
በመከላከያ ሚኒስትር ስር የሚገኘው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ/ሜቴክ)፣ሲጀምር አስራሁለት የሚደርሱ የተለያዩ ከደርግ/ወታደራዊው መንግስት በተወረሱ ፋብሪካዎችን ሥራ የጀመረ ድርጅት ነው፡፡ ሜቴክ በ2010 እኤአ በአስር ቢሊዩን (10,000,000,000)ብር መነሻ ካፒታል የተመሠረተ ድርጅት ነው ይሉናል፡፡ በአሁኑ ግዜ በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ዘመን ከስባ አምስት ፋብሪካዎች በላይ ያሰባሰበ ድርጅት ለመሆን ችሎል፡፡ ሜቴክ ኮርፖሬሽን ከ13,000 ሠራተኞች ሲኖሩት ከነዚህ ውስጥ 1,000 ዎቹ ማሃንዲሶች ናቸው፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሃገሪቱን የኢኮኖሚ ትስስር መሪ ዶክተር ደብረፂዋን ገብረሚካኤል ሜቴክ በሃገር ውስጥና ከባህር ማዶ ሃገራት የቢዝነስ አጋሮቹ ጋር በመሆን ወደሃገር ውስጥ የሚገቡ ምርትና ሸቀጦችን በመተካት የውጭ ምንዛሪ ለማዳን ሜቴክ ይንቀሳቀሳል ቢሉም ሜቴክ የሰራው ምርትና ያዳነው የውጭ ምንዛሪ ደፍረው አልገለፁም፡፡ ሜቴክ መንግስታዊ ሞኖፖሊ እንደሆነ የግሉን ዘርፍ ስራ እየነጠቀ እንደሆነ ዶክተሩ የሚመሩት ቴሌኮም ከዓለማችን ካሉ ሃገራት የመጨረሻ ተርታ ውስጥ መሆኑን መረዳት የተሳናቸው ኢንተርኔት አጠቃቀም ባለመቻላቸው ነው ተብለው ይታማሉ፡፡
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar