fredag 7. februar 2014

አቶ አስራት ጣሤ ታሰሩ

አቶ አስራት ጣሤ ታሰሩ

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ፣ በክስ ሂደት ላይ የነበረው የአኬልዳማ ዶክመንተሪ በድጋሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መታየቱን ተከትሎ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ከፃፉት አስተያየት ጋር በተያያዘ “ዘለፋ አዘል ጽሑፍ” ጽፈዋል በሚል ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ በተላለፈባቸው መሰረት በዛሬው እለት በፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የተገኙ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ለ7 ቀን ታስረው በቀጣዩ ሳምንት እንዲቀርቡ በማለት የእስር ትዕዛዝ ወስኖባቸዋል ፡
ኢህአዴግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱ ተጋለጠ::
ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ 4 አመራሮችና አባላት እንዲታሰሩ ኢህአዴግ ወስኗል፤ የክስ ቅድመሁኔታዎች በፍርድ ቤት መጠናቀቃቸውን ታውቋል፡፡
ኢህአዴግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱን የፍትህ ሚ/ር ምንጮች አጋለጡ፡፡ ምንጮቹ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት በኢህአዴግ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ክስ እንዲከፈትባቸውና እንዲታሰሩ የተወሰኑት የአንድነት አባላት በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም የመጀመሪያው ዙር ክስና እስር በ4 አመራሮችና አባላት ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar