torsdag 23. januar 2014

በአንድነት እንነሳ!!!

አምባገነኑና ዘረኛው የወያኔ ስርአት ወደ ስልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ በሃገራችን ያለው የፍትህ የዲሞክራሲ እና የሉአላዊነት ጥያቄ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንጂ እየተሻሻለ ሲመጣ አይተን አናውቅም።  ይህ መንግስት ያሉትን ችግሮች ሲያባብስ እና የኢትዮጵያን ህልውና ጥያቄ ውስጥ ሲከት እንጂ ሲያስተካክል ያየንበት ጊዜ የለም። ያስቀመጠውን ህገ- መንግስትም ሲጥስና ሲንድ እንጂ ሲያስጠብቅም አላየንም ለዚህም እየጨመረ የመጣው የሙስና መስፋፋት፣ የአንድ ዘር የበላይነት፣ በአሸባሪ ስም የፓለቲካ እስረኞች ቁጥር መጨመር፣ በህገ-መንግስቱ የተፈቀደውን ሠላማዊ ሠልፍ መከልከል፣ የህዝብ መብት አፍኖ የመናገርና የመፃፍ መብት መከልከል፣ የህዝብ መፈናቀል መሬትን ለባዕዳን ሀገሮች መቸብቸብ፣ የኑሮ ውድነት መስፋፋት፣ ጣልቃ መግባት ለዜጐች አለመቆርቆር የመሣሠሉት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የመጡ ነገሮች ናቸው እነዚህ ደግሞ በቅርብ በዓለም ዓቀፍ ሠብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ተረጋግጠዋል።

በቅርብ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሠር ሁለተኛ መሆኑዋ የሠማነው ነገር ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህና ሌሎችም በርካታ ችግሮች እያሉ ብሎም እየተባባሡ አምባገነኑ መንግስት ስልጣኑ ላይ ተቆናጦ ይገኛል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ብሎ መመርመሩ ተገቢ ነው። መንግስትን መንግስትነቱን ካለ ህዝብ ፍላጐት በጉልበቱ እየቀጠለ እንዳለ አጠያያቂ አይደለም። ሌላው ዓምባገነኑ መንግስት ችግሮችን እያባባሠም በስልጣን ለመቀጠሉ ትልቍን ሚና የሚጫወተው የህዝብ አንድ ሆኖ በቆራጥነት ሃገር ጎጂ አፍኝና ዘረኛ የሆነውን መንግስት ለማስወገድ አለመነሣት ነው፡፡

እዚህ ላይ በቅርብ በሳውዱ አረቢያ ያሉ ዜጐቻችን ላይ የደረሠውን አሣፋሪ በደል አስመልክቶ በተለያዩ ሃገራት ያሉ ኢትዮጲያውያን ያሣዩትን የወገንና የሃገር መቆርቆር ማየት እንችላለን በዚህ የወገን የድረሡልኝ ምላሽ በተለያዪ ዓለማት ያሉ ኢትዮጲያዊያንና ወዳጆች ካለምንም የሃይማኖት የብሄር የቋንቋ ልዩነት በአንድነት ሆነው ምላሽ ሠጥተዋል በዚህም ቢያንስ በኢትዮጲያና በሣዑዲ ዓረቢያ ታፍኖ ሊቀር የነበረውን ችግር በአደባባይ አውጥተዋል። በሳውዲ በሚገኘው ህዝባችንም የሚቆረቆርለት መንግስት ባይኖረውም የሚቆረቆርለት ወገን እንዳለው አሳይቷል። ለህዝብ ደንታ የሌለው የወያኔ መንግስት በግድ ሳውዲአረቢያ ወደ ሚገኘው ህዝባችን ፊቱን እንዲመልስ ተገዷል። እነዚህ ጥቂት ነገሮች ሊሆኑ የቻሉት በሃገር ውስጥ ያለው ህዝባችን በገዛ ሃገሩ ለወገኑ ድምጹን ለማሰማት ቢከለከልም በተለያዩ አለማት ያሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ አንድ ሆነው ድምጻቸውን ማሰማት በመቻላቸው ነው። ከዚህ የመንማረው ዛሬም የኢትዮጵያ ህዝብ ካለምንም የቋንቋ የብሄር የሃይማኖት ልዩነት በፍጹም የሃገር ፍቅር በቆራጥነት እና በአንድነት ከተነሳን ይህን አሳፋሪ እና አምባገነን መንግስት የማናስወግድበት ምክነያት የለም። መንግስት ለእድሜ ማራዘሚያ ያስቀመጠልንን በብሄር እና በሃይማኖት የመለያየት መርዝ
አስወግደን አንድ ሆነን መነሳት የኢትዮጲያን ውድቀት እና የወገን እንግልት ያሳስበናል የመንል ሁሉግዴታችን ነው።

  http://ethiolion.com/Pdf/01212014Enenesa.pdf

http://quatero.net/pdf/eden.pdf

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar