lørdag 31. januar 2015

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

ጥር 21/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ የምርጫ ቦርድ የሚባል ተቋም ያለበትን ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህ ደረጃ እንዲዋራድ ከጀርባ ሆኖ አመራር የሚሰጠው ገዢ ፓርቲም ሆነ መንግሰት በዚያው ልክ የሚገባቸውን የተዋረደ ደረጃ የያዙበት ዕለት ነው ብለን እናምናለን፡፡ አንድነት ፓርቲ አንድም የህግ ጥሰት ሳይፈፅም የሚያደርጋቸውን ሁሉ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና በሀገሪቱ ህግ እየፈፀመ ባለበት ሁኔታ በህግ ሽፋን የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ፋና ሬዲዮ፣ የመንግሰት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር የከፈቱት ዘመቻ የመጨረሻ የሆነውን አንድም ህጋዊ መሰረት የሌለውን ህገወጥ ውሳኔ በአንድነት ፓርቲ እና አባላት ላይ አሰተላልፈዋል፡፡UDJ/Andinet party logo
ገዢው ፓርቲና መንግሰት በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲነበብ ያደረጉት የፖለቲካ ውሳኔ በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ከወረቀት አልፎ በተግባር እንዳይታይ ግብዓት መሬቱን ፈፅመዋል፡፡ በዚህ ፀያፍ ተግባር ከፊትም ሆነ ከጀርባ ሆነው የተሳተፉ ግለሰቦችም ሆኖ ተቋማት በታሪክ ተገቢው የውርደት ቦታ እንደሚይዙ እምነታችን ነው፡፡ ይህ ህገወጥ አካሄድ ህጋዊ መሰመር እንዲከተል የበኩላቸሁን ድርሻ የተወጣችሁ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች በሀገር ውሰጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ ሁሉ በተለይ በገዢው ፓርቲ እኩይ ሴራ በሀስት ተወንጅላችሁ በወህኒ ቤት ለምትማቅቁ ታጋዮች ታሪካችሁ በወርቅ ቀለም ተፅፎዋል፡፡ በቀጣይም ያለምንም መዘናጋት እና ተሰፋ መቁረጥ በምናደርገው ሰላማዊ ትግል በሀገራችን ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሰርዓት ትንሳኤ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለንም፡፡
የምርጫ ቦርድ ተብዬው ተቋም በህገወጥ መንገድ ለሆዳቸው ባደሩ ጥቂት አንድነት ፓርቲ አባላት እና በአንድነት አባልነት በማይታወቁ የገዢው ፓርቲ ጥርቅሞች ለተደረገ ጠቅላላ ጉባዔ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ማለቱን በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን፣ የአንድነት ፓርቲ አባላት ያነገብነው የነፃነት መንፈስ በምርጫ ቦርድ በሚሰጥ ሰርተፊኬትና ዕውቅና ማዕቀፍ ውስጥ የሚገኝ ስለአልሆነ ለነፃነት የምናደርገውን እልህ አስጨራሽ ትግል የምንቀጥል ሲሆን፤ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የአንድነት መዋቅሮች እና የአንድነት አባላት ለዚህ ህገወጥ ቡድን በግልፅ እውቅና እንዲነሱ እንጠይቃለን፡፡
ፓርቲያችን በመጨረሻ ሰዓት እንኳን ተፈትነው ለወደቁ ተቋማት እድል ለመስጠት ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ወሰኖ እንቅሰቃሴ በማድረግ ላይ ቢሆንም፤ በዛሬው ዕለት ጥር 22/ 2007 ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ የፓርቲያቸን ፅ/ቤት በፖሊስ ተወሮ የፓርቲው ንብረት ያለምን ህጋው ርክክብ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎዋል፡፡ በአሰተዳደር የተሰጠን ውሳኔ በፍርድ ቤት የማሰለወጥ ህጋዊ ሰርዓት እንዳለ ቢታወቅም ህገወጥ አስተዳደራዊ ውሳኔን በፖሊስ ወረራ ለማሰፈፀም የተሄደበት መስመር ገዢው ፓርቲና መንግሰት አሁንም ከጫካ አሰተሳሰብ ያለመውጣቸውን እና የአውራ ፓርቲ ፍልስፍናቸውን በማናለብኝነት ለመተግበር መቁረጣቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ በዚህ ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂው ትእዛዙን ያስተላለፈው ክፍል መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
ሰለሆነም በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣የሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅቶች፣ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ሰርዓት እንዲጎለብት ፍላጎት ያለችሁ ሁሉ ይህን እኩይ ተግባር በማውገዝ ተጨባጭ እርምጃ እንድትወሰዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ድል የህዝብ ነው!!!

tirsdag 27. januar 2015

አቶ ትግስቱ አወሉ በአንድነት የክልል አመራሮች ላይ በስልክ ዛቻ እየፈፀሙ መሆኑ ተገለፀ፡፡


የአንድነት ፓርቲ ሰሞኑን በኢህአዲግና ምርጫ ቦርድ ከፍተኛ ዘመቻ ተከፍቶበት እንደሚገኝ መላው ኢትዮጵያዊ እየተከታተለው ያለ እውነታ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን አንድነት ፓርቲን ለመፈረካከስ ከሚሰሩት ግለሰቦች መካከል አቶ ትግስቱ አወሉ የተባሉና የቀድሞ የአንድነት አባል በአሁኑ ሰዓት እራሳቸውን ፕሬዝደንት አድርገው ከምርጫ ቦርድ ጋር በጋራ በመስራት ላይ ያሉ ግለሰብ በ16/05/2007 ዓ.ም ላደረጉት ህገ-ወጥ ጉባኤ ተልእኳቸውን ለማስፈፀም በየክፍለሀገሩ የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ የጉባኤ አባላትን በስልክና በአካል በመሄድ ለዚህ ህገ-ወጥ አንድነት ፓርቲ ነኝ ባይ ጉባኤ እንዲገኙ በማግባባት፤ከመንግስት ፈሰስ በተደረገላቸው ገንዘብ በመደለል እንዲሁም እንቢ ያሉ ግለሰቦችን ‹‹መንግስት ከኔ ጎን ነው እንቢ ካልክ/ሽ እርምጃ እንወስዳለን፤…..ወዘተ›› ማስፈራሪያ ሲጠቀሙ እንደነበር በየአካባቢው የሚገኙ የአንድነት አባላት ሰሞኑን ሲገልፁ የነበረ ሲሆን ዛሬ በደረሰን መረጃ መሰረት ግለሰቡ በደቡብ ወሎ የአንድነት መዋቅር በሚገኝባቸው ሐይቅ፤ወረባቦ፤ደሴ፤ኮምቦልቻ፤ኩታበር …….የመሳሰሉት ወረዳዎች የሚገኙ የአንድነት የወረዳ አመራሮች ጋር ስልክ በመደወል ከፍተኛ መስፈራራትና ዛቻ የተቀላቀለበት ድርጊት መፈፀማቸውን ከየወረዳዎቹ ያሉ የአንድነት አመራሮች ሪፖርት አድርደዋል፡፡ ግለሰቡ አንድነት ፓርቲ የኔ ነው፤እኔም ነኝ የምመራው፤ በኔ አስተዳደር ስር ሆናችሁ ላለመሳተፍ ከወሰናችሁ፤ በመንግስት በኩል ከፍተኛ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ተደርጓል›› ….ወዘተ የሚል ማስፈራሪያ እንደሚያሰሙ ገልፀዋል፡፡ አባላቶቹ አያይዘውም ‹‹እኛ አንድነት አንድ እንጂ ሁለት አይደለም፤ህጋዊ የሆነው አንድነት ፓርቲ በተገቢው ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ባለበት አግባብ መንግስትና ምርጫ ቦርድ ፓርቲውን ለመበታተን ለሚያደርጉት ዘመቻ ተገዢ አንሆንም፤ሰላማዊ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ አቶ ትግስቱ አወሉ በህጋዊውና በትክክለኛው የአንድነት ፓርቲ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እራሳቸውን እጩ አድርገው አቅርበው በመሳተፍ የራሳቸውን አንድ ድምፅ ብቻ አግኝተው መውደቃቸው የሚታወስ ነው፡

onsdag 21. januar 2015

ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው ውይይት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀውን ይህን ውይይት በርካቶች በአካል በስብሰባው ቦታ ተገኝተው ከተከታተሉት ታዳሚዎች ባሻገር በርካቶች ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በስካይፒ የተከትሉት ሲሆን፤ ፓናሊስቶቹ ባቀረቧቸው ሀሳቦች ላይ ውይይት ተካሂዷል።
ፕሮፌሰር መስፍን  ሰማያዊ ፓርቱ እና በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ኮሚቴ በመተባበር ያዘጋጁትን ውይይት ሲከፍቱ
ሁላችንም ስንለወጥ ነው ለውጥ የሚመጣው ብለዋል  ፕሮፌሰር መስፍን፤ ከጣሊያን ጊዜ አንስቶ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ባንዳው፣ፖሊሱ፣ባለስልጣኑ ሁሉ በመሸጦነት ማለፋቸውን በማውሳት፤ አንድ ትውልድ ይህን የመሸጦነት ባህል እየተባበረ ከሄደ ለውጥ እንደማይመጣ በአንጽንኦት ተናግረዋል።
ተከታዩ ተናጋሪ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ደግሞ፦‹ለህወሓቶች ፖለቲካ ማለት ወዳጅና ጠላት የሚለይበትና ፍልሚያ የሚደረግበት ነው ፡፡ አንድ የናዚ ሰውም ፦ፖለቲካ ማለት ወዳጅና ጠላት የሚለይበት ሜዳ ነው>> ነው የሚለው፡፡ብለዋል።
ህወሀቶች ያለ ጠላት መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ያሉት ዶክተር ዳኛቸው፤ ድህነትንም ጠላት ብለውታል፡፡ ሲጀመር እኛ እና እነሱ ይባልና- ጠላትና ወዳጅ ወደሚለው ያድጋል፡፡›› ብለዋል። ሁላችንም በሀገራችን የባለቤትነት መብት ቢገባንም የሀገሪቱ ፖለቲካ ዝግ ሆኗል ያሉት ዶክተር ዳኛቸው፤ ውድድር በሌለበት ቦታ ፍትሐዊ ምርጫ ማድረግ እንደማይቻል ገልፀዋል።
የአዲሲቷ ኢትዮጰያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው፤ በጎሳና በዘር ተከፋፈግለናል፤ ሀገራችንን ለመቀየር ከፈለግን ለውጡ ከራሳችን መጀመር አለበት ብለዋል።
እኛ ለሀገራችን ዋጋ ካልከፈልን፤ማንም ለኢትዮጰያ ዋጋ ሊከፍልልን አይችልም ብለዋል-አቶ ኦባንግ።
የዞን 9 ጦማርያን አባል የሆነችው ሶልያና ሽመልስ በበኩሏ ትንሽ የሚመስሉ ጥረቶችን ማድነቅ እንደሚያስፈልግ በመጥቀስ፤ ቀደም ሲል ጠቀሜታው ብዙም ግምት ያልተሰጠውንና በአሁኑ ወቅት ተጽእኖ እየፈጠረ ያለውን በኢንተርኔት መረጃ የመለዋወጥን እና የመጻፍን ጉዳይ በተደራጀ መልኩ መጠቀም እንደሚያስፈልግ መክራለች።
በምርጫ 97 ወቅት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር የነበሩት ዳኛ ፍሬህይወት ሳሙኤል በበኩላቸው ኢትዮጰያ ውስጥ የህግ የበላይነት እንደሌለ ምሳሌዎችን በመጥቀስ ተናግረዋል።
ኢትዮጰያ ውስጥ ወደ እስር ቤት የተወረወሩት አንድም በፖለቲካ የተሳተፉ አለያም ድሆች ናቸው ያሉት ዳኛ ፍሬህይወት፤ “የሀብታም ክስ ከፖሊስ አልፎ ፍርድ ቤት አይደርስም ብለዋል።
“ለውጥ ይመጣል፡፡ ለውጥ ይሸተኛል”በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ናቸው።
ለውጡ እንደስከዛሬው እንዳይከሽፍ ግን ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ቡድኖችበራሳችን ላይ አብዮት ማምጣት አለብን፡፡ያሉት ኢንጂነር ይልቃል  ከእስካሁኑ የተለየ ለውጥ እንዲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ማድረግ አለብን›› ብለዋል።

ያለ ነጻ ሚዲያ – ምርጫ ወይስ ቁማር? የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሰሞኑን ሥጋቱን ይፋ ሊያደርግ ነው!

* ኢህአዴግ አሸነፈ፤ ፋና መሰከረ!

ምርጫ ያለ ነጻ ሚዲያ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተመልካች (Human Rights Watch) በያዝነው ሳምንት ማገባደጃ አካባቢ በኢትዮጵያ የሚዲያ ነጻነትን አስመልክቶ አጠቃላይ ዘገባ እንደሚያወጣ ተሰማ፡፡
ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ መረጃውን ያቀረቡና ከዘገባው ጋር ተዛማጅነት ክፍሎች እንደተናገሩት የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ይህንን ዘገባ ያጠናቀረው በተጨባጭ ከሚዲያ ጋር በተያያዘ ሰለባ የሆኑትን በሚዲያው መስክ የተሰማሩትን በማነጋገርና የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ በመሰብሰብ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዘገባው ከዚህ በፊት ከወጡት ዘገባዎች ለየት ባለ መልኩ በፕሬስ ሚዲያው ላይ የተሰማሩትን ክፍሎች በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡ በተለምዶው በጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው አፈና በብዙ መልኩ የሚነገር ሲሆን በዚህ ዘገባ ግን ኢህአዴግ በአሳታሚነት፣ በአከፋፋይነት፣ በአታሚነት፣ በሻጭነት (አዟሪነት)፣ ወዘተ የተሰማሩትን እንዴት ስልታዊ በሆነ መልኩ እንደሚያዳክም፣ እንደሚያፍን፣ እንደሚያሰቃይና ባጠቃላይ ከሜዳው እንደሚያስወግድ የሚያስረዳ እንደሚሆን ጎልጉል ካገኘው መረጃ ለመገመት ተችሏል፡፡
በመጪው ግንቦት ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በማያያዝ ይወጣል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ዘገባ በተለይ የኢህአዴግን ቋት የሚሞሉ ለጋሽ አገራት፣ ዓለምአቀፍ የፍትሕ አካላት፣ የሲቪክ ማኅበረሰቦች፣ ወዘተ ከወዲሁ ግንዛቤ ይዘው ኢህአዴግ አደርገዋለሁ ለሚለው “ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ” ምርጫ ያለ ነጻ ሚዲያ ተሳትፎ እንዴት ውጤት አልባ እንደሆነ የሚያስረዳና ጠለቅ ያለ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
elec tionበዘንድሮው ምርጫ ባልተጠበቀና ለመቀበል በሚያስቸግር መልኩ የአውሮጳ ኅብረት “በጀት የለም” በሚል ምርጫውን አልታዘብምምብሏል፡፡ በይፋ የተሰጠው ምክንያት ይህ ቢሆንም ጉዳዩ የበጀት ሳይሆን “ኢህአዴግ ከኢህአዴግ ጋር የሚያደርገውን የ99.6 በመቶ የምርጫ ውጤት መታዘብ በራሱ ያስታዝባል” በሚል ነው ኅብረቱ ምርጫ መታዘቡን በቅድሚያ ትዝብት የተወው በማለት የተሳለቁ መኖራቸው ተሰምቷል፡፡ ሆኖም ግን ኢህአዴግ በበኩሉ “ባትታዘቡ ምን ገደደኝ” በማለት ኅብረቱ ምርጫውን ለመታዘብ አለመፈለጉን በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ትዝብት አልፎታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዚህ ስለ ሚዲያ ነጻነት በሚያትተው አዲስ ዘገባና በኅብረቱ ውሳኔ ዙሪያ ኢህአዴግ “ዓለምአቀፋዊ ሽልማት ባገኙ የዘርፉ ባለሙያዎቹ” ተጠቅሞ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት ባለ “ነጻነት” የሚዲያ ሥራ እንደሚሠሩ በነዚሁ “ሚዲያዎች” ምላሽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡
የአውሮጳ ኅብረትን “ምርጫ አልታዘብም” የማለት ውሳኔን በተመለከተ ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ለጎልጉል እንደተናገሩት ኅብረቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከበጀት እጥረት ሳይሆን እየከረረና እየመረረ የመጣውን የኢህአዴግን አምባገነንነት፣ በቀደሙት “ምርጫዎች” የተከሰተውን ዓይንአውጣ ቅጥፈት እንዲሁም የኢህአዴግን የሞራል ዝቅጠት በማገናዘብና ከተሞክሮ በመነሳት የግንቦቱን ምርጫ አስቀድሞ በማጣጣል ዋጋ እንደማይሰጠው ከመናገር አኳያ ነው በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ይህንን አስደንጋጭ የአውሮጳ ኅብረት ማዕቀብ ተከትሎ የሰብዓዊ መብት ተመልካቹ ድርጅት በማስረጃ የተደገፈ ዘገባ ከምርጫው በፊት አስቀድሞ ማውጣቱ ታስቦና ታቅዶ የተደረገ ብቻ ሳይሆን የአውሮጳ ኅብረትን እነማን ይከተሉታል የሚል ጥያቄ አስነስቷል፡፡
በግንቦት 2007 አካሂደዋለሁ ለሚለው ምርጫ ኢህአዴግ አጋጣሚውን ተጠቅሞ የውጭ ምንዛሬ ኮሮጆውን እንዲሞሉለት ከአውሮጳ ኅብረት በተጨማሪ ሌሎች አገራትን በተናጠል መለመኑ ይታወቃል፡፡
source (http://www.goolgule.com

tirsdag 20. januar 2015

 


 

ኢትዮጰያ ውስጥ ያለው ችግር የዘር ፉክክር ነው>>ሲሉ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ተናገሩ።

ፕሮፌሰር መስፍን ይህን ያሉት ሰማያዊ ፓርቱ እና በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ኮሚቴ በመተባበር ያዘጋጁትን ውይይት ሲከፍቱ ነው።
<<ሁላችንም ስንለወጥ ነው ለውጥ የሚመጣው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ከጣሊያን ጊዜ አንስቶ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ባንዳው፣ፖሊሱ፣ባለስልጣኑ ሁሉ በመሸጦነት ማለፋቸውን በማውሳት፤ አንድ ትውልድ ይህን የመሸጦነት ባህል እየተባበረ ከሄደ ለውጥ እንደማይመጣ በአንጽንኦት ተናግረዋል።
ተከታዩ ተናጋሪ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ደግሞ፦‹ለህወሓቶች ፖለቲካ ማለት ወዳጅና ጠላት የሚለይበትና ፍልሚያ የሚደረግበት ነው ፡፡ አንድ የናዚ ሰውም ፦<<ፖለቲካ ማለት ወዳጅና ጠላት የሚለይበት ሜዳ ነው>> ነው የሚለው፡፡>>ብለዋል።
<<ህወሀቶች ያለ ጠላት መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡>>ያሉት ዶክተር ዳኛቸው፤ <<ድህነትንም ጠላት ብለውታል፡፡

ሲጀመር እኛ እና እነሱ ይባልና- ጠላትና ወዳጅ ወደሚለው ያድጋል፡፡›› ብለዋል። ሁላችንም በሀገራችን የባለቤትነት መብት ቢገባንም የሀገሪቱ ፖለቲካ ዝግ ሆኗል ያሉት ዶክተር ዳኛቸው፤ <<ውድድር በሌለበት ቦታ ፍትሐዊ ምርጫ ማድረግ እንደማይቻል ገልፀዋል።
የአዲሲቷ ኢትዮጰያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው፤ <<በጎሳና በዘር ተከፋፈግለናል፤ ሀገራችንን ለመቀየር ከፈለግን ለውጡ ከራሳችን መጀመር አለበት ብለዋል።
<<እኛ ለሀገራችን ዋጋ ካልከፈልን፤ማንም ለኢትዮጰያ ዋጋ ሊከፍልልን አይችልም>>ብለዋል-አቶ ኦባንግ።
የዞን 9 ጦማርያን አባል የሆነችው ሶልያና ሽመልስ በበኩሏ ትንሽ የሚመስሉ ጥረቶችን ማድነቅ እንደሚያስፈልግ በመጥቀስ፤ ቀደም ሲል ጠቀሜታው ብዙም ግምት ያልተሰጠውንና በአሁኑ ወቅት ተጽእኖ እየፈጠረ ያለውን በኢንተርኔት መረጃ የመለዋወጥን  እና የመጻፍን ጉዳይ በተደራጀ መልኩ መጠቀም እንደሚያስፈልግ መክራለች።
በምርጫ 97 ወቅት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር የነበሩት ዳኛ ፍሬህይወት ሳሙኤል በበኩላቸው ኢትዮጰያ ውስጥ የህግ የበላይነት እንደሌለ ምሳሌዎችን በመጥቀስ ተናግረዋል።
ኢትዮጰያ ውስጥ ወደ እስር ቤት የተወረወሩት አንድም በፖለቲካ የተሳተፉ አለያም ድሆች ናቸው ያሉት ዳኛ ፍሬህይወት፤ “የሀብታም ክስ ከፖሊስ አልፎ ፍርድ ቤት አይደርስም>> ብለዋል።
“ለውጥ ይመጣል፡፡ ለውጥ ይሸተኛል”በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ናቸው።
<< ለውጡ እንደስከዛሬው እንዳይከሽፍ ግን ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ቡድኖችበራሳችን ላይ አብዮት ማምጣት አለብን፡፡>>ያሉት ኢንጂነር ይልቃል << ከእስካሁኑ የተለየ ለውጥ እንዲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ማድረግ አለብን›› ብለዋል።
ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀውን ይህን ውይይት በርካቶች  በአካል በስብሰባው ቦታ ተገኝተው ከተከታተሉት ታዳሚዎች ባሻገር በርካቶች ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በስካይፒ የተከትሉት ሲሆን፤ ፓናሊስቶቹ ባቀረቧቸው ሀሳቦች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

lørdag 3. januar 2015

ቀኑ ሲቃረብ መውጫው ይጠባል!

ኢትዮጵያ ሀገራችን በታሪኳ ከአስከፊ የፈተና አረንቋ ውስጥ ተገፍታ የገባችበት ዘመን ቢኖር ይህ የምንገኝበት ዘመነ ወያኔ ብቻ ነው፡፡ ዜጎችዋ ከፋሽስት ኢጣልያ በከፋ ሁኔታ ይህ ቀረሽ የማይባል የመከራ መአት የወረደባቸውና እየወረ ደባ ቸው የሚገኝበት ዘመን ቢኖር ይህ የምንገኝበት ዘመን ወያኔ ብቻ ነው፡፡ እስር ቤቶች ሞልተው ተጨማሪ እስር ቤቶች መገ ንባት ከልማት ተቆጥሮ የሚፎከርበት ዘመን ቢኖር ይኸው ዘመነ ወያኔ ብቻ ነው፡፡ የሀገሪቱ ብሄራዊ ባንክ ንብረት የሆ ነው ወርቅ በባሌስትራ ለውጦ እስከ መዝረፍ የደረሰ በጠራራ ፀሀይ የህ ዝብና የሀገር ሀብት ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ በጥቂቶች የሚዘረፍበት ዘመን ቢኖር የምንገኝበት ዘመነ ወያኔ ብቻ ነው፡፡ የጅምላ እስር፤ የጅምላ ግድያ፤ የጅምላ ስደትና መፈናቀል፤ ይበልጡንም በታሪካችን ታይቶ በማያውቅ መልኩ ለሞት፤ ለእስር፤ ለመፈናቀልና ለስደ ት ምክንያቱ የተገኘንበት ዘውግ የሆነበት ዘረኛ ዘመን ቢኖር ይኸው ዘመነ ወያኔ ብቻ ነው፡፡
ባጠቃላይ ላለፉት 23 አመታት ወያኔ ማድረግ የሚችለውን አስከፊ ነገር ሁሉ በሀገርና በህዝብ ላይ ሲፈፅም ቆይቷል፡፡ ዛሬ ከ23 አመ ታት በዃላ ሀገራችንና ህዝባችን ያልተዘፈቁበት የችግር ማጥ፤ ያልደረሰ የሀብትና የሰብአዊ ውድመት፤ ያልተፈፀመ የግፍና የሰቆቃ አይነት የለም፡፡ ወያኔ ይህን ሁሉ ሲፈፅም መሳሪያ አድርጎ ከተጠቀመባቸው ተቋማት ውስጥ ዋነኛዎቹ የመከላከያ፤ ፍርድ ቤትና የፖሊስና የደህንነት መሆናቸው ጥያቄ የለውም፡፡ የእነዚህ ተቋማት አባላት ከወያኔ ጥቃት ሰለባ ከመሆን ባይተርፉም የዚህን ወንጀለኛና ዘረኛ ቡድን እድሜ በአንድ ቀን በመጨመሩ ስራ ላይ ከፍተኛውን ድርሻ እንደያዙ ዛሬም መገኘታቸው አሌ የማይባል እውነት ነው፡፡ይህ ሲባል ግን በሀገርና በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ክህደት፤ ግፍና ሰቆቃ የሚያማቸው፤ መከራው መረራቸው፤ ብሶቱ ብሶታቸው የሆኑ አባላት የሉም ማለት እንዳልሆነ፤ ይልቁንም አብዛኛዎቹ የዚህ ስሌት ተካፋይ ስለመሆናቸው የሚጠራጠር የለም፡፡
ነገር ግን ከህዝብ አብራክ በወጡና ልጆቹን ሳይመግብ በከፈለው ታክስ በተደራጀ የመከላከያ፤ የፖሊስና የደህንነት ተቋማት ውስጥ የምትገኙ አብዛኛውና የግፉ ቀማሽ የሆናችሁ አባላት ዛሬ የምትገኙበት ሁኔታ እንደ አለፉት 23 አመታት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ፤ ከዛሬ ነገ የተሻለን ነገር ተስፋ በማድረግ፤ በግርግሩ ፍርፋሪ ሊወድቅልኝ ይችላል ከሚል ራስ ወዳድነት…… ወዘተ በመሳሰሉ በርካታ ምክንያቶች ለፍትህ፤ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ብሎም ለኢትዮጵያችን ቀጣይ ህልውና በሚደረጉ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በመቆም ብሎም የጥቂት ዘረ ኛች ስልጣንና ምቾት እድሜ ለማራዘም የተጓዛችሁበት መንገድ ብዙም ማስኬድ ከማያስችልበት፤ ይልቁንም ዛሬ ከሁለት መንታ መንገድ የ ደረሳችሁበትና ቆም ብሎም ማየትና ማገናዘብን ከሚጠይቅ ወቅት ላይ ትገኛላችሁ፡፡ አንዱ በዘረኝነት በትር እየተወቀጡ የወያኔ ሎሌ ሆኖ መቀጠል፤ ሌላው ከህዝብ አብራክ የተገኛችሁ ናችሁና ከህዝብ ወገን ተቀላቅሎ ሀገርን፤ ወገንንና ራስን ነፃ ለማውጣት መነሳት..
ለመከላከያ ሰራዊት፦ ላለፉት 23 አመታት ከጠመንጃ ተሸካሚነት ላለፈ ለማይፈልጉህ፤ ለአንተነትህ መለኪያው እውቀትህ፤ ችሎታ ህና አገልግሎትህ ሳይሆን የተገኘህበት ዘውግ መስፈሪያህ ለሆነበት ዘረኛ ስርአት፤ መቀየሪያ መለያ ልብስ ተነፍጎህ ቀዳዳ እየጣፍክ የልጆችህን የረሀብ ልቅሶ እያዳመጥክ በአንተ ትከሻ በዘረፉት ሀብት የገነቧቸውን ህንፃዎች ጠባቂ ላደረጉህ፤ ፍትህ ነፃነት ሲል በተራበ አንጀታቸውና በደ ከመ ድምፃቸው በጠየቁ ወገኖችህ ላይ ይህ ቀረ የማይባል ግፍ ሲያ ስፈፅምህ ለቆየው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ዛሬም ተገቢውን ምላሽ የመስጠት እድሉ አለህ፡፡አልረፈደምና ተጠቀምበት!!!
የፖሊስ ሰራዊት አባላት፤- ፍትህ ላሉ ጥይትን፤ ነፃነት ላሉ የጭካኔ በትርን፤ ሀገሬን ላሉ ከጨለማ ዘብጥያ መወርወርን.. ዋነኛ ተግባርህ በሆነበት በዚህ ዘረኛና በወንጀል የተጨማለቀ ስርአት ውስጥ የቆየህበት ያለፉት 23 አመታት ለአንተም፤ ለቤተሰብህም፤ ለተገኘህበት ህብረ ተሰብ ሆነ ለሀገርህ የፈየደው አንዳች ነገር ያለመኖሩን ይበልጡኑ ከእሳት ወደ እረመጥ ከሆነው የወያኔ ጉዞ ራስህን አውጥተህ ከህዝባዊው ወገን የምትቀላቀልበት የመጨረሻው ሰአት መሆኑን ተገንዝበህ ምርጫህን ከወገንህ አድርግ፡፡ ለአንተም አልረፈደም!!
የደህንነት አባላት፦ ለሀገር ደህንነት ለህዝብ ሰላም ሲባል በህዝብ ሀብት በተደራጀ ተቋም ተጠቅመህ በሀገርህ ላይ ክህደትን፤ በወገ ንህ ላይ ግፍና ሰቆቃን ስትፈፅም መቆየትህ ከወንጀሎች ሁል የከፋ ወንጀል መሆኑን ተገንዝበህ ለፍትህ ለነ ፃነትና ለዲሞክራሲ ሲሉ በተነሱ ወገኖችህ ላይ ስትሰነዝር የቆየኸውን በትር በፍትህ በነፃነትና በዲሞክራሲ ላይ በቆሙት ዘ ረኛ አዛዦችህ ላይ የማሻው ጊዜ አሁን ነው፡፡ ስለ ዚህም ከህዝባዊው ወገን ተቀላቅለህ ህዝባዊ ወገንተኝነትህን የምታሳይበት ብሎም የበደልከውን የምትክስበት ጊዜውም እድሉ አለህና ተጠ ቀምበት፡፡ላንተም አልረፈደም!!
በመጨረሻም ልጇን የምትጠላ እናት፤ ወገኑን የሚገፋ ህዝብ፤ ዜጎቹን የማይቀበል ሀገር የለምና ይህን በአስከፊነቱ ወደር የማይገኝለት የወያኔ ዘረኛ ስርአት ደግፎ ማቆየት ከማይቻልበት ይበልጡንም እንደ ትሪፖሊና ኢያሪኮ የግፈኞች ግንብ በህዝባዊ ሀይል ከሚገረሰስበት ከ መጨረሻዋ ደቂቃ ከመደረሱ በፊት ከእናታችሁ እቅፍ ከወገናችሁ መሀል ግቡ!! ተቀላቀሉ!! ቀኑ ሲቃረብ መውጫው ይጠባልና ጊዜ ሳታጠ ፉ ፈር ቀዳጅ ወንድሞቻችሁን መከተል ብልህነት ነው እንላለን!!!
የኢያሪኮም የጋዳፊም ግንብ ተንዷል፤ የወያኔም ይናዳል!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!