ሰሞኑን
ኢህአዴግ በፈለፈላቸው ድርጅቶች ታጅቦ የ”ባንዲራ ቀን” በሚል የመለስን ፈረጀ ብዙ ዝክር ሊደግስ ከወዲያ ወዲህ
እያለ ነው። አቶ መለስ “ጨርቅ” ብለው ሲያነሱና ሲጥሉት የነበረውን ያገር መለያ ለፈጠራና ከጀርባው ተንኮል ያዘለ
ዓላማቸው ሲሉ ቀኑ እንዲዘከር አድርገዋል፤ የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈጻሚ እንደመሆናቸውም የታዘዙትን በሠንደቅ
ዓላማው ላይ ጨምረዋል። በዚሁ የ”ባንዲራ ክብር” ሳይሆን በሌላ አህጉራዊ ክስተት ራሳቸው ያሰፉትን ጨርቅ ገልብጠው
ባደባባይ ሰቅለውት ነበር። በወቅቱ ራሳቸው ያሰሩትን ባንዲራ አናትና ግርጌ መለየት ባለመቻላቸው ተወግዘውበታል፤
የትግራይን ቢሆን እንዲህ ያደርጉት ነበር ተብሎም ተጠይቋል።
ባድመ
ስትወረር “ደርግ ኢሰፓ” ተብለው ጎዳና ላይ የተጣሉት የቀድሞው ሰራዊት አባላት ለዳግም ዘመቻ “እናት አገር ጥሪ”
ሲተም በገጸ በረከትነት የተሰጠው ያደራ ቃል ኪዳን ይኸው “አታስፈልግም ጨርቅ ነህ” የተባለው መለያ ነበር። ሲፈልጉ
የሚጥሉት፣ ሲጨንቃቸው የሚያነሱት መከረኛ ባንዲራ ዳግም አጀንዳ ሆኖ ሰሞኑንን ቀርቦልናል።

ዋሽንግተን
በሚገኘው የኢህአዴግ ጽ/ቤት ውስጥ የመዋቅሩ “መሪ” ተብለው የተቀመጡትን ግርማ ብሩን ለማነጋገር እንደመጡ
የሚናገሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ወዲ ወይኒ ጥይት ሲተኩሱ ተሰምቷል። ታይቷል። ተረጋግጧል! በኢትዮጵያ ስም የተሰቀለው
የህወሃት/ኢህአዴግ ዓርማ ወርዷል! በዚሁ በፊልም ተደግፎ በቀረበው ዜናና የማህበራዊ ገጽ ዓምዶች ላይ ዋሽንግቶን
ከተማ ከዋይት ሃውስ 4 ማይል ርቀት ላይ በሚገኘው የኢህአዴግ ግቢ ውስጥ ተሰቅሎ የነበረው “ጨርቅ” ወርዶ ተጥሏል።
“የጨርቁ ፍቅር ያቃጠለው” የጽህፈት ቤቱ ሰራተኛ የተጣለውን “ጨርቅ” ሰብስቦ ወደ ቢሮ ሲያስገባም ከካሜራ እይታ
አላመለጠም። እንግዲህ ይህንን እውነት ነው ለመካድና “ከዓይናችሁ ጆሯችሁን እምኑ” እየተባልን ያለነው።
በሌላ
በኩል የህዝብ ቀልብ ለመሳብ “ባንዲራ ያዋረዱ” በሚል “ኢህአዴግ በፈቃዱ ያሰራውን ጨርቅ” አውርደው የጣሉትን
ለመክሰስና ከሃዲ አድርጎ ለመሳል ተሞክሯል፤ ሙከራውም ቀጥሏል። ሁኔታውን የሚከታተሉ እንደሚሉት “ይህ የኢትዮጵያ
ባንዲራ ነው” በማለት የሚጠሩትን ጨርቅ “ይህ የእኔ ባንዲራ አይደለም” በማለት ቀዳደው የሚጥሉ ዜጎች በምን ሂሳብ
ተቃውሞ ይሰነዘርባቸዋል የሚል ጥያቄ እያነሱ ነው።
ህወሃት
ትግራይን ነጻ ለማውጣት ትግል ጀምሮ፣ በወቅቱ ደርግ በነበረው የአመራር ጥበብ እጥረትና ሌሎች ተጽዕኖዎች ከአገዛዝ
መንበር ተነስቶ ህወሃት/ኢህአዴግ አገር ገዢ ለመሆን ሲታደል የአገሪቱን ባንዲራ “ጨርቅ” ብሎ አዋርዶታል። የቀለብ
መቋጠሪያው እራፊ አድርጎ ክብሩን ገፎታል። ባደባባይ አገርና ህዝብ እየተቃወመ በጠብ መንጃ ሃይል አስወግዶታል፤
አቃጥሎታል። ራሱ ባሰፋው ሌላ “ጨርቅ” ተክቶበታል። ይህ የሸፍጥ ታሪክና ተግባር የተረሳ ተደርጎ ዛሬ
ህወሃት/ኢህአዴግ ደርሶ ለሠንደቅ ዓላማ ክብር ሰጪ ሆኖ ሙግት መግጠሙ ጥያቄውን የሚያነሱ ክፍሎች ተግባሩ
“ያቅለሸልሻል” ባይ ናቸው።
“አገር
የነሱ መፈንጫና ሃብት ማግበስበሻ የሆነችላቸው የድጋፍ ቀረርቶ ለማሰማት ቅድሚያ ቢይዙ፣ አገር የላችሁም፣ ባንዲራ
አልባ ናችሁ፣ የተባልን የነሱ የሆነውን ጨርቅ አንፈልግም ብንል ምን ይገርማል?” የሚሉት ክፍሎች፣ “በሎንደን
የኤርትራ ኤምባሲን ዘልቀው ለሰዓታት የተቆጣጠሩት አምባገነን በሚባሉት የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ “ዲፕሎማቶች”
ጥይት አልተተኮሰባቸውም። ኢሳያስን አምባገነን በማለት የኤርትራን ህዝብ “ነጻ” አወጣለሁ የሚለው ህወሃት ግን በወዲ
ወይኒ አማካይነት ህግ ባለበት አገር የህወሃትን ማንነት ባደባባይ አሳይቷል። “እዛው ህወሃት በሚነዳት አገር ውስጥ
ቢሆን ኖሮ ስንቱን ይረሽን ነበር” ሲሉም የሚጠይቁ አሉ። እነዚህ ክፍሎች “አገር ቤት የተረሸኑትንና ታስረው
የሚሰቃዩትን ቤት ይቁጠራቸው” ሲሉ ተደፈርን በሚል ስሜታቸውን የሚያንጸባርቁትን ወገኖች “ወዮልኝ ቀን ያጋደለ
እለት” በሚል ምጸት ጥርሳቸውን ይነክሱባቸዋል።
http://www.goolgule.com/degraded-meles-sebhat-eprdf-whats-next/?utm_content=fbshare-js-large&utm_campaign=&awesm=fbshare.me_dR51&utm
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar