mandag 30. september 2013

የተቃውሞ ፓርቲዎች ሠላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ

udj 5 19
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ከ 33ቱ ፓርቲዎች ጋራ በመሆን ለዛሬ በመስቀል አደባባይ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ክልከላ የአንድነት ጽ/ቤት በሚገኝበት ቀበና መካሄዱ ተገለፀ።
የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ሰልፉን ተከታትሎ ባደረሰን መረጃ መሰረት እጅግ በርካታ ሠላማዊ ሰልፈኞች ሠልፉን ለማከናወን ወዳቀዱበት መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ተከላክሎዋል። ከ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ጋ ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ከ 33ቱ ፓርቲዎች ጋራ በመሆን ለዛሬ በመስቀል አደባባይ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ክልከላ የአንድነት ጽ/ቤት በሚገኝበት ቀበና መካሄዱ ተገለፀ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ሰልፉን ተከታትሎ ባደረሰን መረጃ መሰረት እጅግ በርካታ ሠላማዊ ሰልፈኞች ሠልፉን ለማከናወን ወዳቀዱበት መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ተከላክሎዋል። አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰልፉ ወደ 80,000 የሚጠጉ ሰዎች መሳተፋቸውን የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እንደሚገምቱ ጠቅሷል። የዜና አውታሩ አያይዞም የመንግሥት ቃል አቀባይ ሬድዋን ሁሴን በሰልፉ የተገኙት በጥቂት መቶ የሚቆጠሩ እንደሆኑ መግለፃቸውንም ገልጿል።
Demonstration der äthiopischen Oppositions-Partei am 29.09.2013. zugeliefert von: Lidet Abebe copyright: DW/Y.G. Egziabher
ሰልፈኞቹ የጸረ-ሽብር ሕጉ ይሰረዝ፣ የታሰሩ የኅሊና እስረኞች ይፈቱ፣ የኢሕአዴግ መገለጫው ሙስና ነው፣ የሕዝቡ የመሬት ባለቤትነት ይረጋገጥ፣ መብትን መጠየቅ አሸባሪነት አይደለም፣ ፍትኅ እንፈልጋለን፣ ዲሞክራሲ እንሻለን የሚሉና ሌሎች በርካታ መፈክሮችንም በከፍተኛ ድምፅ ማሰማታቸው ታውቋል።
በሰልፉ ላይ ከቃሊቲ እስር ቤት የተላከው የአንዱዓለም አራጌን ጨምሮ ዝዋይ ከሚገኙ እስረኞች የተላከ መዕልክት በንባብ ቀርቧል። ሠልፉ በአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ንግግር በፓርቲው ጽ/ቤት መጠናቀቁ ታውቋል። (ፎቶና ዜና: DW)

«እዚህ ያላችሁ አብዛኞቻችሁ የልጄቼ ልጆች ልትሆኑ ትችላላችሁ። ተስፋ የማድረግባችሁ ናችሁ» ብለዋል ዶር ነጋሶ

By:Minilik Salsawi 29.09.13

«ፖሊሶች ከአቅማቸው በላይ ነዉ። ሕገ መንግስትና በሕግ ሳይሆን በመመሪያ ነዉ የሚተዳደሩት። ሕዝቡ ሰላማዊ ሆኖም ከመርካቶ፣ ከሳሪስ፣ ከሜክሲሶ ሕዝቡ እንዳያልፍ ማድረጋቸው የፍርሃታቸው ጥግ የት እንደደረሰ የሚያሳይ ነዉ። የሰዉን ሁኔታ የተረዱ ይመስለኛል» አቶ ግርማ ሰይፉ

«ለአይንህ መጨረሻዉን የማታየው ሕዝብን ማየት ያሰደስታል። ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በራሱ ግብ አይደለም። ላለፉት 3 ወራት በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል ስናደርግ የነበረው የመጀመሪያ ፌዝ አጠናቀናል። የመጀመሪያዉን ፌዝ አጠናቀቅን ስንል ፣ የትግሉ ሂደት ተጠናቀቀ ማለት አይደለም። ከመጣነዉ ይልቅ የሚቀረን እንደሚረዝም ነዉ የምናስበዉ» አቶ ሃብታሙ አያሌው። አቶ ሃብታሙ በቅርቡ በጸረ-ሽብር ሕጉ ዙሪያ በኢቲቪ በተደረገው ክርክር አንድነት ወክለዉ ቀርቦ የነበረ ወጣት የአንድነት አመራር አባል ነዉ።

AFP, Bloomberg News, AL JAzria ….የመሳሰሉ በርካታ የዉጭ ጋዜጠኞች ተገኝተዉ ነበር። ፖሊሶች መንገዱን መዝጋታቸውን ታዝበዋል። «ሰልፉ አልተፈቀደም እንዴ ? ከተፈቀደ ለምንድን ነው መንገድ የሚዘጉትም ? ህዝቡ እንዳይቀላቀል ለምን ያደርጋሉ ? » የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

የሰላማዊ ሰልፉ መርሃ ግብር ተጠናቋል። ምንም እንኳን አገዛዙ አይን ባወጣ መልኩ የሕዝብን መብት ቢረግጥ የአዲስ አበባ ሕዝብ ምን ያህል የሰለጠነ እንደሆነም አሳይቷል። አንድ ሰው ሳይጎዳ፣ አንዲት ጠጠር ሳይወረወር ሰልፍ በሚያስደንቅ ሁኔታ ተጠናቋል።

ከመርካቶ፣ ከሳሪስ ልደታ የሚመጡ መንገድ ተዘግቶ መምጣት አልቻሉም። በመቶ ሺህ የሚቆጠረዉ በቀበና አደባባይ የተሰበሰበው ሕዝብ በአጭሩ ከአንድ አካባቢ የተሰበሰበዉ ህዝብ ነዉ። ፖሊሶች መንገድ ባይዘጉና፣ ከሁሉም የአዲስ አበባ ክፍሎች ሕዝቡ እንዲያልፍ ቢደረግ ኖሮ ሚሊዮኖች ሊገኙ የሚችሉበት ሁኔታ ነበር።

ሰልፉን ለመዝጋት ዶር ነጋሶ ንግግር አድርገዋል። ከሁለት ሳምንታት በፊት 70 አመታቸውን እንዳከበሩ የገለጹት ዶር ነጋሶ የተሰማቸዉን ከፍተኛ ደስታ ገልሰዋል።

«እዚህ ያላችሁ አብዛኞቻችሁ የልጄቼ ልጆች ልትሆኑ ትችላላችሁ። ተስፋ የማድረግባችሁ ናችሁ» ብለዋል ዶር ነጋሶ

በመጨረሻ የሰልፉ አዘጋጆች መንገዱን ለዘጉባቸው ፖሊስ ሰራዊቶች ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

ሰበር ዜና፣ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!

20130928_230706
20130928_175953
September 29, 2013
ዛሬ ሴፕቴምበር 28 በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የታሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ። በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ በስጦታ እና ጨረታ ብቻ 408 ,633.85 የኖርዌጅያን ክሮነር የተገኘ ሲሆን ። ይህ ገቢ ከምግብ ሺያጭ ፣ ከመግቢያ ትኬት፣ ከቲሸርት ሺያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶች ሺያጭ ሳይጭምር መሆኑ ወዳጆችን ሲያስፈነድቅ ጠላቶችንን አንገት አስደፍቷል ። በፕሮግራሙ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ኮማንደር አሰፋ ማሩ በመገኘት ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖች ጋር ምክክር አድርገዋል። ሙሉ ዘገባውን በቅርብ ይዘን እንቀርባለን ።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
ከኖርዌይ

onsdag 25. september 2013

የአልሸባብ የናይሮቢ ጥቃት እየተወገዘ ነው

1814fb497784122f4f25346aec515b43_XL
ባለፈው ቅዳሜ መስከረም 11 ቀን 2006 ዓ.ም. በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ምዕራባዊ ክፍል የሚገኘው ዝነኛው ዌስትጌት የገበያ ማዕከልን በመውረር፣ 62 ሰዎችን ገድሎ ከ200 በላይ በሚሆኑት ላይ የአካል ጉዳት ያደረሰው አሸባሪው አልሸባብ በዓለም ዙሪያ እየተወገዘ ነው፡፡
የአልሸባብ አረመኔያዊ ድርጊት ሰለባ ለሆኑት ሰዎች ቤተሰቦችና ለኬንያ መንግሥት የሐዘን መግለጫዎች እየጎረፉ ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አማካይነት የአልሸባብን ጥቃት አውግዟል፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ አልሸባብ በንፁኃን ሰዎች ላይ በፈጸመው አደጋ ማዘናቸውን ገልጸው፣ የጥቃቱን ፈጻሚዎች በቁጥጥር ሥር ለማዋልና ለሕግ ለማቅረብ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር በመሆኗ በፀረ ሽብር ትግሉ ሌሎች የአፍሪካ አገሮችን በማስተባበር ግንባር ቀደም ሚና ለመጫወት ቁርጠኛ መሆኗን አስረድተዋል፡፡ የአልሸባብን የሽብር እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ለማኮላሸት እንዲቻል የሶማሊያን መንግሥት የፀጥታና የደኅንነት መዋቅሮችን ለማጠናከር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፉን በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
የሽብር ጥቃቱ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ከሽብርተኝነት ራሳቸውን ለመከላከል በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥት (ኢጋድ) ግንባር ቀደም መሪነት በተቀናጀ ሁኔታ መምራት እንዳለባቸው አመላካች መሆኑን ዶ/ር ቴድሮስ አስታውቀዋል፡፡
ኢጋድ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ በዌስትጌት የገበያ ማዕከል በሽብርተኞች በደረሰው ጥቃት ማዘኑን ገልጾ፣ ለኬንያ መንግሥት፣ ሕዝብና የአደጋው ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡ ድርጊቱንም አውግዟል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን በበኩላቸው፣ በናይሮቢ የተፈጸመው የሽብር ጥቃት እጅግ አሳዛኝ ነው ብለዋል፡፡ ድርጊቱ አሳዛኝ ከመሆኑም በላይ ሊወገዝ የሚገባው ነው ብለዋል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በናይሮቢ በተፈጸመው የአሸባሪዎች ጥቃት ለሞቱትና ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች፣ መንግሥትና ሕዝብ መፅናናትን ተመኝተው፣ መንግሥታቸው አሸባሪዎችን ለሕግ ለማቅረብ ከኬንያ መንግሥት ጎን እንደሚሰለፍ አስታውቀዋል፡፡ በኬንያና በአሜሪካ መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት በማስታወስ ሽብርተኞችን ለማንበርከክ አሜሪካ ድጋፏን ትቀጥላለች ብለዋል፡፡
የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዊሊያም ሔግ መንግሥታቸው በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኘውን አሸባሪ ድርጅት አልሸባብን ከኬንያ ጎን ሆኖ ይፋለማል ብለዋል፡፡ ድርጊቱንም አረመኔያዊ በማለት ገልጸውታል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት የአልሸባብን ድርጊት አውግዞ ከኬንያ ሕዝብና መንግሥት ጎን እንደሚቆም አረጋግጧል፡፡ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔትናያሁ እንዲሁ ሐዘናቸውን ገልጸው፣ መንግሥታቸው ከኬንያ ጋር በፀረ ሽብር ትግሉ እንደሚተባበር ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካና የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው አሸባሪዎች በተሳተፉበት በዚህ ጥቃት የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችና ፈንጂዎች ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን፣ ሦስት የኬንያ ወታደሮችን ጨምሮ 62 ሰዎች መገደላቸውን ዘግይተው የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ የ18 ወይም የ19 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶቹ አሜሪካዊያን የሶማሊያ ወይም የዓረብ ዝርያ ያላቸው ሲሆኑ፣ እንግሊዛዊቷ ግን ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሽብር ተግባሮች የተሳተፈች መሆኗን የኬንያ ባለሥልጣናት መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ ሳማንታ ሊውትዌይት እንደምትባል የተነገረላት እንግሊዛዊት ከዚህ ቀደም የተገደለው ጀርሜይን ሊንድሴይ የተባለ አሸባሪ ሚስት እንደሆነች ተዘግቧል፡፡ ይህች ሴት ከአሜሪካዊያኑ ጋር መገደሏ ተነግሯል፡፡ የእዚህች ሴት ባል እ.ኤ.አ. በ2005 በለንደን የቦምብ ጥቃት ሲያካሂድ የተገደለ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የአሜሪካና የእንግሊዝ ባለሥልጣናት ስለተጠቀሱት አሸባሪዎች ጉዳይ ምርመራ መጀመራቸው ታውቋል፡፡
ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ የኬንያ ፀጥታ ኃይሎች የዌስትጌት ገበያ ማዕከልን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራቸውንና በአሸባሪዎቹ የተጠመዱትን ፈንጂዎች ማንሳታቸው በተለያዩ ዘገባዎች ተገልጿል፡፡ ምንም እንኳ የገበያ ማዕከሉን እየተቆጣጠሩ በነበረበት ወቅት ተኩስና ፍንዳታዎች ቢሰሙም፣ ከአራት ቀናት ትንቅንቅ በኋላ ዘመቻው ትናንት ማምሻውን ወደ መጨረሻው እየተቃረበ ነበር ተብሏል፡፡
የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚና መሐመድ በአሸባሪዎቹ የታገቱት በሙሉ ነፃ መውጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡ አንድ የኬንያ ፖሊስ ባለሥልጣን ደግሞ በአሸባሪዎች ላይ የተጀመረው ዘመቻ እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል፡፡ ቀደም ሲል የት እንደደረሱ ያልታወቁ 63 ሰዎች እንደነበሩ ቢገለጽም ዕጣ ፈንታቸው አልታወቀም፡፡ አልሸባብ በትዊተር ድረ ገጹ ታጋቾች በእጁ እንደሚገኙ አስታውቆ፣ በርካታ አስከሬኖች በየቦታው መውደቃቸውን ገልጿል፡፡ የኬንያ ፀጥታ ኃይሎች ግን አንድ ወይም ሁለት አሸባሪዎች በሕይወት ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመው፣ ዘመቻው እየተጠናቀቀ መሆኑን እየገለጹ ነበር፡፡ ታጋቾችም ሙሉ በሙሉ ነፃ መውጣታቸውንም አስታውቀዋል፡፡ አልሸባብ ማክሰኞ ማምሻውን በትዊተር እንደገለጸው፣ ታጣቂዎቹ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱንና በተጠናከረ ሁኔታ የገበያ ማዕከሉን ተቆጣጥሯል፡፡
በሌላ በኩል የናይሮቢ የሆስፒታል ምንጮች መሞታቸው ከተረጋገጠው 62 ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች 60 አስከሬኖችን ለመቀበል እየተጠባበቁ እንደነበር ተሰምቷል፡፡ ምናልባትም የደረሱበት ያልታወቁ የተባሉ ሰዎችን አልሸባብ ፈጅቷቸዋል የሚል ግምት አሳድሯል፡፡ መሞታቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ውስጥ ብዙዎቹ ኬንያውያን ሲሆኑ 18 ያህሉ ደግሞ የእንግሊዝ፣ የሆላንድ፣ የፈረንሳይ፣ የአውስትራሊያ፣ የፔሩ፣ የህንድ፣ የስዊዘርላንድ፣ የቻይና፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የኒውዚላንድና የካናዳ ዜጎች ሲገኙበት፣ ታዋቂው የጋና ገጣሚ ፕሮፌሰር ኮፊ አዎኒ መገደላቸው ታውቋል፡፡ አምስት አሜሪካውያን ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል ይገኛሉ፡፡
የኬንያው ጭፍጨፋ በአልሸባብ ቢፈጸምም ከጀርባው ግን ዓለም አቀፍ አሸባሪው አልቃይዳ እንዳለበት መረጋገጡን የኬንያ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡ የአልሸባብና የተባባሪው አልቃይዳ ዓላማ ኬንያ በሶማሊያ ሰላም ለመፍጠር በሚደረገው ትግል አልሸባብን በመደምሰስ ተሳታፊ በመሆኗ ለመቅጣት ነው፡፡ እስከ ማክሰኞ ምሽት ድረስ በገበያ ማዕከሉ የተወሰነ ሥፍራ ውስጥ የመሸጉ አሸባሪዎች በእጃቸው ላይ ታጋቾች መኖራቸውን በመግለጻቸው የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ተብሏል፡፡ የኬንያ ባለሥልጣናት ግን ዘመቻው ወደ መጠናቀቂያው መቃረቡን ገልጸዋል፡፡ ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ በገበያ ማዕከሉ ውስጥ የኬንያ የፀጥታ ኃይሎችና አሸባሪዎቹ የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ እንደነበር ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡
አልሸባብ በናይሮቢ ውስጥ በፈጸመው የጭካኔ ተግባር ምክንያት የኢጋድ አባል አገሮችና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተጠናከረና በተደራጀ ሁኔታ እንዲዘምቱበት እየተነገረ ሲሆን፣ በተለይ ለሰላማቸውና ለደኅንነታቸው በእጅጉ የሚጨነቁት ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ኡጋንዳ ኃይላቸውን አስተባብረው ወሳኝ ዕርምጃ ሊወስዱበት እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡ በአልሸባብ ላይ የሚደረገው ዘመቻም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚቸረውም ይጠበቃል፡፡

ሰበር ዜና ከአዲስ አበባ፤ ፖሊስ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት አሰረ

september 25. 20 13

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የታሰሩ የፓርቲውን የቅስቀሳ ቡድን አባላት ለማስፈታትወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ የሽሮ ሜዳ ፖሊስ ማዘዣ ጣብያ በማምራት ለፖሊሶቹ ‹‹ልጆቹ የፈጸሙት ህገ ወጥ ድርጊት የለም፣ሲቀሰቅሱ የነበሩትም እውቅና የተሰጠውን ሰላማዊ ሰልፍ ነው፡፡ቅስቀሳው ህገ ወጥ ነው የምትሉም ከሆነ እነርሱን የላኳቸው እኔ በመሆኔ እኔን ልታስሩኝ ትችላላችሁ ››ብለዋል፡፡
ፖሊስ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን በማሰር ወጣቶቹን ለቅቋቸዋል፡፡

tirsdag 24. september 2013

የአሸባብ አመፅ በኬንያ

SEPTEMBER 24, 2013 LEAVE A COMMENT
0,,17111886_403,00
ራሱን አሸባብ ሲል የሚጠራው የሶማሊያ አማፂ ቡድን አሽበባብ በናይሮቢዉ የገበያ አዳራሽ ባደረሰዉ ጥቃት ከሞቱት ሰዎች መካከል 6ቱ ብሪታናዊያን ሲሆኑ በሌላ በኩል ከአሸባሪዎቹ ጋ የተባበሩ የብሪታንያ ዜጎች መኖራቸዉ በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።
በኬንያ የሚኖሩ የጎረቤት አገሮች ስደተኞችም ከጥቃቱ ጋ በተያያዘ ስጋት ገብቶናል እያሉ ነው። የፀጥታ ጥናት ተቋም በበኩሉ ለዚህ አይነቱ አደጋ ወታደራዊ ርምጃ ብቻውን መፍትሄ አይሆንም ባይ ነው።
አሸባብ ናይሮቢ በሚገኝ የገበያ አዳራሽ ላይ ባደረሰው ጥቃት የአሜሪካ ፖለቲከኞችን እያወዛገበ ነው።የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ መስተዳድር አደጋውን የጣሉትን ወገኖች ተከታትሎ ለመያዝ እና ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈፀም ለመከላከል ከኬንያ እና ከሌሎች የአካባቢው መንግስታት ጋ አብሮ እንደሚሰራ አስታውቋል። ባለሙያዎችም ወደ ኬንያ ተልከዋል። በሌላ በኩል የኦባማ መንግስት ተቃዋሚዎች ዮናይትድ ስቴትስ በአሸባብ ላይ ቀጥታ ወታደራዊ ርምጃ መውሰድ አለባት እያሉ ነው። ዝርዝር ዘገባዉን ከሶስት ዘገባዎች በድምፅ ያገኛሉ።
ጃፈር አሊ
ሀና ደምሴ
አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሐመድ
ሊንኩን በመንካት ዝርዝር ዘገባውን ያዳምቱ
ብሪታንያ እና የኬንያው ጥቃት
በኬንያ ጥቃት ላይ የዮናይትድ ስቴትስ አቋም
የኬንያው ጥቃት እና የስደተኞች ስጋት

ሰማያዊ ፓርቲና በፖሊስ የተገታው ሰላማዊ ሰልፉ፣

ሰማያዊ ፓርቲ ፣ በአቅዱ መሠረት ፣ ትናንት በመስቀል አደባባይ ሊያካሂደው የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ እርምጃ መደናቀፉ ተነገረ።
0,,17107279_303,00
ሁኔታውን የተከታተለው ዘጋቢአችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር እንደገለጸው፤ ሰልፈኞቹ፤ ወደ መስቀል አደባባይ እንዳይኼዱ በፖሊስ በመከልከላቸው፤ ሰልፉ የተከናወነው በፓርቲው ጽ/ቤት ግቢ ነበር።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ተክሌ የኋላ

15 የሚሆኑ የአንድነት ፖርቲ አባላት ዛሬ ህገወጥ እስር ተፈጸመባቸው

September 24th, 2013   
 
አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ መስከረም 19 ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 15 አባላቱ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው፡፡ አባላቱ ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው ጎዳና በመኪና ላይ እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት ሚኒሊክ ት/ቤት ፊትለፊት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የሚተላለፈውን መኪና መንገድ በመዝጋት ቅስቀሳውን አደናቅፈዋል፡፡

553582_717269128289551_1267195516_nበስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች “ቀስቃሾቹ ህጋዊ ወረቀት ይዘዋል፤ልቀቋቸው” በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል ከአንድነት ፓርቲ ጎን እንደሚቆሙም ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ 15 የሚሆኑትን የቅስቀሳ ቡድን አባላት ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል፡፡

 የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አባላቱ ወደ ታሰሩበት 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ረ/ኢ መንግስቱ ለማ የተባሉትን የፖሊስ ጣቢያው ኃላፊ የታሰሩት አባላት እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡ ኃላፊውም “ህጋዊ ሰልፍ እንደምታደርጉ እናውቃለን ይቀስቅሱ የሚል መመሪያ አልደረሰንም ብለዋል፡፡ አመራሮቹ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነርንና የከተማዋን መስተዳድር ሃላፊዎች ለማነጋገር ተንቀሳቅሰዋል፡፡

በተለያየ አቅጣጫ የተሰማሩት ሌሎቹ የአንድነት ፓርቲ ቅስቀሳ ቡድን አባላት ስኬታማ የመኪና ላይ ቅስቀሳ በማደረግ ላይ ናቸው፡፡

በተያያዘም ዜና የአራት ኪሎ ነዋሪዎች እውቅና ተችሮታል የተባለን የአንድነት የመስከረም 19 ሰላማዊ ሰልፍ ህዝብ አሳታፊ ለማድረግ ዛሬ ማለዳ ከአንድነት ቢሮ በዛ ያሉ መኪኖች ለቅስቀሳ ወጥተዋል፡፡

በአራት ኪሎና በአካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ለመቀስቀስ ከወጡ መኪኖች መካከል የተወሰኑት በፖሊስ በህገ ወጥ መንገድ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርገዋል፡፡
በመኪኖቹ ውስጥ የነበሩትን የአንድነት አባላት ፖሊስ ወደ ጣብያ ለመውሰድ ባደረገው ሙከራ ህዝብ መሰብሰብ ችሏል፡፡ሁኔታውን በአንክሮ ይከታተል የነበረ ህዝብ ፖሊሶቹን ልጆቹን መውሰድ አትችሉም፣ሰልፉ እንደተፈቀደ እየታወቀ መቀስቀስ አትችሉም ማለታችሁ ህገ ወጥ ድርጊት ነው››በማለት እጅግ በሚያስደስት ሁኔታ ተከራክረዋል፡፡

አዎን ህገ ወጥ ድርጊት ሲፈጸም በእኔ ላይ ካልሆነ ምን አገባኝ ብለን የምናልፍበት ዘመን ማብቃት ይኖርበታል ፡፡ይህንን ደግሞ የአራት ኪሎ ሰዎች ስለ ጀመሩት ከወዲሁ ምስጋናችን ይድረሳቸው፡፡

fredag 20. september 2013

አሳዛኝ ሰበር ዜና ዲፕሎማቱ እጅ ላይ ያረፈችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ሬሳ ትላንት ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰደ ።

ትላንት ቀን መስከረም 8 2006 ለ5ኛ ግዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግዜያዊ መጠለያ ኮንቴነር ውስጥ፡ የአንዲት ኢትዮጵያዊት አስዛኝ፡ ህልፈተ ህይወት የአካባቢውን ማህበረሰብ እንምባ ሲያራጭ፡ደረት ሲያዳቃ መዋሉን የአይን ምስክሮች ገለጹ ። ወጣቷ በቤት ሰራተኝነት ኮንተራት የመጣች የክርስትና እምነት ተከታይ መሆኗን የሚናገሩት እነዚህ የአይን እማኞች የወጣቷ ሬሳ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዱን አረጋግጠዋል።
የእህቶቻችን ሞት ከሚፈበረክበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የስደተኞች ጊዜያዊ መጠለያ ኮንቴነር ፡ ያለምንም ህክምና እና በቂ መሰረታዊ ፍጆታ በለሌለበት ሁኔታ እንደ ወንጀለኛ የኮንቴነር የብረት በር ተከርችሞባቸው ከሚገኙ እህቶቻችን መሃከል አንድ ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ በተከታታይ የሁለት ኢትዮጵያውያን ህልፈተ ህይወት መሰማቱ የአካባቢውን ማህበረሰብ አስደንግጦል።
በተለይ ትላንት ማለዳ በኢትዮጵያ ሰዓት አቋጣጠር ከጠዋቱ 3 አካባቢ አስከሬንዋ ጊዘያዊ መጠለያ ኮንቴነር ውስጥ፡ ሞታ የተገኘችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ህመሙ አገርሽቶባት ስታቃስት «ጣረሞት ስታሰማ» ፡ እንደ ነበር የሚናገሩ ወገኖች ዲፕሎማቱ ትብብር እንዲያደርጉላት ስልክ ቢደወልላቸውም በወቅቱ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የወጣቷ ህይወት በሚያሳዝን ሁኔታ ማለፉን ይገልጻሉ።ሞች እዚህ ደረጃ ላይ ከመድረሷ በፊት ዲፕሎማቱ በኤንባሲው ሃላፊነት ወደ ሆስፒታል ወስደው ማስመርመር እና ህይወቷን ከሞት መታደግ ሲችሉ ባስዩት ግዴለሽነት እና ወገናዊ ርህራሄ የጎደለው አሰራር የወጣቷ ህይወት እዚህ በረሃ ላይ ቀርቷል ብለዋል። ወጣቷን ወደዚህ ግዜያዊ መጠለያ ግቢ ዲፕሎማቱ ከአሰሪዎቾ ተረክበው ሲያመጧት ሃኪም ቤት ውሰዱኝ ህይወቴን አጣሁ !! አድኑኝ ኸረ የወገን ያለህ !! ኸረ ያህገር ያለህ !! አናቴ ድረሺልኝ !! እያለች ትማጸናቸው እንደነበረ በአካባቢው የነበሩ የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል ። የወጣቷ የሰውነት አቋም እና አጠቃላይ ሁኔታ ያዩ አንዳንድ ታዛቢዎች በውስጦ፡የቆየ በሽታ እንደሌለባት እና ወጣቷ አንጀቴ ተቃጠለ ውሃ ውሃ ስትል እንደነበር እና ሃኪም ቤት ውሰዱኝ፡እያለች ልብ በሚነካ ሁኔታ ስትማፀን የታዘቡ ወገኖች ምናልባትም ከምግብ ጋር የተቀልላቀለ መርዝ ነክ ነገር በልታ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ያጎላሉ።
በማያያዝ ዲፕሎማቱ ወጣቷን ከአሰሪዎቾ ተቀበለው ወደ መጠለያ ሲያመጧት ለአመታት የደከመኩበትን የወር ደሞዜን እባካቹ ከአስሪዪ ላይ ተቀበሉልኝ እያለች ትጮህ እንደ ነበረ እና ወደ መጨረሻ አካባቢ እየደከመች ስትመጣ ሞች በሚያሳዝን አንደበት ሆስፒታል በር ላይ ወስዳችሁ ጣሉኝ፡የወግን ያለህ እያለች እስከ ዕለት ሞቷ ታለቅስ እንደ ነበረ እና ይህንንም ተማጽኖ ዲፕሎማቶቹ «የመንፈስ ጭንቀት ነው» ፡ «ስራ በዝቷባት ነው» ፡« ሃገር መግባት ፈልጋ ነው» ስታጭበረብር ነው» ወዘተ …… በሚል ፌዝ በጭካኔ ሌሎችን ሰላም ትነሳለች በሚል ለብቸዋ ኮንቴነር ውስጥ፡አስገብተው እንደቆለፉባት እና በነጋታው ወጣቷ ሞታ ማደሯን አንዳንድ የኮሚኒቲው አባላት እንባ እየተናነቃቸው ገልጸዋል ። ይህ በዚህ እንዳለ ትላንት 4 ሰዓት ከ15 ደቂቃ አካባቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ የወጣቷ አስከሬን በሳውዲ የማዘጋጃ ሰራተኞች ተነስቶ ወደ አልታወቀ ስፈራ እንደተወሰደ እነዚህ የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል።
Ethiopian Hagere ከሳውዲ አረቢያ ጅዳ በዋዲ
 Ethiopian Hagere

lørdag 14. september 2013

ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ እሁድ ሴፕቴምበር 22 ቀን 2013 በዋሽንግተን ዲሲ / ቨርጂኒያ

ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ እሁድ ሴፕቴምበር 22 ቀን 2013 በዋሽንግተን ዲሲ / ቨርጂኒያእሁድ ሴፕቴምበር 22 ቀን 2013 በዋሽንግተን ዲሲ/ ቨርጂኒያ የግንቦት 7 ንቅናቄ አመራር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሚገኙበት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ከሕብረተሰቡ ጋር ውይይት ለማድረግ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ተዘጋጅቷል..

ቀን : እሁድ ሴፕቴምበር 22 2013


ሰአት: 2.00 pm – 6:00 pm


ቦታ : ሸራተን ናሽናል ሆቴል (ከዳማ ምግብ ቤት አጠገብ የሚገነው) 900 South Orme Street, Arlington, VA


መግቢያ: $20


ለተጨማሪ መረጃ: 571-239-7001



የግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ

fredag 13. september 2013

በኮንዶሚኒየም ቤቶች ሺያጭ ሥም ስደተኛውን የወያኔ ጭሰኛ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ይከሽፋል::

ወያኔ እንደ ድርጅት የሚፈልገውን የፖለቲካ ጥቅም የሚያስገኝለት እስከመሰለው ድረስ በህዝብና በአገር ላይ የማይፈጽማቸው ምንም አይነት እኩይ ተግባሮች እንደማይኖሩ በተግባር ያስመሰከረ ድርጅት ነው::
ለአብነት ያህል ለመጥቀስ ፤
  1. ድርጅቱ ገና ትግራይ በረሃ ውስጥ ትግል ላይ በነበረበት ወቅት የትግራይን ወጣቶች ከትምህርት ገበታቸው እያነቀ በመውሰድ አላማውን በግልጽ ላልተረዱትና ላላመኑበት ጦርነት ማግዶአቸዋል:: በዚህም የተነሳ ወያኔ እራሱ ይፋ ባደረገው አሃዝ ብቻ ቁጥራቸው 60 ሺህ የሆኑ ለጋ ወጣቶች ላለፉት 22 አመታት የህዝባችንን ስቃይና መከራ እያራዘመ ያለውን የድርጅቱን መሪዎች ሥልጣን ላይ አውጥቶ ለማንገስ ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል ::
  2. የአገራችንን ክብርና መልካም ገጽታ እስከዛሬ አበላሽቶ ባለፈው በዚያ አስከፊ የ1977ቱ ድርቅ ወቅት ለትግራይ ተጎጂዎች ከአለም አቀፍ ለጋሾች የተበረከተውን የነፍስ አድን እህል በሱዳን በኩል ወደውጭ አሳልፎ በመቸብቸብ መሪዎቹና ተከታዮቻቸው ለተንደላቀቀ ኑሮ ሲበቁ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህጻናት፤ አሮጊቶችና አዛውንቶች እንደቅጠል እንዲረግፉ ምክንያት ሆኖአል::
  3. የትግራይ ህዝብ ተማሮ በመንግሥት ላይ እንዲያምጽ ለመቀስቀስ በደሃው አቅማችን የተገነቡ ትምህርት ቤቶችን፤ የህክምን አገልግሎት መስጫ ተቋሞችን ፤ ድልድዮችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በፈንጂና በመድፍ ከማውደም አልፎ የተሳሳተ መረጃ ለደርግ በመስጠት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ህዝብ ለገበያ እንደወጣ ሃውዜን ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ እንዲጨፈጨፍ አድርጎአል::
  4. የደርግ አገዛዝ ከተወገደ ቦኋላ ሥልጣን ላይ ለመደላደል የሚያስችል ድጋፍ ለመሸመት ሲባል የአገራችንን ሉአላዊ ጥቅም ለባዕድ አሳልፎ የሰጠ በርካታ ግልጽና ድብቅ ውሎችን ከ3ኛ አካላት ጋር ፈጽሞአል :: ከውሎቹ አንዱ የህዝባችንን ትኩረት ለማስለወጥ ካለፈው 2 አመት ጀምሮ በሰፊው እየተዘመረለት የሚገኘው የአባይ ወንዝን የመጠቀም መብታችንን የሚጻረር እንደነበረ ጉልህ ማስረጃ አለ::
  5. በሚሊዮን የሚጠጋ ህዝባችንን ከቀያቸው በማፈናቀል ለም መሬታችንንና ድንግል የተፈጥሮ ሃብታችንን ለህንድ ፡ ለቻይናና ለአረብ ከበርቴዎች በመቸብቸብ በገዛ አገራችን የባዕድ አሽከር እንዲንሆን ፈርዶብናል::
  6. በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችን ለባርነት ሥራ ወደ አረብ አገር በመላክ ከፍተኛ ሰቆቃ እንድፈጸምባቸው በማድረግ ብሄራዊ ክብራችንን ኩራታችንን የሚያጎድፍ ተግባር ፈጽሞአል::
  7. በሙስናና ዘረፋ የተጨማለቀ ሥርዓት በማቋቋም አብዛኛው ህዝባችን ከወለል በታች ወደወረደ የድህነት አረንቋ ውስጥ ገብቶ የቁም ስቃይ እንዲቀበል አድርጎአል::
  8. መብታቸውን ለማስከበር በጠየቁ ወገኖቻችን ላይ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ጦር በማዝመት በርካቶችን አስጨፍጭፎአል፤ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎአል ፤ ለእስርና ለስደት ዳርጎአቸዋል:: ወዘተ
ወያኔ ይህንንና ግዝፈታቸው ከዚህ የከበዱ በርካታ ሰቆቃዎችን በአገርና በወገን ላይ እየፈጸመ የአገዛዝ ዘመኑን ሊያራዝም የቻለው፤
  1. ህዝባችን በዘር ፤ በቋንቋና በሃይማኖት ተከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዳይተማመንና የጎሪጥ እንድተያይ ሌት ተቀን ተንኮል በመሸረቡ
  2. የጦር ሃይል ፤ የፖሊስ ሠራዊት፤ የደህንነትና ሌሎች የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋሞች በሙሉ ከአንድ አካባቢ በተሰባሰቡ የጥቅም ተጋሪዎች ቁጥጥር ሥር እንዲወድቅ ተደርጎ እሺ ያለውን በጥቅም እምቢ ያለውን ደግሞ በጠመንጃ ሃይል ጸጥ ለጥ ለማድረግ በመመኮሩ፤
  3. ከራሳቸው የግል ሚቾትና ቅንጦት አሻግረው በወገንና በአገር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃ ማየት የማይፈልጉ ወይም የማይችሉ ተፈጥሮአዊ ባህሪያቸው “ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል “ ካለቺው እንስሳ የማይለይ ሆዳሞች ከተለያየ የህበረሰተሰብ ክፍል ተመልምለው ከአገዛዙ ዙሪያ በሎሌነት ለመሰለፍ በመቻላቸው እንደሆነ ይታወቃል::
በሌላ አገላለጽ ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው ቀደም ሲል ፋሽስት ጣሊያን የአገራችንን ህዝብ በባርነት ለመግዛት አድርጋው ከነበረው ቅስም ሰባሪ እርምጃዎች በባህሪም ሆነ በአይነት አንድ መሆኑ ግልጽ ነው:: ለመብቱና ለነጻነቱ ቀናዕ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ትናንት ለጣሊያን መደለያዎች ተታሎ ወይም የሃይል እርምጃ ተንበርክኮ ነጻነቱን አስነጥቆ ለመኖር እንዳልፈቀደ ሁሉ ዛሬም ከአገሩ የሰሜን ክፍል የበቀሉ ባንዳዎች በጉልበታቸውም ሆነ ሌሎች መሸንገያዎች የሚያደርጉትን አሜን ብሎ እስከወዲያኛው ለመገዛት ፈቃደኛ አለመሆኑን በሚያደርገው ተቃውሞ እየገለጸ ነው::
ይህንን ሃቅ የተረዳው ወያኔ የጭቆና ክንዱን ለማፈርጠም የሚያስፈልገውን ገንዘብ በስደት ውጭ አገር ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለመሰብሰብና የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለማዳከም በኮንዶሚኒየም ቤት ሽያጭ ሥም አዲስ እቅድና ስልት ነድፍ መንቀሳቀስ ጀምሮአል::
ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠፉ በቅርቡ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ እንዳረጋገጡት ወያኔ በስደት ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ የነደፈው የኮንዶሚኒየም ቤት ሺያጭ ዋና አላማ አገር ቤት ውስጥ እየተፏፏመ የመጣውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመምታት በተለያዩ የምዕራብ አገሮች ከፍ ብለው እየተደመጡ ያሉትን ድምጾች አሰቀድሞ ለማዳከም በመፈለጉ እንደሆነ አያጠራጥርም::
ምንም እንኳን ለራሳቸው ማንነትና ስብእና ክብር የሌላቸው አንዳንድ ዜጎች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ፈሊጥ በዚህ የወያኔ ወጥመድ ውስጥ ለመውደቅ ውር ውር እያሉና በየአገሩ የሚገኘውን የወያኔ ኤምባሲ በር ማንኳኳት የጀመሩ መኖራቸው ባይካድም አንድ ወቅት ላይ ግር ግር ፈጥሮ ወዲያው እንደተጨናገፈው የአባይ ቦንድ ሺያጭ የታሰበውን ያህል ውጠት እንደማያስገኝ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት የሚኖረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሩንና ወገኖቹን ጠልቶ ሳይሆን የተሰደደው ለዘመናት የዘለቀው ኢፍትሃዊነት የፈጠረው ኋላ ቀርነትና ድህነት አገሩ ላይ ለመኖር ያለውን ምኞትና ተስፋ አጨልሞበት አለያም በፖለቲካ ችግር ምክንያት ህይወቱን ለማቆየት ተገዶ ነው ብሎ ያምናል::
በዚህም የተነሳ ማንኛውም ስደተኛ ስደት የሚያስከትለውን ማህበራዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶች ተቋቁሞ አንድ ቀን አገሬ ገብቼ ከወገኖቼ ጋር በሠላም እኖርበታለሁ ብሎ ያጠራቀማትን ጥሪት በከፍተኛ ንቅዘትና ሙሰኝነት ወደ መጨረሻው ታሪካዊ ሞቱ እየወረደ ያለውን የወያኔ ሥርዓት ተማምኖ በማውጣት ቦኋላ እንዳይጸጸት ወገናዊ ምክሩን ይለግሳል::
ወያኔ ለዲያስፖራው ያዘጋጀው የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ሺያጭ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት የታለም የከተማና የገጠር ህዝባችንን የወያኔ ጭሰኛ ያደረገ የአገር ውስጥ ፖሊሲ አካል ነው:: ከ7 አመት በፊት ኮንዶሚኒዬም ቤት ለማግኘት ለተመዘገቡ 800 ሺህ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ያልተዳረሰ ቤት እንዴትና በምን ስሌት ነው በሰው አገር ያውም በአንጻራዊ ምቾት ለምንኖር ዜጎች የታሰበልን ብሎ እራስን መጠየቅ ከትዝብትና ከታሪክ ተወቃሽነት የሚያድን ተግባር ነው ::
ሃብት በተትረፈረፈበትና የሚበላ የሚጠጣ ነገር ከሰው ተርፎ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ በሚጣልበት አሜሪካና አውሮጳ ለምንኖር ዜጎች ከሚስኪኑ ህዝባችን ጉሮሮ በተነጥቀ ገንዘብ ቤተመንሥት ውስጥ ተዘጋጅቶ የተላከ ምግብና መጠጥ ለመደለያነት ሲያጓጉዝ የኖረ መንግሥት አሁን ደግሞ በኮንዶሚኒየም ቤት ሥም ቢመጣብን ጥፋቱ የሱ ሳይሆን የእኛ ለክብራችንና ለነጻነታችን ዋጋ የማንሰጥ ስግብግቦች መሆኑን ምን ጊዜም መዘንጋት የለበትም::
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በስደት ውጭ አገር የሚኖር ማንኛውም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወያኔ በኮንዶሚኒዬም ቤት ሽያጭ ሥም ትግሉን ለማዳከም የዘረጋውን ይህንን የተንኮል ሴራ እንዲያከሽፍ ወገናዊ ሃላፊነት እንዳለበት ያስገነዝባል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

torsdag 12. september 2013

ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ በረሀብ አድማው ገፍታበታለች


መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩኒስኮና የ’ኢንተርናሽናል ዊመንስ ሚዲያ ፋውንዴሽን’ ሽልማቶች አሸናፊ የሆነቸው ታዋቂዋ ፀሀፊና መምህር ርእዮት አለሙ በእስር ቤት የጀመረቸውን የረሀብ አድማ የቀጠለች ሲሆን፣ በእስር ቤት የሚገኙ ሌሎች እስረኞች እያሰቃዩዋት መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

በግፍ የታሰረቸው ርእዮት ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑዋ የሚደርስባት ስቃይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ስልት ርእዮት ከእናትና አባቷ እንዲሁም ከነፍስ አባቷ በስተቀር ሌሎች ሰዎች እንዳይጠይቋት የተላለፈውን መመሪያ በመቃወም የረሀብ አድማውን መጀመሩዋ ታውቋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው እናቷ ወ/ሮ አሰለፈች ተክለማርያም ርእዮት የጨጓራ በሽተኛ ብትሆንም በአድማው በመግፋት ምግብ አልቀበልም በማለቱዋ እያለቀስኩ ምግቡን ይዤ ተመለስኩ ብለዋል።

በቅርቡ በሙስና ተከሰው ወደ እስር ቤት የተላኩት ኮሎኔል ሀይማኖት በርእዮት ላይ የስድብ ናዳ ሲያወርዱባት በማደራቸው ርእዮት እንቅልፍ አጥታ ማደሩዋንና ብትሞትም በበሽታ ሳይሆን በእነሱ ምክንያት መሞቱዋን እንዲያውቁት እንደነገረቻቸው ወ/ሮ አሰለፈች ተናግረዋል

ኮሎኔል ሀይማኖት ከርእዮት ጋር እንደማይተዋወቁ ወ/ሮ አሰለፈች ገልጸው፣ ኮሎኔሏ አቤኔዘር ከምትባለዋ የእስር ቤቱ የሴቶች ሀላፊ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዳላቸውም ገልጸዋል

በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ ተወካዮች ርእዮትን ለመጠየቅ ቃሊቲ ቢገኙም እንዳያገኙዋት መከልከላቸው ይታወቃል። የማረሚያ ቤት ሀላፊዎችን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።