቸኛ አመራጭ የመሆኑ ጉዳይ በስነ-አመክንዮ ተሰናስሎ ቀርቦበት ነበር፡፡ በዚህ ተጠየቅ ደግሞ አብዮቱን ከዳር ለማድረስ ሊተገበሩ የሚችሉ (በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ) ስልቶች እና በመጀመሪያው የንቅናቄው ምዕራፍ ሥርዓቱ ለመመለስ ሊገደድባቸው የሚገቡ ጥያቄዎችን እንዳስሳለን፡፡

 ለምን እንሞታለን? 
 የዓለም ታሪክ አምባ-ገነኖች እብደታቸውን እንዲተገብሩ የሚያስችላቸው የታጠቀው ኃይል (ጦር ሠራዊት፣ ደህንነት እና ፖሊስ) ስለመሆኑ አያሌ ማሳያዎችን ዘርዝሮ ያስረግጣል፡፡ የኢትዮጵያችን የቅርብ ጊዜ ታሪክንም ብንመለከት፣ የአፄ ኃይለስላሴ ጨቋኝ አስተዳደርን ግማሽ ክፍለ ዘመን አፋፍ ድረስ ተሸክመው የተጓዙት እነዚህ ኃይሎች መሆናቸው ጉዳዩን አምነን እንድንቀበል ያስገድደናል፡፡ የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በላኤ-ሰብ ዘመን በታሪክነት ተመዝግቦ ለመታወስ የቻለውም ይህንኑ ክፍል አጥብቆ በመያዙ መሆኑ የትላንት ክስተት ነው፡፡ ባለፉት ሁለት አስርታት ያስተናገድነው የኢህአዴግ ብልጣ ብልጥ አምባ-ገነን አስተዳደርም ከከፋፍለህ-ግዛ ስልቱ በተጨማሪ ዋና መሰረቱ ጠብ-መንጃ አንጋቹ አካል ለመሆኑ ይህ ትውልድ የአይን እማኝ ነው፡፡ አዲሱ የሕዳሴ አብዮታችንም በዚህ ኃይል ላይ ትኩረት ያደርግ ዘንድ የተገደደበት መግፍኤ ይኸው ነው፡፡

 ከግፉአኑ (ከጭቁኖቹ) አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊት ‹‹ተኩስ!?›› ተብሎ በታዘዘ ቁጥር ስለምን አምሳያው የመከራ ተቸንካሪ ላይ ሁሌ ጥይት እንደሚያዘንብ እጅግ ግራ አጋቢ ነው፡፡ እውን የህፃናትን ግንባር የሚበረቅሰው፣ እህት-ወንድሙን አነጣጥሮ የሚጥለው ሥርዓቱን ተቀብሎት፣ ትዕዛዙንም አምኖበት ነው ወይ? በጉልበትም ሆነ በሥነ-ምግባር ከሚልቃቸው ግለሰቦች የሚተላለፍለትን መመሪያ እየተገበረ ሰጥ-ለጥ ብሎ የሚገዛው የግል ጥቅም አመዝኖበት? ወይስ ለአለቆቹ የዘፈቀደ ተግባር ሎሌ ሆኖ? …የደህንነት መ/ቤቱ አባላትስ እንዲህ ታች ወርደውና አጎንብሰው የፓርቲ አገልጋይ የመሆናቸው ምስጢር ምን ይሆን? ከገዥው-ግንባር የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን ድርጅቶች ቢሮ፣ አመራሩን እና ጋዜጠኞችን በመሰለል መጠመዳቸው የ‹‹እንጀራ›› ጉዳይ ብቻ ሆኖባቸው ነውን? ንፁሀንን በጠራራ ፀሀይ ሳይቀር አፍነው ለስቅየት አሳልፈው እንዲሰጡ የተገደዱበት መነሾስ ምንድር ነው? …የፖሊስ ሠራዊትስ የሥርዓቱ የማጥቂያ መሳሪያ በመሆን እንዲህ ማዕረጉን አቅልሎ ለሀፍረት የተዳረገበት ጉዳይ በማን እርግማን ይሆን? …እኮ ለምንድር ነው የእነርሱንም ጭምር ነፃነትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያውጅ ጥያቄ ባነሳን ቁጥር ደማችንን ደመ-ከልብ የሚያደርጉት?

እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ሰፊ ጥናት የሚጠይቅ መሆኑ ሳይዘነጋ፣ የንቃተ ህሊና ማነስ እና ነፍሰ-ገዳይን አወዳሹ ነባር ባሕላችን ከገፊ-ምክንያቶቹ መካከል ስለመጠቀሳቸው ለመናገር ግን የምሁራን ትንተና የሚያስፈልገው አይመስለኝም፡፡ ከዚህ አኳያም ሕዳሴን መሰረት የሚያደርገው አብዮታችን ከትኩረት ማዕከሉ ቀዳሚ አድርጎ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳና የንቃት ሥራ በመስራት፣ ባለፉት ዘመናት የጭቆናው አስፈፃሚ ሆኖ በታሪክ ጥቁር መዝገብ የሰፈረውን ታጣቂ ኃይል፣ ወደ ተባባሪነት (ሕዝባዊነት) መለወጥ እንደሚኖርበት ተረድቶ መፍትሔ ካላበጀለት በታሪክ ፊት ከሥሉስ ውድቀቱ የሚታደገው አይኖርም፡፡ በአናቱም አብዮቱ ክብሩን ሊመልስለት እንጂ፣ ነቅንቆ ሊበትነው የተነሳሳ እንዳልሆነ ታጣቂ ኃይሉን ማሳመን የእኛ ዓብይ ተግባር ነው፡፡ እነርሱ አንድም በኑሮ ውድነት፣ ሁለትም ነገን በመስጋት ስር እንዲያድሩ ተቀይደው ነጻነታቸውና መብታቸው የተገፈፈ የመሆኑን እውነታ አስረግጦ ነግሮ ከሕዝብ ጎን በመቆም ሚናቸውን ይወጡ ዘንድ ማግባባት አብዮታዊ ግዴታ ለመሆኑ ነጋሪ አያሻም፡፡ ከለውጡ በኋላም ሠራዊቱ ከአገር አለኝታነቱ በዘለለ፣ ከአድሎአዊነትና ከእርስ በርስ (ከዘውጋዊ) ጥላቻ በፀዳ ፍትሓዊ አስተዳደር ተጠቃሚ የመሆኑን ጉዳይ ማሳመኑ በቀውጢው ሰዓት ወሳኝ ድጋፍ ለማግኘት ጠቃሚ ነው፡፡ የጥቂት ጀነራሎች የሙስና ወንጀልም፣ አቻ ባልደረቦቻቸውንም ሆነ መላ ሠራዊቱን የሚወክል አለመሆኑን ከዘለፋ በራቁ ጨዋ ቃላት መወትወት ጉልህ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ይህን ታላቅ ተልዕኮ ለማሳካት በተለይም የአዛዦቹም ሆነ የተራው ወታደር ቤተሰብ፣ ጎረቤት፣ ጓደኞች፣ ዘመድ-ወዳጅ ወገኖች ቀዳሚውን ኃላፊነት መሸከም ይጠበቅባቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡

 የትግሉ ስልቶች… 
 ‹‹የከፋ ጭቆና ቢኖርም ሥርዓቱን የተሸከሙት ብዙ ሰዎች ለረጅም ጊዜ ትብብር ከነፈጉት ጨቋኙ አገዛዝ ተዳክሞ በመጨረሻ መውደቁ አይቀርም›› የሚለው ጄን ሻርፕ፤ የትብብር መንፈግ ፅንሰ-ሀሳብን የሰላማዊ ተቃውሞው ዋነኛው የትግል ማዕከል አድርጎ ያቀርበዋል፡፡ ለዚህ ስልት መተግበር ሀሳብን የማሰራጫ መንገዶች ያስፈልጋሉ፡፡ በይፋ የማይታወቁ የትግሉ መሪዎች/ቡድኖች፣ ሐሳቡ ጨቋኞቹን ለመጣል በሚካሄደው መሬት አንቀጥቅ አብዮት ላይ እንዴት ከፍተኛ ሚና ሊኖረው እንደሚችል፣ ለማሕበረሰቡ ማስገንዘብ ይገባቸዋል፡፡ ይህን ማሕበረሰባዊ ጠንካራ መረዳት ለመፍጠርም፣ በራሪ ጽሑፎችን፣ ማሕበራዊ ድረ-ገፆችን፣ ሕብረ-ዜማዎችን፣ አጫጭር አነቃቂ  ፊልሞችንና የሞባይል ስልክ መልዕክት መለዋወጫ ዘዴዎችን ጨምሮ የተለያዩ የምስልና የድምፅ ሚዲያዎችን ማመቻቸት (መዘርጋት) ይጠበቅባቸዋል፡፡ እነዚህ ከግብፅ እስከ ዩክሬን ተሞክረው የተሳኩ አማራጮችን በኢትዮጵያችንም ለመተግበር፣ በሚገባ መደራጀትና በኃላፊነት መስራት በእጅጉ አስፈላጊና ግዴታ የመሆኑ ጉዳይ አያከራክርም፡፡ እንዲሁም ከሕዝበ-ሙስሊሙ የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የተፈተነ እንቅስቃሴ ስኬታማ ተሞክሮዎችን ማጎልበትና ወደ ፖለቲካዊው ተቃውሞ መቀላቀል እንደሚቻል መዘንጋት የለበትም፡፡ የአደባባይ ተቃውሞ የሚፈቅደውን ሕገ-መንግስታዊ መብት በምልአት አንጠፍጥፎ መጠቀም ለሰላማዊ ትግሉ ዋነኛ መሰረት እንደሆነ አምኖ መቀበልም ሌላው መረሳት የሌለበት ጭብጥ ነው፡፡ እነዚህን ኩነቶች ለመተግበር የማይነጣጠሉትን እንቅስቃሴዎችም በሶስት በመክፈል በደምሳሳው እንመለከታቸዋለን፡፡

 የአደባባይ እምቢተኛነት… 
 ዛሬ ላይ ስለመታገያ መንገዶቹ ብዙ ነጥቦችን ዘርዝሮ ማቅረቡ ላያስፈልግ እንደሚችል ይሰማኛል፡፡ ምክንያቱም በአገዛዝ ውስጥ የሚመረጡ የትግል ስልቶች በይፋ ከመቅረብ ይልቅ፣ በተቃውሞው አደረጃጀት ጥልቅ ዝግጅት እንደየአውዱ እየተመረጡ ቢተገበሩ የተሻለ ውጤታማ እንደሚሆኑ አምናለሁና፡፡ ሆኖም በዚህ መነሻነት ጥቂት ነጥቦችን ብቻ አንስቼ አልፋለሁ፡፡ በእነ ጄን ሻርፕ እና መሰል የትግሉ መምህራን ተደጋግሞ የሚጠቀሰው ‹‹የአደባባይ መቀመጥ›› የሚባለው ለሰላማዊው አመፅ ግንባር ቀደም ተደርጎ ይጠቀሳል፡፡ ለረዘሙ ቀናት/ሳምንታት አደባባዮችን ሞልቶ፣ ተጨባጭ ፖለቲካዊ ማሻሻያም ሆነ መሰረታዊ የሥልጣን ሽግግር እስኪደረግ ድረስ የመተካካት ስልት በተከተለ እና ግላዊ የዕለት ተዕለት የኑሮ መመሰቃቀሎችን ባገናዘበ (በእጅጉ ጉዳቶቹን በሚቀንስ) መልኩ በፈረቃ ፕሮግራም የሚደረግ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በትእምርትነትም የእስልምናን፣ የክርስትናን እና የአይሁድ እምነት ምልክቶችን ለመሰባሰቢነት በመጠቀም፣ በዋና ዋና ግልፅ ሕዝባዊ የመሰባሰቢያ ስፍራዎች ላይ የሰላም ድንኳኖችን መዘርጋት፣ የመማፀኛ ፊርማ ማሰባሰብ፣ በሕንፃዎች አናትና በግድግዳዎች ላይ ለውጥ የሚጠይቁ መፈክሮችንና ምስሎችን መለጠፍ፣ የመኪና ጥሩንባንና ሌሎች ከፍተኛ ድምፅ ሰጪ መሳሪያዎችን ያለማቋረጥ ማስጮኽ፣ የቤት ውስጥ መቀመጥ፣ የሥራ፣ የትምህርትና የረሃብ አድማዎችን መምታት፣ በማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ ማደም፣ በየእምነት ተቋማቱ በጋራ ፀሎት ማድረግ… በዚሁ ስር የሚካተቱ ተግባራት ናቸው፡፡

 በርግጥ ይህ ሁሉ ሲሆን የአገዛዙ መሪዎች ሕዝባዊ አብዮቱን በታጠቀው ኃይል ለመቀልበስ ሙከራ ማድረጋቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ይሁንና በዚህን ጊዜ ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር እሰጥ-ገባ ውስጥ ባለመግባት፣ ምንም አይነት አፀፌታዊ ግብረ-መልስ ባለመስጠት፣ በተንኳሽ የቁጣ ቃላት በመጎነታተል ለማበሳጨት ባለመሞከር፣ ተቀጣጣይና ስለት ነገሮችን ከአካባቢው በማራቅ ወይም በፍፁም ባለመያዝ… የተቀኙ ስልቶችን መከተል የሕዳሴ አብዮታችን መገለጫ ነውና፤ በዚሁ መንገድ መፅናት ግዴታ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ይህ አካሄድ በአንዳንድ አገራት እንደተስተዋለው አጋጣሚውን በመጠቀም አብዮቱን ለመጥለፍም ሆነ ሰርገው በመግባት ወደ ደም-አፋሳሽ ነውጥ ለመግፋት የሚሞክሩትን ለመከላከል ያስችላል፡፡

 ሌላኛው ጭብጥ፣ የትግሉን ግብ በግልፅ ቋንቋ ካስቀመጡ በኋላ፣ የተለያዩ ሀገራትና ተቋማት ለሥርዓቱ የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያቋርጡ መወትወት ነው፡፡ ቀጥታዊዎቹን ሰብአዊ ዕርዳታዎች ሳይጨምር ኢህአዴግ በቀዳሚነት የባጀት ድጋፎቹን ከነዚህ ሀገራትና ተቋማት እንዳያገኝ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጫና የሚካሄድበትን ስልት መቅረፅ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ አፈናውን ለማራዘም በርትተው በሚሰሩት የሥርዓቱ ፊት-አውራሪዎች ላይ፤ የጉዞ ማዕቀቦችን ጨምሮ ሌሎች ወደ ድርድሩ ማዕቀፍ እንዲመጡ የሚያስገድዱ ግላዊ ጫናዎች እንዲጠናከሩባቸው መጣር፣ ተጨማሪ የትግሉ መንገድ መሆን ይኖርበታል፡፡

 አብዛኛዎቹ የአለማችን ጨካኝ አገዛዞችን ለታሪካዊ ሽንፈት የዳረገው ሌላው የመታገያ ስልት፣ አፋኝ ሕጎቻቸውን በግልጭ መጣስ መሆኑ በቀዳሚነት የሚወሳ ነው፡፡ በእርግጥ ይህን መሰል የአደባባይ የኢ-ፍትሓዊ ሕጎች ጥሰት ብዙ ዜጐችን ለእስር ይዳርጋል፡፡ ሆኖም የሰላማዊ አብዮት ውጤት መገለጫ፣ የዜጐች እስርን የመዳፈር ብርታት እንደሆነ ከመታወቁ አኳያ፣ ይህኛው አካሄድ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ በእኛም ምድር እስርን የሚዳፈሩ ብርቱና ቆራጥ ጎበዛዝት በተበራከቱ ቁጥር፣ የተቃውሞ አድራጊዎች መጠን በሂደት እየጨመረ እንደሚመጣና ግንባሩም ስጋት አድሮበት ከአፈና እርምጃዎቹ መቆጠቡ ስለማይቀር፣ ለምንፈልገው ሥርዓታዊ ሽግግር አስገዳጅ ፈቃደኝነት ውስጥ ልንከተው እንደሚቻለን ማመን ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ይሁንና ውጥረቱ እየበረታ በሄደ ቁጥር ሥርዓቱ ተቃውሞውን ለማክሸፍ በብዛት ወደ እስር መላኩ አይቀሬ ቢሆንም ‹ስለኔ አታልቅሱ› እንዲል መጽሐፉ፣ በእርምጃው ሳይደናገጡ በአቋም በመፅናት ከአደባባዩ ሳያፈገፍጉ፣ ታሳሪዎቹን በጀግንነት እያወደሱ፣ ለእስር የሚዳርጉ ሕጎችን በመጣስ ጀግኖቹን መቀላቀልና ማጎሪያዎቹን አለቅጥ ማጨናነቅ አገዛዙን ለማሽመድመድ ጠቃሚነቱ በተግባር የተሞከረ ስልት መሆኑን ማስታወስ ያሻል፡፡ ነፃነቱን በነፃ ያገኘ ከቶም ቢሆን የለምና! በሰላም ጊዜ እንጂ በእንዲህ አይነቱ የንቅናቄ ወቅት እስር ቤት ቅንጣት ታህል የሚያስፍራ አለመሆኑን በልበ-ሕሊና ማሳደሩ ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

 ኢኮኖሚያዊ ትብብር መንፈግ
 ስለትብብር መንፈስ መንፈግ ጉዳይ አስቀድመን ልናነሳው የሚገባን ኢኮኖሚ ተኮር የሆነውን የትግል ስልት ነው፡፡ ይህ ሥርዓት ለጭቆናው መሰረት ካደረጋቸው መካከል፣ በዝባዥ የምጣኔ-ሀብት ተቋማትን ማቋቋሙ አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እናም የኢኮኖሚ ትብብር መንፈግን ቀዳሚው የትግል አማራጫችን ብናደርገው የሕዳሴውን አብዮት ግቦች በአጭር ጊዜ ለማሳካት የማስቻሉ ዕድል የሰፋ ይሆናል፡፡ ለዚህም በዋናነት ልናተኩርባቸው የሚገቡ ሁለት ጉዳዮች አሉ፡፡ አንደኛው በማዕከላዊ መንግስቱ በቀጥታ እንደሚመሩና እንደሚደገፉ ከሚነገርላቸው ድርጅቶች፣ ምርቶችን ባለመግዛትና የምርት ሂደቱንም ከውስጥ በማጨናገፍ፣ እንዲዳከሙ ማድረግን የሚመለከት ነው፡፡ ረዥሙ ትግል ከባድ ዋጋ እንደሚጠይቀን ከተማመንን፣ ለህልውናችን የቀን ተቀን ኑሮ እጅግ ወሳኝ የሆኑትን የምርት 3 ውጤቶች ከመንግስታዊ ተቋማቱ አለመግዛት፣ ሥርዓቱን ለማሽመድመድ ውጤታማ መሆኑ አይቀርም፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ፣ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሠራተኞችንና መሀከለኛ የአመራሩን አባላት፣ የምርት ሂደቱን እንዲያስተጓጉሉ በማግባባት፣ ተቋማቱን በዝግመታዊ ሂደት አቅማቸውን ማድቀቅ አንዱ የትብብር መንፈግ አማራጭ ነው፡፡ ይህ መንገድ ከዛሬው ነባራዊ ሁኔታችን አንፃር የማይቻል ቢመስልም፤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ‹‹በርግጥ! እንችላለን!!›› እንዲል፤ እኛም የነቃንለትን ሃሳብ ለመፈፀም የማንፈነቅለው ድንጋይ እንደማይኖር በተግባር ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡ ደግሞም በቀላሉ በማይደበዝዝ መነቃቃት ካልታደስን መጪው ጊዜ አደገኛ ይሆን ዘንድ እንደመፍቀድ ይቆጥራልና፤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ መንግስታዊ የንግድ ተቋማት ውስጥ ያሉትን ሠራተኞች በአንድ የግንኙነት መስመር በማስተሳሰር ሁኔታዎች ግድ ባሉ ቀን በተመሳሳይ ጊዜ በማንቀሳቀስ፣ ሥርዓቱን ክፉኛ ማዳካሙ ተግዳሮት የበዛ አለመሆኑ አከራካሪ አይመስለኝም፡፡ የኢኮኖሚ ትብብር መንፈግን የግድ የሚያደርገው ሌላው ጉዳይ፣ ግብር (ታክስ) ያለመክፈል ሕዝባዊ እምቢተኝነትንም ስለሚያጠቃልል ነው፡፡ የጭቆናው አገዛዝ ተጠናክሮ የቆመው በታክስ ሥርዓቱ ላይ መሆኑንም ሆነ ለሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያው መጥቀሙን በቅጡ መገንዘብ ከቻልን ታክስ ባለመክፈል፣ የቆመበትን መሰረት መቦርቦር የሚቻልበት ዕድል መኖሩን ማስታወስ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

 ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያችን ነባራዊ ሀቅ፣ አብዮቶቹ ከተተገበረባቸው ሀገራት አንድ ለየት የሚል ገፅ ያለው ከመሆኑ ጋር የሚነሳ ነው፡፡ ይኸውም የገዢው ግንባር አባላት ተከፋፍለው በሀገሪቷ ኢኮኖሚ የአንበሳውን ድርሻ መያዛቸው ነው፡፡ ከማዕድን ቁፋሮ እስከ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ፤ ከፋይናንሺያል ተቋማት እስከ አልኮል ምርቶች ድረስ የተቆጣጠሩበትን መንገድ ማዳከም፤ ሕዝባዊ ጉዳት ሳይከተል ቀጥታ የሥርዓቱን የመጨቆኛ ምንጭ ማድረቁን ቀላል ያደርገዋል፡፡ በርግጥ አገዛዙ ከእነዚህ የፓርቲዎቹ ተቋማት ምንም አይነት አገልግሎት ላለመጠቀም የሚደረገውን አድማ በመመዝመዝ፣ ሂደቱን በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ያነጣጠረና ብሔሩን ሆን ተብሎ ለመጉዳት ታስቦ እንደተደረገ አስመስሎ የሚነዛውን መርዛም ፕሮፓጋንዳ ከወዲሁ ለማጨናገፍ፣ ከድርጅቶቹ ምርቶቹን ያለመግዛት ውሳኔ፣ ከማንኛውም ብሔር ጋር እንደማይገናኝ ማመን እና መተማመንን መፍጠር ቀዳሚው ተግባር መሆኑ ይኖርበታል፡፡ በ‹‹ኤፈርት›› የበለፀገች ትግራይ፣ በ‹‹ዲንሾ›› ያደገች ኦሮሚያ፣ አልያም በ‹‹ጥረት›› የተጠቀመ የአማራ ክልል አለመኖሩን፣ መጀመሪያውኑ ከልብ ተገንዝበን ከተንቀሳቀስን፣ ፓርቲ ተኮር ድርጅቶቹን ማግለል አስቸጋሪ አይሆንብንም፡፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴው ቀጣይ ቅቡል መሪዎችም ይህን ጭብጥ ሕዝቡ ዘንድ በሚገባ ማስረፅ አንዱ ኃላፊነታቸው መሆኑን ሊዘነጉት አይገባም፡፡

 የገዥው ፓርቲ አባላት… 
 ሶስተኛው ልንዘጋጅበት የሚገባው ጉዳይ፣ በመጀመሪያው የአብዮቱ እርከን ለዘብተኞቹን የግንባሩ አባላት በእንቅስቃሴው እንዲሳተፉ ማመቻቸት ነው፡፡ በተለይም ከድህረ-97ቱ የምርጫ ፖለቲካ ድቀት እና ይህን ተከትሎ በመጣው የተቃውሞ ስብስብ መዳከም የተነሳ፣ ‹ፓርቲውን በአዝጋሚው መንገድም ቢሆን እየገሩ መሄድ ይቻላል› በሚል የተቀላቀሉ እንዳሉ ይታወቃልና፤ እነዚህን ወንድሞችና እህቶች በሂደቱ ውስጥ ለማሳተፍ፣ የአብዮቱን መሪ ህልም እንዲያምኑበት ማድረጉ የግድ ነው፡፡ እነርሱን እያካተትን በተጓዝን መጠን፣ ሌሎቹም የፓርቲው አባላት ትግሉን በመቀላቀል፣ የራሳቸውን ጥያቄዎች አንግበው ሥርዓቱ ወደመነጋገር እንዲመጣ ያስችሉታል ብዬ አምናለሁ፡፡ የታቀደ አብዮት ስኬቶችን ስንመረምር እነዚህን መሰል ክስተቶችንም የለውጡ አካል ማድረጉን መረዳታችን አይቀርም፡፡ በነገራችን ላይ በመታደሳችን ዘመን ለቀደሙ ወንጀሎችም ሆነ ሀገራዊ ውድመቶች ሂሳብ ማወራረድን ታሳቢ ማድረግ ፍፁም አብዮቱን መጎተት ከመሆኑም በላይ፣ የታሪካችንን አስቀያሚ ገፅ በመድገም ቁልቁል መዝቀጥ እንደሆነ መተማመን ይኖርብናል፡፡ ግባችን ኢትዮጵያን እያደሱ ወደፊት ማራመድ እስከሆነ ዘንዳ፣ የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን የመፍጠሪያው መንገድ ላይ ብቻ ማተኮር ብቸኛው መፍትሄ ነው፡፡ ያለፈው ዘመን ሰማዕታትን እየዘከርን፣ ለአጥፊዎቹ ምህረት እያደረግን በይቅርባይነትና በመቻቻል ላይ የምታብበውን ኢትዮጵያን መመስረት የሕዳሴው አብዮት ግብ ሊሆን ይገባል፡፡

 የንቅናቄው ፊት መሪዎች 
 ይህን የለውጥ መንፈስ በፊት መሪነት ማስተባበር የሚችሉ ጠንካራ የሲቪክ ተቋማት በሀገሪቱ ያለመኖራቸው ጉዳይ፣ ለሂደቱ መፍጠን የግድ ሌላ አማራጭ እንድንፈልግ ያስገድደናል፡፡ በርግጥ አንዳንድ ወገኖች ለእንዲህ አይነቱ ጊዜ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መጠቀምን ይመክራሉ፡፡ ይህ ግን አደገኛና ያልተጠበቀ ክስረት ሊያስከትል የሚችል ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ድርጅቶቹ የየራሳቸው የተለያየ ዓላማ አንግበው የሚታገሉ በመሆኑ ከተሳታፊነት አልፈው በመሪነት መምጣታቸው፣ ሁነቱን ከሁሉን አሳታፊነት ወደ ቡድንነት፤ ከዲሞክራሲያዊ ሽግግር ወደ ሥልጣን ነጠቃነት (መፈንቅለ መንግስት) የመቀየር አደገኛ ክስተት ውስጥ ሊያስገባው ይችላል፡፡ ይህ አካሄድ በሌሎች ሀገራት ለከሸፉ አብዮቶች በማሳያነት መጠቀሱንም ታሳቢ በማድረግ፣ ለእኛ ችግር መፍትሔውን አዲስ (ከዚህ ቀደም ያልተሞከረ) አማራጭን ከራሳችን ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር መፈለግ ላይ ማተኮሩ ይበጃል፡፡ በግሌም ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ግዴታ ለመሸከም የተሻሉ ናቸው ብዬ የማስበው ዩንቨርስቲዎቻችንን ነው፡፡ በመላ ሀገሪቱ በተመሳሳይ ወቅት መጀመር የሚኖርበትን የሕዳሴ አብዮት፣ ሁሉም መንግስታዊ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙበትን ከተሞች ጨምሮ አጎራባች አካባቢዎችን ለማስተባበር ኃላፊነት የሚወስዱበት መንገድን ማማቻቸቱ የሚሳካበትን ስልት ከወዲሁ መቀየስ የሚቻል ይመስለኛል፡፡ ርግጥ ነው በዛሬው እውነታ ላይ ሆነን በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የገዢው ፓርቲ የፖለቲካ መናኸሪያ የመሆናቸውን ነገር ግምት ውስጥ አስገብተን ስናምሰለስለው፣ ሁነቶቹ አልጋ በአልጋ ሊሆኑ እንደማይችሉ ከማንም የተሰወረ አይሆንም፡፡ ግና፣ በየተቋማቱ የየትኛውም ፓርቲ አባል ያልሆኑ ለውጥ አራማጅ መምህራንና ተማሪዎች በራስ ተነሳሽነት በመሰባሰብ የማስተባበሩን ኃላፊነት ተረክበው ከፊት መስመር እንዲሰለፉ የማንቃትና ማብቃት ሥራ ቢሰራ፣ አንድም እዚህ ግባ የሚባል ተግዳሮት ባለመኖሩ ሂደቱን ለማፋጠን ይጠቅማል፤ ሁለትም ከንቅናቄው ስፋት አኳያ ለከበደ መስዋዕትነት የመዳረጉ አጋጣሚ እጅግ የጠበበ በመሆኑ ግንባር ቀደም ተሰላፊ ደፋሮችን ማግኘት አዳጋች አያደርገውም፡፡ ይህ ዕቅድ የሚሳካ ከሆነ ደግሞ ዩኒቨርስቲዎቹ በዕኩል ውክልና የጋራ ማዕከል (አዲስ አበባ ለዚህ አመቺ ሊሆን ይችላል) አቋቁመው አብዮቱን በሀገርና ሕዝብ ጥቅም አስተሳስረው መምራት እንደሚኖርባቸው እንደማይዘነጉት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ 

 የአብዮቱ የመጀመሪያ ጥያቄዎች
 ሕዝባዊ ንቅናቄው በሚገባ ተጠናክሮ ከቀጠለ በኋላ መንግስት እጁን ተጠምዝዞ እንዲተገብራቸው መነሳት ያለባቸው ቀዳሚ ጥያቄዎች (ለለውጡ መደላድል የሚሆኑት) የሚከተሉት ቢሆኑ መልካም ነው፡- በመላ ሀገሪቱ ባሉ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ የፖለቲካ፣ የሕሊና እና የሀይማኖት እስረኞችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት፤ በውጪ ሀገር ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች እና የመብት ተሟጋቾች ያለልዩነት ወደ ሀገር ቤት ገብተው በነፃ እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የወጡ አፋኝ ሕጎችን መሰረዝ፤ በሀገሪቱ የመንግስት ምሥረታ ላይ የአፈና መዋቅር ሆኖ የሚያገለግለውን ምርጫ ቦርድ አፍርሶ አብዛሃ ኢትዮጵያዊን ሊያሳምን በሚችል ገፅ እንደገና ማዋቀር፤ ለዴሞክራሲ ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ተቋማትን ነፃ ማድረግ፤ የብዙሃን (የመንግስት) ሚዲያን እውነተኛ የሕዝብ ልሳን የሚሆኑበትን አሰራር መዘርጋት፤ መከላከያ ሰራዊቱ፣ የደህንነት ሰራተኛው እና የፖሊስ አባላት በነቢብ ሳይሆን በገቢር ተጠሪነታቸውን ለሕገ-መንግስቱ ማድረግ… ሲሆን፤ እነዚህ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላ በ2007 ዓ.ም. የሚካሄደውን ምርጫ ለተጨማሪ አንድ አመት በማራዘም፤ ለሁሉም ተወዳዳሪዎች (ለነባሮቹም ሆነ አዲስ ለሚደራጁት) መድረኩን ክፍት አድርጐ የሕዳሴውን አብዮት ለውጥ መተግበር ይቻላል ብዬ አምናለሁ፡፡ እዚህ ጋ መዘንጋት የሌለበት ዋነኛው ጉዳይ አብዮቱ በራሱ በገዥው-ፓርቲ ውስጥ ያሉ በፖለቲካ ቀኖናዊነት ያልተጠለፉና ሀገራዊ ለውጥ ፈላጊ የአመራር አባላት ‹የኢህአዴግ መንግስት ወይም ሞት!› የሚሉ ግትር ጓዶቻቸውን አግልለው፣ ይህንን ኃላፊነት እንዲወስዱ ጫና ማድረግ ላይ የሚያተኩር እንጂ፤ በደፈናው ግንባሩን በጠላትነት ፈርጆ የሚያሳድድ አለመሆኑን ግንዛቤ መውስድ ያስፈልጋል፡፡ የሕዳሴው አብዮታችን የ‹ጊሎትን› ማሽን የማይታጠቅና ልጆቹንም የማይበላ፤ በአጥፍቶ መጥፋት ጨዋታ ሕግ የማይመራ መሆኑን ማስረገጥ ቀዳሚው ተግባር ይሆናል፡፡ ጎን ለጎንም የለውጡን (የጥያቄዎቹን) መፈፀም የሚከታተል ከንቅናቄው አስተባባሪዎች፣ ከንግዱ ማሕበረሰብ፣ ከኃይማኖት ተቋማት፣ ከሲቪክ ማሕበራት፣ ከልሂቃኑ እና ከሀገር ሽማግሌዎች መካከል በተወጣጡ ግለሰቦች የጋራ ምክር ቤት አዋቅሮ ቁጥጥር ማድረግ የሚቻልበትን አሰራር መቀየሱ ሌላኛው ጠቃሚ ክዋኔ ነው፡፡ ይህ መንገድ በድህረ-ኢህአዴጓ ኢትዮጵያችን ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ምስቅልቅሎሽ ቦታ እንዳይኖራቸው የመታደግ አቅምንም ለመገንባት ማስቻሉ መዘንጋት የለበትም፡፡

 የተባረከችዋ ቀን መቼ ትሆን? 
 ይህን መሰል የለውጥ ጥያቄ ማቅረቡ ሥርዓቱ ከሃያ ሶስት ዓመት በላይ ከመቆየቱ አኳያ የተቻኮለ እንደማይሆን አምናለሁና፤ ከላይ ከተጠቀሱት ዋና ዋና አብዮታዊ ጉዳዮች አንፃር፤ እንዲሁም በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ ‹‹ልጄ ፋኖ ተሰማራ እንድትል አልፈልግም›› እንዳለው ሁሉ፤ ህወሓት የታሪካችን የመጨረሻው ‹‹ነፃ አውጪ›› ድርጅት ይሆን ዘንድ የሚታወጅበት ዕለትን ከወዲሁ መወሰኑ ላይ ከተስማማን፣ የ2007ቱ ወርሃ መስከረም በሁለት ጉዳዮች ቢመረጥ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ የመጀመሪያው በቀጣዩ ዓመት የሚደረገውን አምስተኛ ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫን የማራዘሙ አስፈላጊነት ከሕዝባዊ ጥያቄው መካከል ግንባር-ቀደም በመሆኑ ለአገዛዙ በቂ የጥሞና ጊዜ መስጠት የማስቻሉ ጠቀሜታ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የአዲስ ዓመት ጅማሮ ከመሆኑ አኳያ ባሕላዊም ሆነ ስነ-ልቦናዊ መነቃቃት የመፍጠር አቅሙ የራሱ በጎ አበርክቶ ይኖረዋል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡

 ከሞላ ጎደል ለሶስት ሳምንታት ያህል የተነጋገርንባቸው እነዚህ ታላላቅ አጀንዳዎች እውን ይሆኑ ዘንድ ቀጠሮውን በልቦናችን ይዘን፣ ራስን በውስጥ ዝግጅት ማሰናዳቱ ለነገ የማይተው የቤት ስራችን መሆኑንም ጨምሮ መረዳት ያሻል፤ በዚህም የሕዳሴያችን ንቅናቄ እንደ ቀዳሚዎቹ ሁለት አብዮቶች አዲስ መዘዝ፣ ሳይሆን አዲስ ተስፋ እንዲያመጣ እናስችላለን ብዬ አስባለሁ፡፡ በመጨረሻም ያቺ ትንሳኤ አብሳሪ ዕለት በኢትዮጵያችን ምድር ከቶም ቢሆን አቻ የላትምና፣ በአያሌ ናፍቆት ስለመጠበቋ ዛሬ ላይ እንዲህ መመስከሩ ከምኞት የተሻገረ መሆኑን አስረግጬ ብናገር ማጋነን አይሆንም፡፡

 ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

fredag 6. juni 2014

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ… አለቃ ጸጋዬ በርሄ ሰክሮ የሰው ሚስት ይዤ ካላደርኩ በማለቱ በቡጢ ተዘረረ

June 6/2014
ማለቂያ የሌለው የወያኔዎች ጉድ …. የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆነው አለቃ ጸጋዬ በርሄ ሰክሮ የሰው ሚስት ይዤ ካላደርኩ በማለቱ በቡጢ ተዘረረ።
አለቃ ጸጋዬ በርሄ በሴሰኝነታቸው የመጣ በአውስትራሊያ በቡጢ ተደብድበዋል።
“ወደዳችሁም ጠላችሁም ሁሉም አድፍጦ ሊበቀላችሁ እየጠበቀ ነው። ” በኬንዊክ የሚኖሩ የትግራይ ልጆች
(በምንሊክ ሳልሳዊ)
በምእራብ አውስትራሊያ ኬንዊክ ግዛት በሚገኘው የትግራይ ተወላጆች ኮሚኒቲ ማእከል ግንቦት ሃያን በማስመልከት በተድረገ ዝግጅት ላይ ለመታደም የዘመቱት የወያኔ ባለስልጣናት በገዛ ወዳጆቻቸው ተዋርደው ተመልሰዋል። በፖለቲካው መስክም ይሁን በሴሰኝነታቸው እድል ያልሰመረላቸው የወያኔ ባለስልጣናት አብሯቸው ከተጓዘው አንዱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆነው አለቃ ጸጋዬ በርሄ ሰክሮ የሰው ሚስት ይዤ ካላደርኩ በማለት ከፕሮቶኮል ውጪ በመንቀሳቀሱ የራያው ተወላጅ አቶ ተከስተ በትደጋጋሚ ለ4 ጊዜ ቡጢ ሲያቀምሳቸው በክፍተኛ ደረጃ በማእከሉ ውስጥ ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር።
ጸጋየ በርኸ
ጸጋየ በርኸ
ሁኔታውን ለማረጋጋት ቢሞከርም ከሌሎች የጸጋዬ ባለሟሎች ጋር ግብግብ በመያያዝ .. እኔ ወዲ ራያ በማለት አቶ ተከስተ በጸጋዬ እና ተከታዮቹ ላይ ጉዳት አድርሰዋል። በትግራይ የራያ ተወላጅ እና የቀድሞ የሕወሃት አባል የሆኑት አቶ ተከስተ ባለቤታቸው ይዘው በዝግጅቱ ላይ የመጡ ቢሆንም በወቅቱ በነበረው ክፍተኛ የመጠጥ ብዛት ከልክ በላይ የጠጡት አለቃ ጸጋዬ በቆንጆ የራያ ልብስ ደምቃ በሹሩባ ያጌጠችው የአቶ ተከስተ ሚስት አይናቸው ገብታ እንዲያመጡላቸው ቢያዙም የሰው ሚስት እንደሆነችና ባለቤቷ አብሮ እንዳለ ቢነገራቸውም ሊሰሙ ባለመቻላቸው ያለችበት ቦታ ድረስ በስካር መንፈስ ሰተት ብለው ሲሄዱ ነገሩ የገባው የቀድሞ የሕወሓት አባል አቶ ተከስተ በቡጢ ተቀብሏቸው መሬት ላይ ዘርግፏቸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምእራብ አውስትራሊያ ኬንዊኪ የሚገኘው የትግራይ ኮሚኒቲ ለሁለት ተከፍሎ የወያኔ መሪዎችን በማፋጠጥ ክባድ የፖለቲካ ኪሳራ እንደተፈጠረ ወዳጆቻችን ገልጸውልናል። ሕወሓት በኢትዮጵያ የሚያደርገው ድርጊት ለነገ ልጆቻችን ቂም ማትረፍ ነው ወደዳችሁም ጠላችሁን ሕዝቡ ተለያየ ብላችሁ እያሰበችሁ ከሆነ አትሳሳቱ ሁሉ አድፍጦ እየጠበቀ ነው ድንገት የፈነዳ እለት ይበቀላቹሃል። በቀሉም ለትግራይ ተወላጆች ይተርፋል መፍትሄ አምጡ በማለት የመከሩ ሲሆን በሌላው ወገን ደሞ አማራው አድብቷል የአማራው ጅብ እንዳይበላችሁ እናንተ እርስ በርስ እየተባላችሁ ነው አታናቆሩ ሲሉ መካሪዎችን ሮሮ አስምተዋል።
ከእራት በፊት በቤተክርስቲያናት መካከል የተከፋፈለውን አካል ለማስታረቅ የሞከሩት የወያኔ ባለስልጣናት በፍጹም ለማስማማት ባለመቻላቸው በአቡነ ማትያስ ስም ለማስፈራራት ቢሞክሩም መሳቂያ ሆነዋል። የተዋህዶ ቤትክርስቲያን በመንደርተኖች የተክፈለች ሲሆን የአድዋ እና የተንቤን ተብለው የሚጠሩት ቤተክርስቲያኖች ሲኖሩ በኮሚኒቲ ማእከሉ ውስጥ ያለውን ከሕወሓት ቢሮ ጋር አብሮ የተጣበቀውን አድዋዎች ሲያስተዳድሩት ተንቤኖች ደሞ የራሳቸውን ቤተክርስቲያን በመመስረት ተገንጥለው ወተዋል። ይህንን ግኡዳይ ለመፍታት እና ወደ አንድነት ለማምጣት በቦትው የተገኙት የፖለቲካ ባለስልጣናት አለቃ ጸጋዬ እና የአባይ ወልዱ ባለቤት እንዳልተሳካላቸው ሲታወቅ ከተንቤን ተወላጆች ጠንካራ ሂስ ቀርቦባቸዋል።
# ምንሊክሳልሳዊ