July14/2014
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (ሁማን ራይት) ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ባሰራጨው ዜና የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከእንግሊዝ ለኢትዮጵያ ዕርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች በሙሉ (የእንግሊዝ መንግሥትንም ጨምሮ) ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ቅድምያ መስጠታቸውን እና አለመስጠታቸውን በሚያጣራ መልኩ ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግ ያሳለፈውን ውሳኔ ''ጠቃሚ እርምጃ'' በማለት አሞካሽቶታል።
ውሳኔው በተለይ በቅርቡ ከአርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ መታገት በኃላ የእንግሊዝ መንግስት ''የባህር ማዶ የልማት ትብብር ድርጅት'' (UK Department for International DEVELOPMENT
(DFID) ) ለኢትዮጵያ መንግስት የገንዘብ ድጎማ ሊያደርግ የነበረ ከመሆኑ አንፃር የዛሬው ውሳኔ ከፍተኛ መልዕክት ማስተላለፉ አይቀርም።በሌላ በኩል የዛሬው የፍርድቤቱ ውሳኔ ይሄው የልማት ድርጅት (DFID) በበቂ ሁኔታ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ ይዞታ ጉዳይ አለመመርመሩን ጠቁሞ በእዚሁ አዲሱ የፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግበት ማዘዙን ያብራራል።
የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የእርምጃውን ፋይዳ ሲያስረዳ የድርጅቱ የአፍሪካ ክፍል ተጠሪ የተናገሩትን በመጥቀስ ነው።እንዲህ ይነበባል -
''የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድቤት ውሳኔ ለሌሎች መንግሥታት እና እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የማንቅያ ጥሪ ነው።ምክንያቱም ሀገራትም ሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሚሰጡትን የልማት ፕሮግራም ሁሉ ቅድምያ ከሰብዓዊ ይዞታ አንፃር እንዲመለከቱ ያደርጋል''ይላል።
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (ሁማን ራይት) ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ባሰራጨው ዜና የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከእንግሊዝ ለኢትዮጵያ ዕርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች በሙሉ (የእንግሊዝ መንግሥትንም ጨምሮ) ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ቅድምያ መስጠታቸውን እና አለመስጠታቸውን በሚያጣራ መልኩ ሕጋዊ ምርመራ እንዲደረግ ያሳለፈውን ውሳኔ ''ጠቃሚ እርምጃ'' በማለት አሞካሽቶታል።
ውሳኔው በተለይ በቅርቡ ከአርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ መታገት በኃላ የእንግሊዝ መንግስት ''የባህር ማዶ የልማት ትብብር ድርጅት'' (UK Department for International DEVELOPMENT

የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የእርምጃውን ፋይዳ ሲያስረዳ የድርጅቱ የአፍሪካ ክፍል ተጠሪ የተናገሩትን በመጥቀስ ነው።እንዲህ ይነበባል -
''የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድቤት ውሳኔ ለሌሎች መንግሥታት እና እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የማንቅያ ጥሪ ነው።ምክንያቱም ሀገራትም ሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሚሰጡትን የልማት ፕሮግራም ሁሉ ቅድምያ ከሰብዓዊ ይዞታ አንፃር እንዲመለከቱ ያደርጋል''ይላል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar