የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሃፊ አቶ አስራት ጣሴ በበኩላቸው፣ የፓለቲካ ምህዳሩ መጥበቡን፣ የሠላማዊ ትግል ተስፋ መዳፈኑንና ህገ መንግስቱ እየተከበረ አለመሆኑን እንዳስረዱ ጠቅሰው፤ በነፃው ፕሬስ ህግ፣ ተሻሽሎ በወጣው የፓርቲ ህግ፣ በፀረ ሽብርተኛ አዋጁ ዙሪያ እንደተወያዩበት ተናግረዋል። በ2002 ዓ.ም. ምርጫ በዝርፊያና በንጥቂያ ኢህአዴግ 99.6 በመቶ ድምፅ አግኝቶ ማለፉን በመጥቀስ፤ 2007ዓ.ም. የሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ አጣብቂኝ እንደሆነብን ለአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት አስረድቻለሁ ብለዋል - አቶ አስራት፡ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህዝቡን ሰብስበን ማነጋገር፣ ሠላማዊ ሰልፍ ማድርግ እንዳልቻልንም፣ የመንግስትን ጫና በማሳየት ገለፃ አድርጌያለሁ በማለት አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡ የአውሮፓ ህብረት አባላት ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትም ጋር ቀደም ብለው ውይይት ማድረጋቸውን የተናገሩት አና ጎሜዝ፣ አገሪቱ በኢኮኖሚ ማደጓለ እንደሚገልፅና ልማቱ ግን ህዝቡን ከድህነት ያላወጣ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በ2007 ዓ.ም. ለሚደረገው አገራዊ ምርጫም ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አና ጐሜዝ ገልፀው፤ ታዛቢዎችን ከመላክ በተጨማሪ በየሁኔታው እና በየወቅቱ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ መድረክ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በውይይቱ ላይ ተካፋይ እንደነበሩ ታውቋል፡፡
Source: Addis Ademas
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar