torsdag 31. oktober 2013

የጉዲፈቻ ልጃቸውን የገደሉ ተፈረደባቸው

ኣንዲት የጉዲፈቻ ልጃቸውን ኣሰቃይተው ለሞት ያበቁ ባልና ሚስት አሜሪካውያን ከ28 እስከ37 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተፈረደባቸው።
Bild I: Adoptiveltern in USA Höchststrafen für Hunger und Unterkühlung Tod von Teenager-Mädchen aus Äthiopien erhalten 2910 2013
Titel: Hana Williams - Larry Williams und Carri von Sedro-Woolley, Washington wurden für schuldig befunden, Vernachlässigung, Missbrauch und schließlich Tötung der 13-jährigen Hana Williams aus Äthiopien.
Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn DW Bonn - 2013
Schlagworte: Hana Williams´s Grab in Washington State - Seattle
የ13 ዓመትዋ ሐና ዊሊያምስ ህይወቷን ያጣችዉ በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር ግንቦት 12 ቀን 2011ሲሆን ከትናንንት በስተያ ማክሰኞ ዕለት ያስቻለው የሲኣትል ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ ሚስት ወ/ሮ ካሪ ዊሊያምስ 37 ዓመት እና ባል ላሪ ዊሊያምስ ደግሞ 28 ዓመት እንዲታሰሩ ፈርዶባቸዋል።
ካሪ እና ላሪ ዊሊያምስ ኣንድ ሌላ እትዮጵያዊ የጉዲፈቻ ልጅን ጨምሮ ስድስት አብራካቸዉ የተገኙ ልጆችም ኣሏቸው።
በ ዩኤስ አሜሪካ ከሴኣትል በስተ ሰሜን 60 ማይልስ ወይንም 100 ኪ ሜ ላይ በምትገኘው መለስተኛ ከተማ ሲድሮ ዊሊ ነዋሪ የሆኑት ካሪ ዊሊያምስ እና ባለቤትዋ ላሪ ዊሊያምስ የራሳቸው 6 የአብራክ ልጆች እያላቸው ከእነዚህ በተጨማሪ ያኔ ሐና ዓለሙ ትባል የነበረችውን ሙዋች ሐና ዊሊያምስን እና የጉድፈቻ ወንድምዋን ዒማኑዔል ዊሊያምስን ከኢትዮጵያ በጉድፈቻ ያመጡኣቸው እ ኣ ኣ በ2008 ዓ,ም ሲሆን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የትምህርት ክፍል ኣስተባባሪ ወ/ሮ መታሰቢያ ሙሉጌታ እንደሚሉት ህጻናቱ ከጉዲፈቻ ቤተሰቦቻቸው ጋር በሰላም የኖሩት የመጀመሪያውን ዓመት ብቻ ነው።
ሀና ዊሊያምስ ሞታ የተገኘችው በ3ኛ ዓመትዋ መሆኑ ነው ኣሁንም እንደ እ አ ኣ ግንቦት 12 ቀን 2012ዓ ም ሲሆን ኣሙዋሙዋትዋም ወ/ሮ መታሰቢያ እንደሚሉት የምግብ እጥረትን ጨምሮ ተደብድባ መሆኑን ኃኪሞች መስክረዋል።
Bild I: Adoptiveltern in USA Höchststrafen für Hunger und Unterkühlung Tod von Teenager-Mädchen aus Äthiopien erhalten 2910 2013
Titel: Hana Williams - Larry Williams und Carri von Sedro-Woolley, Washington wurden für schuldig befunden, Vernachlässigung, Missbrauch und schließlich Tötung der 13-jährigen Hana Williams aus Äthiopien.
Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn DW Bonn - 2013
Schlagworte: Hana Williams´s Grab in Washington State - Seattle
በመካከሉ ጉዳዩ እንደ መቀዛቀዝ ማለቱ ባይቀርም የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ባለመታከት ባደረጉት ክትትል የችሎቱ ሂደት እንደገና ተፋጥኖ ባለፈው ማክሰኖ በዋለው ችሎት ኣንደኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ካሪ ዊሊያምስ በ37 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ተፈርዶባታል። 37 ዓመት በአሜሪካ የመጨረሻው ረጅሙ ቅጣት ሲሆን ዳኛ ሱዛን ኮክ እንደሚሉት እንዲያውም ወንጀለኛዋ እድሜዋ ከፈቀደ ከዚያም በላይ በወህኒ ቤት ልትቆይ ትችላለች።
2ኛው ተከሳሽ እና የቦይንግ ኣውሮፕላን ፋብሪካ ሰራተኛ የሆነው ባል ላሪ ዊሊያምስ ደግሞ የ28 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል። የሁለቱም ክስ ከሀና ዊሊያምስ ግድያ በተጨማሪም የወንድሙዋ ዒማኑዔል ዊሊያምስ በደል እና ድብደባንም ያካትታል።
ሁለቱ ወንጀለኛ ጥንዶች ከችሎት በቀጥታ ወደ ወህኒ ከተላኩ በኃላ ዒማኑዔል ዊሊያምስን ጨምሮ ስድስቱ የአብራክ ልጆችም ወዲያውኑ ለጉድፈቻ ተቋም መሰጠታቸውም ታውቀዋል።

ሰርካለም ፋሲል እጅግ ልብ የሚነካ ደብዳቤ እስር ቤት ለሚገኘው እስክንድር ነጋ በድምጽ ላከች።

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ከ3ወራት ዝምታ በኋል ተነፈሰች። እጅግ ልብ የሚነካው የሰርካለም መልዕክት ዛሬ በኢሳት ሬዲዮ ላይ ታገኙታላችሁ። በ3 የደህንነት ሃይሎች መሃል አዲስ አበባ ላይ የታፈኑት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ አበበ አካሉ መናገር የማልፈልገውን ፈጸሙብኝ ይላሉ። ለባሌቤቴም ለልጆቼም አልተናገርኩም። ሆድ ይፍጀው! አሉ። ምን ይሆን?

aaa

onsdag 30. oktober 2013

ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳንኞች እየተሸጠ ነው

ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳንኞች እየተሸጠ ነው
ከደቡብ ጎንደር : ከምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም : ከሴሜን ወሎ ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚመጡ ወገኖቻችን ባሰሪወቻቸው አና ባካባቢው በዚህ ሥራ በተሰማሩ ( የትግራይ ተወላጆች ) ግፍ እየተሰራባቸው ነው :: ባለፉት 2 ወራት ብቻ የ16 ሰወች አስከሬን በተለያየ አካባቢ ወድቆ የተገኘ ሲሆን ጎዳዩን ቀለል በማድረግ እና እውነቱን ሰው እንዳይገነዘብ ሲባል የተለያዩ መላምቶች በመንግስት ሆን ተብሎ ተሰጦታል ::
ለምሳሌ በአንድ ሳምንት ዉስጥ በተደጋጋሚ የተፈፀመውን እሄን ድርጊት በቀጥታ በብሔሮች መካከል በተነሳ ግጭህት ( የወሎ እና የጎጃም በሚል ) እርስ በርስ በጩቤ እየተዋጉ ነው በማለት ጉዳዩን አድበስብሶት የቀረ ሲሆን ሌሎች ገለልተኛ ሚዲአወችም እሄንኑ በማስተጋባት እውነቱ ተደብቆ ወንጀሉ ግን ቀጥሏል ::
በሁመራ ከተማ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ የህገወጥ መሳሪያ ዝውውር በስፋት የሚፈፀም ሲሆን በዚህ ሥራ የተሰማሩት ሁሉም የትግራይ ተወላጆች ከሱዳኖች ለሚቀበሉት መሳሪያ ክፍያ እንዲሆን የሚሰጠው የገበሬወችን ኩላሊት ነው ::
እንዲህ አይነት ሥራ በሱዳን በኩል ወደ እስራኤለ በህገወጥ መልኩ የሚጉዓዙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለ እንደሆነና አልፎ አልፎም በሱዳን በገድሃሪት እና አጎራባች አካባቢወች ድረስ በመምጣት ካምፕ ዉስጥ በመግባት ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች አፍኖ በመያዝ ብዙ እሺ ዶላር በማስከፈል ይለቁአቸዋል መክፈል ያልቻሉትን ግን ኩላልታቸውን በማውጣት ለእልፈተሞት ይዳረጋሉ ::
ለወገኖቻችን እንድረስላቸው !!
የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ
ሰሜን ጎንደር

fredag 25. oktober 2013

የአንድነት አመራር አፈና እና ድብደባ ተፈጸመባቸው

የአንድነት አመራር አፈና እና ድብደባ ተፈጸመባቸው ——————————- የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና በሚሊዩኖች ድምጽ ለነጻነት ሕዝባዊ ንቅናቄ በተለያዩ ከተሞች በመንቀሳቀስ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉት መምህር አበበ አካሉ ትናንት 14/02/06 ዓ.ም የደህንነት መስሪያ ቤት አባላት ነን ባሉ ሶስት ቅጥረኞች የግድያ ሙከራና አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ለፍኖተ ነጻነት ይፋ አድርገዋል፡፡ ሰላማዊው ታጋይ እንደተናገሩት በምሳ ሰዓት ኮተቤ መሳለሚያ አካባቢ ለስራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ ህገ ወጦቹ ያካራክሯት የነበረችን ላንድክሩዘር መኪና የእግረኛ መንገድ እንድትዘጋ በማድረግ አቶ አበበን በሀይል በመኪናው በመጫን ወደማያውቁት ሰዋራ ቦታ በመውሰድ ቤቶች በሚሰሩበት አካባቢ ከመኪናዋ በማውረድ ሺሚንቶ ላይ በማስተኛት በሰላማዊ መንገድ የሚያካሂዱትን ትግል እንዲያቆሙ ይህ ካልሆነም‹‹ በሽብርተኝነት በመወንጀል መንግስትን በሀይል ለማውረድ ትሰራለህ›› በማለት እንደሚወነጅሏቸው በመንገር በቃላት ለምግለጽ በሚቸግር ሁኔታ ድብደባ እየተፈራረቁ እንዳካሄዱባቸው ተናግረዋል፡፡ መምህር አበበ ከቀኑ 6፡30 እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ግለሰቦቹ ሽጉጥ ደግነውባቸውና የማያውቁትን የአልኮል ቃና ያለው ፈሻሽ ነገር በመጋትና ከሲሚንቶ ጋር አጣብቀው በመርገጥ የግድያ ሙከራ ካደረጉበቫቸው በኋላ ከምሽት ላይ በመኪና አውጥተው እንደጣሏቸው ለፍኖተ ነጻነት ተናግረዋል፡፡ ፍኖተ ነጻነት ፓርቲው አመራሩ በህገ ወጥ መንገድ መያዛቸውንና መደብደቡን በተመለከተ ምን እያደረገ ነው በማለት የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች በመጠየቅ ከአመራሮቹ ‹‹ጉዳዩን በማጣራት ላይ እንገኛለን፡፡አውሬነት የተሞላበትን አስነዋሪ ድርጊትም በቸልታ የምናልፈው አይሆንም››የሚል ምላሽ አግኝታለች፡፡ መምህር አበበ አካሉ በአሁኑ ወቅት በመኖሪያ ቤታቸው ተኝተው ይገኛሉ፡፡ ሰላማዊው ታጋይ ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባት ናቸው፡፡

ሲኖዶሱ የፓትርያርኩን ውሳኔ አስቀየረ


ቅዱስ ሲኖዶሱ በትናንትናው የስብሰባ ውሎው ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ በአብላጫ ድምጽ ወስኖባቸው የነበሩት የአዲስ አበባው ሊቀ ጳጳስ አቡነ እስጢፋኖስ በዛሬው ዕለት ፓትርያርኩ አቡነ ማቲያስ ‹‹አዲስ አበባ የእኔ ልዩ ሐገረ ስብከት በመሆኑና ማንም ሊያዝበት ስለማይችል ሊቀ ጳጳሱ በቦታቸው እንዲቀጥሉ በመወሰን የትናንቱን ውሳኔ ሽሪያለሁ››ማለታቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
ስብሰባው ከሰዓት በኋላ ቀጣዩን አጀንዳ በማንሳት ከመወያየቱ በፊት ተቃውሞ እንዳላቸው የገለጹ ጳጳሳት ፓትርያርኩ የሲኖዶሱን ውሳኔ በመሻር ሊቀ ጳጳሱን በመንበራቸው እንዲቀጥሉ ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ የቤቱን ውሳኔ እንዲያከብሩ ጠይቀዋል፡፡
ፓትርያርኩም በመጨረሻ የሲኖዶሱን ውሳኔ የመጨረሻ በማድርግ መውሰዳቸውን በመግለጽ አቡነ እስጢፋኖስ በሲኖዶሱ ውሳኔ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ሲኖዶሱ በነገ ውሎው በአቡነ እስጢፋኖስ ቦታ ሌላ ሊቀ ጳጳስ ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት

ወያኔ ወደ ሙኒክ መጥቷልና ወገን ተዘጋጅ!!!!!!!!!



ወያኔን መደገፍ ማለት በወገኖችዎ ላይ የሚደርሰውን ይህን ግፍ መደገፍ መሆኑን ይገንዘቡ!!









የወያኔን የዘረፋ ጉዞ ተባብረን እንግታ!!

የወያኔ ቁንጮ የነበረው መለስ ዜናዊ ከሚስቱ ጋር በመሆን ከዘረፉት በላይ ለመዝረፍ በነደፉት የአባይ ግድብ እቅድ ሳቢያ በውጭ ሃገር ካለው ወገናችን ጉልበት በዝባዥ የሆነውን የፈረንጅ ሃገር ስራ ተጋትሮ ያገኛትን ለመመንተፍ የመለስ ውሾች የሆኑት ካድሬ ተብዬዎች ላይ ታች ሲንጠራወዙ ሁለት ዓመት ሆናቸው። ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንም እነዚህን ተላላኪ አሽከሮች በየደረሱበት እያሳደዱ ስብሰባ ብለው የጠሩትን ሲያከሽፉ፣ እግሬ አውጭኝ ሲያስሸመጥጡ፣ የእነርሱን ባንዲራ እያነሱ እውነተኛ የኢትዮጵያ ባንዲራ ሲሰቅሉ፣ ወያኔዎቹ የተከራዩትን አራሽ ተቆጣጥረው የራሳቸውን ስብሰባ ሲያካሄዱ፣ ወዘተ ወዘተ ብዙ ገድል አይተናል። ካድሬዎቹ ውሾች ግን ወትሮም የሰውነት ክብር የላቸውምና በደረሰባቸው ተደጋጋሚ ውርደት ተሸማቀው አርፈው አልተቀመጡም።

እየተሽሎኮለኩና እያደቡ ከዳያስፖራው የውጭ ምንዛሪ ለመንጠቅ ዛሬም የሞት ሞታቸውን ያገኙትን ሁሉ ከመቧጠጥ አላረፉም። በዚህም መሰረት በመጪው ኖቬምበር 02/2013 በጀርመን ሙኒክ በአባይ ቦንድ ስም ዩሮ ለመሰብሰብ እየተጠራሩ መሆኑ ተደርሶበታል። በመሆኑም በሃገሩ ጉዳይ የሚንገበገብ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከቅርብም ከሩቅም ወደ ሙኒክ እንዲከትና የወያኔን ዘረፋ በተለመደው መልኩ እንዲያከሽፍ የተቃውሞ አስተባባሪ ግብረ-ኃይሉ ወገናዊ ጥሪውን ያስተላልፋል።

በእለቱ በሚደረገው ተቃውሞ የተለመደው የወያኔን የዘረፋ ተግባር ከመግታት በተጨማሪ ትናንት የወያኔ መንግስት በደል እንደፈጸመባቸው አመልክተው የስደት ተገን ያገኙና ዛሬ ከወያኔ ጎን ተሰልፈው ለወገኖቻችን ስቃይና ሞት ተባባሪ የሆኑ ለጥቅምና ለሆዳቸው ያደሩ ባንዳዎችን ፎቶ በማንሳትና ቪዲዮ በመቅረጽ ስደት ላመለከቱበት ሃገር መንግስት የማጋለጥ ስራ በሰፊው ይሰራል። ሁላችንም በ02/11/2013 ጀርመን ሙኒክ ተገናኝተን የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ።

ወያኔን ለምን እንደምንቃወም እናውቃለን።

*     በስርዓቱ ደባ እየፈራረሰች ስላለችው ሃገራችን

*     በየጊዜው ስለሚጨፈጨፉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን

*     መሬታቸውና እየተነጠቁ ስለሚፈናቀሉ ወገኖቻችን

*     በየእስር ቤቶቹ ስቃይና መከራን እየተቀበሉ ስላሉ ወንድም እህቶቻችን

*     የካድሬ መፈንጫ ስለሆኑት የሃይማኖት ተቋሞቻችን

*     ታሪክ አልባ ስለተደረገው ሃገራዊ ማንነታችን

*     ስለምንናፍቀውና በወያኔ ስለተዘረፈው የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት

*     ስለተረገጠው፣ ፍትህ፣ ነፃነትና እኩልነታችን ወዘተ ወያኔንና በስሙ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ያለማቅማማት እንድንቃወም ያስገድደናል።

ለወያኔ ያደሩ ሆድ አደር ባንዳዎችም ወያኔ ለሚያፈሰው እያንዳንዱ የደም ጠብታ አስተዋጽኦዋቸው መቼም የማይረሳ ስለሆነ ለተጠያቂነታቸውም ጠንክረን እንሰራለን!!

በሙኒክ ለተዘጋጀው የወያኔ ዘረፋ ሁኔታዎችን እያመቻቹ ያሉትን በቅርብ ቀን ፎቶዎቻቸውንና ስማቸውን ለኢትዮጵያውያን ይፋ እናደርጋ

Source; ECADF

onsdag 23. oktober 2013

Ethiopians in Norway vowed to stand beside Ginbot 7 popular force

123
On 28th of September 2013, successful fundraising was conducted for Ginbot 7 Popular Force (G7pf), recently established and struggling against the woyane junta. The fundraising event, staged from 4:00 – 12:00 p.m. local time, was coordinated by a taskforce established by Democratic Change in Ethiopia Support Organization in Norway (DCESON). The event was able to attract many participants from all over Norway and other European countries. The event was one of the success stories in the history of fundraising in terms of both participation and raised amount of money.
The official announcement of the founding of the Ginbot 7 people`s force has been a positive development and was welcomed by most Ethiopians living in Norway. Ginbot 7 popular force has added a momentum to the struggle and elevated the moral and hope of many Ethiopians living in Norway. The formation of this force marks a new and decisive phase in the struggle against the racist and fascist rule of the Tigray People`s Liberation Front (TPLF) in Ethiopia. Hence, the enthusiasm, inspiration and increased degree of engagement that were witnessed during the event reflected the aspirations and commitments of the participants. Besides, it shows that the force has been able to garner an increasing and widespread support in Norway and inevitably in other parts of the Diaspora at the moment.
The DCESON has been supporting the struggle for democracy, freedom and justice in Ethiopia starting from the pre-kinijit time. The current fundraising event is purely the initiative of DCESON and it was conducted by forming a taskforce consisting of its committed members. DCESON took this mission as a national and timely one and undertook extensive planning and mobilization tasks. On the other hand, the agents of the TPLF and their supporters made futile attempts and campaigns to undermine and hamper this event. This shows that the formation of an armed Ethiopian resistance force has frightened and alarmed the TPLF camp and regime.
Ato Andargachew Tsege, the secretary of the Ginbot 7 Movement for Justice and Freedom and Democracy and Commander Assefa Maru, chief of Ginbot 7 Popular Force, were the guests of the event. The guests received a standing ovation in the event hall which was decorated with the Ethiopian flag and symbols of the popular force.
The event had a series of programs which went on as planned. After the program of the day was announced by Ato Abi Amare, leader of the PR group, opening remarks were given by preventative of the taskforce, Ato Worku Tadesse. A keynote address was given by the chairperson of the DCESON Ato Dawit Mekonnen. Representatives of the Ethiopian asylum seekers` association, w/t Sara Girma, DCESON women’s branch, w/o Guenet Worku, Chairperson of DCESON-Women’s section, W/t Lemlem Andarge, DCESON-Bergen branch, Ato Shume Werku gave speeches to the audience. In addition, W/t Kalkidan Kassahun from Steinskjer, Ato Sally Abraham from Vestness, also held speeches that focused on the significance of the event and the need for increased struggle against the TPLF rule in Ethiopia.  Moreover, the representative of the Tigray People Democratic Movement (TPDM) in Norway, Ato Haile Asmamaw, addressed the event and played the audiovisual message to all Ethiopians sent from the field.
The younger members of the DCESON in fatigues were a unique addition to the event.
Ato Andargachew outlined the tasks and current activities of the force and presented footage showing the training and preparations of the force out in the field. He also mentioned the cooperation with the Tigray People`s Democratic Movement (TPDM), hardships the members of the force undergo and the sacrifices they pay.
Commander Assefa Maru spoke on his part about the objectives, tasks and missions of the force. In his speech, he explained the importance of an armed force and resistance to remove the TPLF from power and pave the way for a democratic and an all-inclusive political system in Ethiopia. He underscored the commitment of the force to achieve its goal and necessity of offering help and support to the force.
The audience learnt from the two guests that Ginbot 7 Popular Force is established by freedom-loving Ethiopians, including youngsters and intellectuals and it is working to remove TPLF by force and to create a peaceful transition period enabling establishment of non-partisan and constitutional defense, police, security, judiciary, etc. which are crucial for a healthy playground for different political parties aspiring power in the country. Among the current G7PF members are many intellectuals who joined this force abandoning their relatively comfortable living, families and professional jobs. This is one of the peculiarities of the G7PF compared to traditional armed struggles in Ethiopia where mainly farmers and other non-intellectuals comprise the main components of the foot soldiers. Presence of skillful leadership on the ground is told to highly assist G7PF members equip not only with armament but also with political, social, cultural knowledge about Ethiopia which is important to build a force that understands why and whom they are fighting for and paying sacrifices.
Food and refreshments were served during the event. Ethiopian music and live performances were staged to make the event entertaining and enjoyable. A short drama showing the atrocities of the TPLF regime in Ethiopia, written by w/t Mihret Ashine, was also presented.
The latter parts of the event were devoted to auctions meant for raising money as planned. The inspiration and enthusiasm of auction hosts, Ato Million Abebe and Ato Amsal Kasie, was the driving force for the high sum of money raised during the auction. The financial contributions of the participants and others, including attendants of the Ethiopian Current Affairs Discussion Forum (ECADF) were high and laudable.
The successful staging of the event was made possible through the cooperation and contributions of the participants as a whole. This event demonstrated what Ethiopians in the diaspora can achieve through cooperation and working together for a common goal.
The fundraising taskforce and DCESON extend their heartfelt thanks and appreciation to all the participants, contributors and huge thanks to all Ethiopians from all over Norway.
Ginbot 7 Popular Force fundraising taskforce in Norway
October 22, 2013

tirsdag 22. oktober 2013

ትእምት የህወሓት ንብረት እንጂ የትግራይ ህዝብ ሃብት እንዳልሆነ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባልና የማረት ሓላፊ ኣቶ ተክለወይኒ ኣሰፋ ተናገሩ

! ……. የገዢዎቻችን ነገር ……….!

ኣንድ
በ1993 ዓም የህወሓት ክፍፍል መለስ የነ ስየ/ተወልደ ቡድን ለማሸነፍ በህወሓት ሰነፎች (የራሳቸው ነፃ ሓሳብ ያልነበራቸው) የፓርቲው ሰዎች ኣሰባስቦ ‘እኔን መርጠዋል’ ብሎ በህወሓት ሊቀመንበርነቱና የጠቅላይ ሚኒስተር ስልጣኑ ይዞ እንደሚቆይ ኣሳወቀ። ኣቶ ኣባይ ወልዱም ይሄንን ‘የመለስ ራእይ’ (ሰነፎች ማሰባሰብ፣ ጎበዞች ማባረር) እየተገበረ ይገኛል።
ሰነፎቹ ስልጣን ተረካቢዎች ኣሁን የጠበቁት የህዝብ ድጋፍ ባለ ማግኘታቸው ግራ ተጋብተው የሚናገሩትን ነገር እስካለማወቅ ደርሰዋል። በተለይ ኣዜብ መስፍንና ኣባይ ወልዱ (እንዲሁም ስብሓት ነጋ) ለሚናገሩት ነገር ‘ይቅር’ እንበላቸው። ብቁ ፖለቲከኞች ኣለመሆናቸው እየነገሩን ነው። ጭንቀታቸው በኣደባብይ ሲናገሩ ያሳዝናሉ።
ሁለት
የህወሓት መሪዎች ከስልጣን መውረድ የማይፈልጉበት ምክንያት (1) እስካሁን የሰሩት ጥፋት እንዳይጋለጥ ይሰጋሉ። (2) የትእምትን ሃብት ማጣት ኣይፈልጉም። (3) ፓርቲው ስልጣን ከለቀቀ ልክ እንደ የድሮ የደርግ ባለስልጣናት በጠላትነት ተፈርጀው ከሀገር የሚባረሩ ይመስላቸዋል።
‘ትእምት ግን የማን ነው?’ ብለን ስንጠይቅ መልሱ ‘የህወሓት መሪዎች’ የሚል እንደሚሆን ግልፅ ነው። ባለፈው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባልና የማረት ሓላፊ ኣቶ ተክለወይኒ ኣሰፋ ትእምት የህወሓት ንብረት እንጂ የትግራይ ህዝብ ሃብት እንዳልሆነ መናገሩ የሚገልፅ post ኣድርጌ ነበር። (መረጃው ያገኘሁት ከፌስቡክ ጓደኛየ ነበር)። መቼና የት እንደተናገረው መጥቀስ እንዳለብኝ ከጓደኞቼ ኣስተያየት ደርሶኛል።
ከተሰጡኝ ኣስተያየቶች በመነሳት ለማጣራት ስሞክር ተክለወይኒ ኣሰፋ ይሄን የተናገረው ባለፈው ዓመት ሮብ ሚያዝያ 10, 2004 ዓም ሲሆን ቦታው በMIT የስብሰባ ኣዳራሽ እንደነበር ለመረዳት ችያለሁ። ‘ለምን ያን እንዲናገር (ኣምኖ እንዲቀበል) ተገደደ?’ የሚለውን ጥያቄ መመለስ ተገቢ ነው፣ ምክንያቱም ብዙ ግዜ (ወይ ሁልግዜ) የህወሓት መሪዎች ትእምት የግል ሃብታቸው መሆኑ እያወቁ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ግን ‘ትእምት የህዝብ ነው’ ይሉን ነበር።
MIT (Mekelle Institute of Technology) ሲቋቋም ዓላማው የክልሉ ጎበዝ ተማሪዎች ተመጠው እዛው ተምረው ገዢውን ፓርቲ በታማኝነት እንዲያገለግሉ ታስቦ ነበር። ቁስ ነገር በመስጠት ጎበዝ ልጆችን ባርያ ኣድርጎ ለመግዛት፣ ይህንን ካልተቻለ ደግሞ ስርዓቱ እንዳይቃወሙ ለማድረግ ነ ው። ህወሓቶች ጎበዝ ተማሪዎችን (ወይ ሙሁራን ባጠቃላይ) ይፈራሉ። ምክንያቱም እነሱ በደምብ የሚያውቁት በሓሳብ ማሸነፍ ሳይሆን ተኩሶ መግደል ነው። ኣሁን የቸገራቸው ይሄንን ነው፤ (ውድድሩ በጠመንጃ ሳይሆን በሓሳብ መሆኑ)።
የMIT ተማሪዎች ግን ህወሓቶች እንደጠበቁት (ስለበሉ ስለጠጡ) ‘ታማኝ ኣገልጋዮች’ መሆን ኣልቻሉም። ጥያቄዎች ማንሳት፣ መብት መጠየቅ፣ መቃወም … ምናምን ጀመሩ። ማስተካከል እንዳለባቸው ተነገራቸው። ኣልተሳካም። ህወሓቶች በጉዳዩ ተሰብስበው ተወያዩ። ‘እነዚህ ተማሪዎች በራሳችን ገንዘብ ኣስተምረን ለኛ ጠላቶች እየፈጠርን ነን።’ (MIT fund የሚደረገው ከትእምት ነበር)። እንደዉጤቱም ‘ጠላቶች’ ለመፍጠር ገንዘባቸው ማባከን እንደሌለባቸው ተስማምተው የMIT ቡጀት ተዘግቶ ተቋሙ ወደ መቐለ ዩኒቨርስቲ እንዲጠቃለል (በጀቱ ከፌደራል መንግስት እንዲሆን ተወሰነ)።
ይሄን ዉሳኔ የMIT ማህበረሰብ ተቃወመው (በወቅቱ ስለ ጉዳዩ ፅፌ ነበር)። ብዙ ችግር ተፈጠረ። የህወሓት መሪዎች የMIT ማህበረሰብ (ተማሪዎችና ኣስተማሪዎች) እየሰበሰቡ ማነጋገር ተያያዙት ። ከነዚህ መሪዎች ኣንዱ ተክለወይኒ ኣሰፋ ነበር። እሱ ተማሪዎቹን ሰብስቦ በበጀት እጥረት ምክንያት MIT fund ማድረግ እንደማይችሉና የመቐለ ዩኒቨርስቲ ኣካል መሆን እንዳለበት ይነግሯቸዋል። ሰመረ የተባለ ተማሪ እጁን በማውጣት ‘ትእምት የትግራይ ህዝብ ሃብት ነው ትሉናላቹ ግን በትክክል የህዝብ ከሆነ ለምን ለህዝብ በሚጠቅም መልኩ ኣታውሉትም?’ ብሎ ይጠይቃል። ተክለወይኒም በጣም ተናዶ “ማን ኣለህ ዉሸታም! ትእምት (EFFORT) የህወሓት ነው፤ ህዝብ ደሞ ማነው?” (“መን ኢሉካ ሓሳዊ! ትእምት ናይ ህወሓት እዩ። ታይ እዩ ህዝቢ ኸ?” ብሎ መለሰለት።
ተክለወይኒ እንዲህ መናገሩ ምን ኣዲስ ነገር ኣለው? ኣዲስ ነገር ኣይደለም። ምናልባት ኣዲስ ከሆነ ግን በራሳቸው ኣንደበት በህዝብ ፊት መናገራቸው ብቻ ነው እንጂ የህወሓት መሆኑማ ማንም ሰው ያውቃል። ኣሁን ኣሁን እኮ ግን ትእምት የህወሓት ኣባላት መሆኑ ቀርተዋል። ትእምት የሁሉም ኣባላት ኣይደለም። ትእምት የተወሰኑ የህወሓት መሪዎች የግል ሃብት ነው። የጥቂት ሰዎች ነው።
ሦስት
በመኾኒ በሺዎች የሚቆጠሩ መኖርያ ቤቶች እንደሚፈርሱ በመንግስት ኣካላት ከተነገረ በኋላ ኗሪዎቹ ኣማራጭ መጠልያ እንዲዘጋጅላቸው ቢጠይቁም መፍትሔ እንዳላገኙ ጠቅሼ ነበር። ከዚህ በመነሳት “ቤቶቹ የሚፈርሱት በምን ምክንያት ነው?” የሚል ነገር ተነስተዋል። የሚፈርስበት ምክንያት “ሕገ ወጥ ግንባታ” ተብሎ ነው።
በመኾኒ ወደ 7 ሺ የሚጠጉ ቤቶች ‘ሕገ ወጥ’ ከሆኑ ‘ሕጋዊ የሆነ ቤት የለም’ ልንል ነው። ግን ይህን ሁሉ ቤት ‘በሕገውጥ መንገድ’ ሲገነባ (ለብዙ ዓመትም ኑሮበታል) ኣስተዳዳሪዎቹ (የመንግስት ተወካዮቹ ) የት ነበሩ? እስኪገነባ ድረስ ዝም ብለው እያዩ ነበር ወይስ ከተገነቡ በኃላ፣ ኣገልግሎት መስጠት ከጀመሩ በኋላ ነው ‘ሕገወጥ’ የሆኑት? ‘ሕገወጥ’ ቤት ከተገነባ ከጅምሩ ነው መቆም የነበረበት። ራሳቸው ይፈቅዳሉ፣ ይሰጣሉ፣ በኋላ ያፈርሳሉ። ይህንን ተግባር በነዋሪዎቹ የሚፈጥረው የስነ ልቦና ችግር ቀላል ኣይደለም። እንደዚህ ዓይነት ችግር ከመልካም ኣስተዳደር እጦት የሚመነጭ ነው።
የህወሓት መሪዎች ያዳላሉ። ምሳሌ ልስጣቹ፡ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት በመቐለ ከተማ የመኖርያ ቤቶች ግንባታ ጉድ ነበር። ብዙ የከተማው ነዋሪዎች ‘ሰራዋት’ ተብሎ በሚጠራ ኣከባቢ (የከተማው ኣስተዳደር ፍቃድ ኣግኝተው፣ ማንም ሳይከለክላቸው) በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ተገነቡ። ኣገልግሎት መስጠት ጀመሩ።
በተመሳሳይ መልኩ (በተመሳሳይ ግዜና ሁኔታ) ግን ለየት ባለ ቦታና ለየት ባሉ ሰዎች ሌላ ዓይነት ቤቶች (ቪላዎች) ይገነቡ ነበር። እነዚህ ለየት ባለ ቦታ የተገነቡ ቪላዎች Hill Top Hotel ኣከባቢ በሚገኝ ‘ልዩ መንደር’ ነው። ‘ልዩ መንደር’ ያልኩበት ምክንያት እዛ ኣከባቢ ቤት መስራት የሚፈቀድለት ሰው የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣን መሆን ኣለበት። ሌላ ተራ ሰው እዛ ኣከባቢ ቤት መስራት ኣይፈቀድለትም። በወቅጡ የነበረ “ጥሕሎ” የተሰኘ መፅሔት “ኣፓርታይድ መንደር” ብሎ ሰይሞታል። እስካሁንም “ኣፓርታይድ መንደር” ተብሎ ይጠራል። ባለስልጣናቱ ለብቻቸው ተለይተው የሚኖሩበት ሠፈር ስለሆነ ነው።
ሁለቱም የ’ሰራዋት’ (የሰላማዊ ሰው)ና ‘ኣፓርታይድ መንደር’ (የባለስልጣናቱ) የቤት ግንባታዎች ማንሳት ለምን ኣስፈለገ? በሰራዋት የተገነቡ ቤቶች ሁሉም በግፍ (በዶዘሮች) እንዲፈርሱ ሲደረግ የባለስልጣናቱ (ኣፓርታይድ መንደር) ግን ማንም ሳይነካው እስከኣሁን ድረስ ኣለ። የተራ ህዝብ ፈረሰ (ሕገወጥ ተባለ) የራሳቸው (የባለስልጣናቱ) ግን ‘ሕጋዊ ሆነ’ (ምክንያቱም እነሱ ኮ ከሕግ በላይ ናቸው)።

torsdag 17. oktober 2013

የመንበረ ፓትርያርክ 32ኛው ጉባኤ የረቡዕ ዕለት ከሰዓት ውሎ ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ ዋና አጀንዳው ‹መቻቻልን› የተመለከተ ሲሆን አቅራቢዎቹም ከፌዴራል ጉዳዮች የተወከሉ አካላት መሆናቸውን በዕለቱ የመርሐ ግብር ዝርዝር ላይ ተገልጧል፡፡ ከሰኞ ጀምሮ ይቀርብ በነበረው የአህጉረ ስብከት ሪፖርቶች ላይ የመብት ጥሰትና ሥልጣንን ለግል ሃይማኖት ማስፋፊያ የመጠቀም አዝማሚያዎች መኖራቸውን፣ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠው እምነትን የመያዝ፣ የማስፋፋትና የአምልኮ ቦታ የማግኘት መብት እየተጣሰ መሆኑን የሚገልጡ ዘገባዎች ይሰሙ ነበር፡፡

በትናንትናው የከሰዓት ውሎ ስለ መቻቻል ገለጣ ከተሰጠ በኋላ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳትና የጉባኤው ተሰብሳቢዎች የየአካባቢያቸውን ችግሮች በዝርዝር ነበር ያነሷቸው፡፡ ‹‹መቻቻል እስከ ምን ድረስ ነው›› ብለው ነበር ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ የጠየቁት፡፡ ‹‹አሁን በምዕራብ ወለጋ ያለው ሁኔታ መንግሥት በአገሩ ያለ ይመስላል ወይ? ሰው እግሩን እሳት እየበላው ቻል ይባላል እንዴእንድንቻቻል አድርጉን፣ እንችላለን›› ነበር ያሉት፡፡
የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሄኖክ ‹በነጆ ወረዳ በሕጋዊ መንገድ ተሠርቶ የነበረው ቤተ ክርስቲያን በአካባቢው ባለ ሥልጣናት ተጽዕኖ እንዲፈርስ መደረጉን፣ ለምን ታፈርሳላችሁ ብለው ድርጊቱን የተቃወሙ ስድሳ ምእመናን መታሠራቸውን›› በኀዘን ነበር የገለጡት፡፡ አያይዘውም ‹‹በባኮ ወረዳ የተመደቡ አንድ ካህን እያረሱ እያሉ የአካባቢው ባለ ሥልጣናት መጡ፤ ካህኑን በሰደፍ እየደበደቡ ‹ከዚህ ሀገር ልቀቁ፣ ይህ የነፍጠኛ መኖሪያ አይደለም› እያሉ አሰቃዩዋቸው፡፡ ካህኑን ሲደበድቧቸው አንበርክከው፣ ለ15 ደቂቃ አተኩረው ፀሐይዋን እንዲያዩ እያስገደዱ ነበር፡፡ ድብደባውን ሰምተው የወጡት ባለቤታቸው በድንጋጤ ታመው ከጥቂት ቀናት በኋላ ሕይወታቸው አለፈ››
‹‹በሰንበትና በቅዱስ ሚካኤል ቀን ምእመናን ሊያስቀድሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ‹ለቅዳሴ ካህናቱ ይበቃሉ፤ እናንተ ውጡ›› እየተባሉ እንዳያስቀድሱ ይደረጋሉ፡፡ ከእኛ ቤተ ክርስቲያን 70 ሜትር ርቀት ላይ ሆን ተብሎ እርስ በርስ ለማጋጨት ለፕሮቴስታንቶች የጸሎት ቦታ ተሰጠ፡፡ ለምን ታጨቃጭቁናላችሁ፤ ይህ ቦታ ለእነርሱ አይሆንም ብሎ በመከራከሩ አንድ ዲያቆን ተደብድቦ ሞተ፡፡ የሕክምና ውጤቱም ሆን ተብሎ በወባ በሽታ ሞተ ተብሎ ተሠራ፡፡ ለሁለት ዓመት ያህል ተከራክረን አሁን ቦታው ለእኛ ተወሰነ፡፡
ጊምቢና መንዲ ላይ የምእመናን ልጆች ትምህርት ቤት ውስጥ በፖሊስ ማተባችሁን በጥሱ እየተባሉ ነው፡፡ ለምን ስንላቸው ከላይ የወረደ መመሪያ አለ ይሉናል፡፡››
ቀጥለው የሀገረ ስብከታቸውን ችግር ያቀረቡት የጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልያስ ነበሩ፡፡ ‹‹በጋሞ ጎፋ መቱ ወረዳ፣ ዋጁ ኡቆ ላይ የመስቀል ማክበሪያ ቦታችን ለሱቅ መሥሪያ ቦታ ተሰጠ፡፡ አቤት ብንል የሚሰማን በማጣታችን ዘንድሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መስቀል ሳናከብር ዋልን፡፡ ሀገሪቱ በችግር ላይ በነበረች ጊዜ እንኳን መስቀል ሳይከበር ቀርቶ አያውቅም ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያን የይዞታ ቦታ ለመንግሥት እየተሰጠ ነው፡፡ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን በቅዱስነታቸው በኩል ለክልሉ ደብዳቤ ጻፍን፡፡ ክልሉ ወሰነልን፡፡ ነገር ግን እስካሁን አልተረከብንም፡፡››
ቀጥለው ሃሳባቸውን የሰጡት የባሰ ካልመጣ በቀር ድምጻቸው ማይሰማው ብጹዕ አቡነ ያሬድ የሶማሌ ክልል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ‹‹በሶማሌ ክልል አምስት አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ናቸው ያሉን፡፡ ምእመናኑ ብዙ ናቸው፡፡ ሲወልዱ የሚያስጠምቁበት፣ ሲያርፉ የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን እንትከል ብንል የሚሰማን አጥተናል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የሚረዱ ምእመናን በግላቸው ጥቃት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ለዚህ መልሳችሁ ምንድን ነው›› ብለዋል፡፡
በገለጻው ላይ ኢትዮጵያ ክርስትናን የተቀበለችው በ4ኛው መክዘ ነው የሚለውን የተቃወሙት ብጹዕ አቡነ ማርቆስ ‹‹ታሪክ ክፉም ሆነ በጎ እንደ ታሪክነቱ መተረክ አለበት፤ አቅራቢው ወንድማችን በ4ኛው መክዘ ክርስትና ገባ ያልከው ተሳስተሃል፡፡ ለመሆኑ ይህንን ለማለት ‹ላይሰንስ አለህ?› አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁትክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ጌታ ባረገ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ላይ አለ፡፡ ይህንን ዛሬ ‹ግራጁዌት አድርገው›፤ ልዑካኑ ስትመጡ ስለምትናገሩት ነገር ዕወቁ፤››
የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንድርያስም ‹‹በቤተ መንግሥት የወርቅ ዕቃ ብቻ አይኖርም፣ የእንጨትም፣ የድንጋይም ዕቃ አለ፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ሁሉም ጥሩ አይሆንም፣ መጥፎም ይኖራል፡፡ ነገር ግን እስከ መጨረሻው የጸና ይድናል ብሏል፡፡ በእኔ ሀገረ ስብከት ስድስት አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፡፡ ሦስቱ በአንድ አካባቢ፣ ሦስቱ በሌላ ቦታ፡፡ ይህንን ለክልሉ መንግሥት ብናሳውቅ አልረዱንም፡፡ የተበደለ ሰው ይጮኻል፤ ሲጮህ ደግሞ ፖለቲካ ነው ይባላል፡፡ ድሮ ያስቸገረን የንዋያተ ቅድሳት ዘረፋ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ወደ ማቃጠል ተዛውሯል፡፡ አንዱ ባለ ሥልጣን እንዲያውም ችግሩን ሳቀርብለት ተቆጣኝ፤ ብዙ ብናገር ነፋስ ስለሚወስደው እዚህ ላይ ይብቃ››
ከብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳት ቀጥሎ የተናገሩት የወላይታ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ‹‹በበዴሳ ወረዳ ያለ አንድ የሌላ እመነት ተከታይ የሆነ ዳኛ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ቄራ አንካፈልም፤ በመኪና አብረን አንሄድም› ብሎ ዐወጀ፡፡ በጋራ በመቻቻል የኖርንበትን ዕድር ሁሉ ለዩ ብሏል፡፡ ታድያ እንዴት መቻቻል ሊመጣ ይችላል፡፡››
ከጉባኤው የቀረበውን ቅሬታና ሃሳብ ያዳመጡት የፌዴራል ጉዳዮች የሥራ ኃላፊዎች የቀረቡት ቅሬታዎች በሰነድ ተደግፈው ቢደርሷቸው እነርሱም በመፍትሔው ላይ መሥራት እንደሚችሉ፤ ኢትዮጵያ የሃይማኖቶች ጉባኤም ጉዳዩ በየደረጃው ቢቀርብለት መፍታት እንደሚችል፡፡ ቅሬታዎችን እንደዚህ ባለ መድረክ ከሚሆን በየጊዜው እየተገናኙ መፍታት ቢቻል›. የሚሉ ሃሳቦችን ሠንዝረዋል፡፡
የዘንድሮው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ በአደረጃጀቱ ውበት፣ በተሳታፊዎቹ ብዛት፣ በአህጉረ ስብከቶች ቁጥር(50 ደርሰዋል)፣ በስብሰባው ቁም ነገረኛነት ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ እነ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በብርቱ እንደ ደከሙበት ያሳያል፡፡ በየዘገባዎቹ የተሰሙትን የመብት ጥሰቶች፣ ሥልጣንን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ጫናዎች፣ የአምልኮ ቦታ እጥረቶች፣ በካህናቱ ላይ የሚፈጸሙትን ግፎችና፣ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ የመንጠቅ ርምጃዎች ግን ሊገቱ ይገባቸዋል፡፡ ከአንዳንድ ክልሎች በቀር በብዙዎቹ የዞንና የክልል ባለ ሥልጣናት ችግሩን ተረድተው ለመፍታት እንደሚጥሩ ተገልጧል፡፡ በወረዳ ደረጃ የሚገኙት ግን ሥልጣንን ተገን በማድረግ የግል እምነታቸውን እያስፋፉ መሆኑን ያሳያል፡፡ በደቡብ ጎንደርና በምሥራቅ ጎጃም የተፈጸሙት የአብያተ ክርስቲያናትን የማቃጠል ርምጃዎች በጊዜው ተጣርተው መፍትሔ ካልተሰጣቸው ፍጻሜያቸው አያምርም፡፡
በየአካባቢው በሚገኙ ባለ ሥልጣናት የሚፈጸሙ ትንኮሳዎችም መቆም አለባቸው፡፡ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳቱ ‹አታስቆጡን› እያሉ ደጋግመው የተናገሩት ነገር የዋዛ አይደለም፡፡ ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላት የሚፈጽሙት ገደብ አልባ ትንኮሳና ጫና ወዴት እያመራ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱም አደረጃጀቷንና አሠራርዋን ይበልጥ የምትፈትሽበት፣ አሁን ለገጠማት ተግዳሮት ብቁ የሚሆን አሠራና አወቃቀር የምትይዝበት፣ ችግሮችን በስብሰባ ብቻ ሳይሆን በአካባቢያዊ ውይይት፣ በሕግ መሥመርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት የምትፈታበት መንገድ ሊኖር ይገባል፡፡  
ያለበለዚያ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል የተረተው ተረት መድረሱ የማይቀር ነው፡፡
በጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም› እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው›› አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡

onsdag 16. oktober 2013

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግስት ላይ ተቃውሞ አሰማች

ጥቅምት (ስድስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትሪያርክ ስብሰባ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ባለው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በቤተክርስቲያኑዋ ታሪክ  ተሰምቶ የማያውቅ ተቃውሞ ተከስቷል። አንድ በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባት እንደገለጹት በስብሰባው ላይ ”  ይህ መንግስት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ እንደተነሳ በስፋት ተነግሯል።

የፌደራል ጉዳዮች የሀይማኖት ክፍል ሃላፊዎች ዛሬ ስለ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ገለጻ ለመስጠት በተገኙበት ወቅት ነው ተቃውሞው የተሰማው።
እድሉን ያገኙት 6 ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም የሰሜን ወሎ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቄርሊዮስ ፣ የምእራብ ወለጋ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ ሄኖክ፣ የጋሞ ጎፋ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤሊያስ ፣ የወላይታ ዳውሮ ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የምስራቅ ጎጃም ሊቀ ጳጳስ ብጹ አቡነ ማርቆስ ፣ የደቡብ ጎንደር ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንድሪያስ የመንግስትን ፖሊሲ እአነሱ ትችት አሰምተዋል።
በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ፣ ግድያና ጫና መጨመሩን የተነጋሩት አባቶች ፣ ፓትሪያርኩም እውነት ነው ይህ ሁሉ ጫና አለብን በማለት በሊቀ ጳጳሳት የቀረቡውን ሀሳብ ደግፈዋል።
ከመላው አለም የተሰባሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀይማኖቱ መሪዎች በተገኙበት ስብሰባ ላይ የመንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያን የሀይማኖት ታሪክ በማሳነስ ባቀረቡበት ወቅት  የሀይማኖት አባቶች ስሜት በተቃቀለበት ሁኔታ መልስ ሰጥተዋል።
የህዝቡን መሬት ነጥቃችሁ ፣ ህዝቡንም መሬቱንም የመንግስት ያደረጋችሁት እናንተ ናችሁ፣ ኢትዮጵያዊው ሀብትና ንብረት እንዳይኖረው አደረጋችሁት እናንተ ናችሁ፣ ከዚህ ቀደም ከነበሩት መንግስታት በባሰ ህዝቡን ያስጨነቀ ይህ መንግስት ነው በማለት አባቶቹ ተናግረዋል።
“በአጼዎችም ዘመን ቢሆን ይህችን አገር  ስትረከቡ እስከ ታሪኩዋ ነው፣ ታሪኩዋን አላጠፋችሁም ወይ?” በማለት ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ ሲናገሩ ከተሰብሳቢው ከፍተኛ ድጋፍ ተችሮአቸዋል።
የሀይማኖት አባቶች የቤተክስርቲያኑዋን ታሪክ አዛብታችሁዋል፣ ቤተክርስቲያኑዋንም ታሪኩዋን አጥፍታችሁዋል በማለት ወጥረው መያዛቸው ታውቋል።

Africa’s journalists honor jailed editor Woubshet Taye

By Sue Valentine/CPJ Africa Program Coordinator
122
Woubshet Taye’s wife Berhane Tesfaye and their son accepted an award on behalf of the imprisoned journalist. (CPJ/Sue Valentine)
Journalists and media owners across Africa gave Ethiopian journalist Woubshet Taye a standing ovation in Cape Town on Saturday night at the CNN MultiChoice African Journalist Awards 2013, but he wasn’t there to see it. Instead his wife and son accepted the Free Press Award on his behalf.
Part of the citation for the award reads: “Ethiopia is a jewel in the African crown for its beauty, its people, its history and, most recently, for its astonishing growth rates. It is the judges’ view that journalists like Woubshet Taye and his colleagues Reeyot Alemu and Eskinder Nega should be out of prison and working to build the prosperity and the freedom of a new Ethiopia. The judges make this award in recognition of Mr. Taye’s work and in solidarity with his condition.”
Presenting the award to Berhane Tesfaye and the couple’s not-quite-five-year-old son, who were dressed in matching white and blue outfits, chair of the judging panel and editor-in-chief of the South African weekly City Press Ferial Haffajee said it was disappointing that “once again there were too many cases” for the judges to consider in this category, which recognizes “excellence and provides support to African journalists who report at continuing risk to their lives and safety.”
Woubshet, deputy editor of the Awramba Times, has been in jail for more than two years. He was detained in June 2011and held incommunicado before being convicted on terrorism charges and sentenced to 14 years imprisonment in January 2012. After Woubshet’s arrest, the paper stopped publishing in Ethiopia and the editor fled into exile. Accepting the award on his behalf, Berhane Tesfaye said her husband was grateful for the solidarity and received the award in the name of all journalists who are oppressed.
In April this year, Ethiopian authorities moved Woubshet to the remote Ziway prison about 83 miles (160 kilometers) from the capital Addis Ababa. His wife said that although it is a long way to travel, she is usually able to visit her husband every two weeks. However, she said that Woubshet’s parents–his father is 102 and his mother 90–are too old to make the journey. In September, Woubshet’s application for a presidential pardon was rejected, according to news sources.
The CNN MultiChoice African Journalist Awards began in 1995. A panel of 10 independent judges selected finalists and winners in 14 categories before naming an overall 2013 winner.
[Reporting from Cape Town]

የአስተዳደሩ ምርመራና ክስ ኤክስፐርት በቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ

-በቦሌ ጉምሩክ ኃላፊና በአንድ ባለሀብት ላይ የተዘጋጀው ክስ ሳይነበብ ቀረ
በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት በሥልጣን ያላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው፣ በማረሚያ ቤት በሚገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት
አስተዳደርና ግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን በነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ መዝገብ፣ በሌሉበት ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት፣ የአስተዳደሩ ፍትሕ ቢሮ የምርመራና ክስ ኤክስፐርት አቶ ተስፋዬ ዘመድኩን በቁጥጥር ሥር ውለው ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተባቸው አቶ ቃሲም ፊጤ፣ አቶ ተስፋዬ ዘመድኩን፣ የሊዝ አሰባሰብ ክትትል ኦፊሰር አቶ ገብረየሱስ ኪዳኔና የመሬት አቅርቦት አፈጻጸም ንዑስ የሥራ ሒደት አቶ በቀለ ገብሬ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 
ሦስቱ ተከሳሾች ሐምሌ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. የተጻፈ ክስ ቀርቦባቸውና ተነቦላቸው የዋስትና መብታቸው በመከልከሉ፣ ማረሚያ ቤት ቆይተው ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ 
ከሦስቱ ተከሳሾች በተጨማሪ በሌሉበት ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት አቶ ተስፋዬ አብረው በመቅረባቸው ቀደም ብሎ የተመሠረተው ክስ ተነቦላቸዋል፡፡ የዋስትና መብታቸውም ታልፎ በማረሚያ ቤት ሆነው ክሳቸውን እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ በጽሕፈት ቤት በኩል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ከአቶ ተስፋዬ በስተቀር ሦስቱ ተከሳሾች ለጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. ተቀጥረው የነበሩት የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የቅድመ ክስ መግለጫ እንዲያቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ አቶ ተስፋዬ ተይዘው በመቅረባቸው ክሱ እንደ አዲስ ተነቦላቸው በሁሉም ላይ የቅድመ ክስ መግለጫ ለማቅረብና ተከሳሾች በጠየቁት የዋስትና መብት ላይ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
ሌላው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞችና ነጋዴዎች ጋር በቁጥጥር ሥር ውለው በነበሩት በባለሥልጣኑ ቀድሞ የቦሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ አዳዩና በተለያዩ ንግድ ሥራዎች ላይ የተሰማሩት አቶ ማሞ ኪሮስ ላይ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ አዘጋጅቶ የመጣ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ በእድሳት ላይ በመሆኑ ዳኞች ቀድሞ ይሠሩበት ከነበረው ችሎት ወደ ሌላ ችሎት በመቀያየራቸውና ሳይሟሉ በመቅረታቸው ሳይነበብ ቀርቷል፡፡ 
አቶ ማሞ ኪሮስ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተሳትፈዋል በሚል መጠርጠራቸውንና አቶ ዮሴፍ አዳዩ በሥልጣን ያላግባብ መገልገል፣ ፈቃድ የሌለው የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘትና በሌሎችም ወንጀሎች መጠርጠራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 
ethiopian reporter

አለማቀፍ ጠበቆች የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ለፍርድ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀመሩ

ጥቅምት (አምስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በወጣት አብዱላሂ ሁሴን አማካኝነት በኢትዮጵያ የኦጋዴን ክፍል የተፈጸመውን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት ፊልም የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በስዊድን ቁጥር አንድ ቴሌቪዥን በትናንትናው እለት መቅረቡን ተከትሎ አለማቀፉ ጠበቆች ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀመረዋል።
ወጣት አብዱላሂ ለኢሳት እንደገለጸው ፊልሙ ከተላለፈ በሁዋላ ሚዲያዎች ሸፊ ሽፋን የሰጡት ሲሆን፣ ስቴላም የተባሉ የ አይ ሲ ጄ ጠበቃ ጉዳዩን ፍርድ ቤት እንደሚያቀርብ በሬዲዮ ይፋ አድርገዋል።
የስዊድን የጦር ወንጀል ኮሚሽን ፍርድ ቤትም ማስረጃዎችን በመመርመር ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ከወጣት አብዲ ጋራ ቀጠሮ ይዘዋል። ጠበቆቹ ጄኔቫ ካለው አይሲጄ ጋር  እና ከሌሎችም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንደሚሞክሩ ተናግሯል።
ትናንት በተላለፈው ፊልም ውስጥ ከዚህ በፊት በኢሳት ያልቀረቡ መረጃዎች መቅረባቸውን ወጣት አብዲ ገልጿል።
ልዩ ፖሊስ እየተባለ በሚጠራው ሀይል የተፈጸመ የዘር ማጥፋት ወንጀልን የሚያሳይ መረጃ መካተቱትን፣ የክልሉን ፕሬዚዳንት የተቸች አንዲት  ሴት በኦበነግ አባልነት ስትፈረጅ የሚያሳይ መረጃ ተካቶበታል ። የክልሉ ፖሊስ ሀላፊው በእስር ላይ የሚገኙትን ሴቶች በመድፈር ብዙ ህጻናት በእስር ቤት ውስጥ መወለዳቸውን በፖሊሶች በራሳቸው ሲነገር የሚያሳይ ፊልም መካተቱትን ወጣት አብዱላሂ ገልጿል።
ፊልሙ ” የዲክታተሮች እስረኞች” የሚል ርእስ ተሰጥቶታል።
ጉዳዩን በማስመልከት የአለማቀፍ የህግ ባለሙያዎች ኮሚሽን በእንግሊዝኛ ኢንተርናሽናል ኮሚሽን ኦፍ ጁሪስትስ  ኮሚሽነር የሆኑት ስቴላ ጋርደ ለኢሳት እንደገለጹት የወንጀሉን ፈጻሚዎች ወደ ፍርድ ለማቅርብ የሚችሉትን ሁሉ እንደሚጥሩ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የአለማቀፍ ወንጀል ( ICC) ፈራሚ አገር ባለመሆኑዋ ማስረጃውን በቀጥታ ለፍርድ ቤቱ መላክ እንደማይቻል የገለጹት ኪሚሽነር ጋርደ፣ ይሁን እንጅ ሰቆቃን ለመከላከል የተቋቋመው  ኮሚቴ ( Committe Against Torture) ፈራሚ አገር በመሆኑ ጉዳዩን በዚሁ በኩል ለመከታተል እና የስዊድን  ፖሊስ ምርመራ ጀምሮ እርምጃ ለመውሰድ  እንዲችሉ ጥረት እንደሚያደርጉ ለኢሳት ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብአዊ መብት ኮሚቴ እነዚህን ማስረጃዎች እንዲያገኙ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
የኖርዌይ የቴሌቪዥን ጣቢያም ፊልሙን በቅርቡ ያሰራጫል ተብሎ ይጠበቃል። ፊልሙ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በተለያዩ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ይቀርባል።
በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የሰጠው አስተያየት የለም።

mandag 14. oktober 2013

http://ethsat.com/video/esat-special-program-oct-13-2013/

ስብሃት ነጋን አጅበው አክቲቪስት መስፍን ላይ ድብደባ የፈጸሙት ግለሰቦች ማንነት ታወቀ

sibsha
(ዘ-ሐበሻ) በትናንትናው ዕለት ዘ-ሐበሻ በሰበር ዜና ባቀረበቸው ቪድዮ ላይ አክቲቪስት መስፍንን በቡጢ የተማቱትና የቆሙ መኪናዎችን ገጭተው ያመለጡት ግለሰቦች ማንነትን ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም አረአያ ማወቁን ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አስታወቀ፡፡
የሕወሓት መንደርን ከቃረምኩት በሚል በኢትኦጵ ጋዜጣ ላይ የሕወሓት ምስጢሮችን በሚያጋልጠው ጽሁፎቹ ታዋቂነትን ያተረፈው ጋዜጠኛ አረአያ ተስፋማርያም (ኢየሩሳሌም አረአያ) በትናንትናው እለት በአክቲቪስቱ ላይ ድብደባ የፈጸሙትን በሕግ የሚጠየቁት ግለሰቦች ሶስቱም የሕወሓት አባላት መሆናቸውን ጠቅሶ ማንነታቸውን ዘርዝሯል።
1ኛው. የሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን ወንድም ታምራት ገ/መድህን፣
2ኛው. የወያኔ ኪነት አባልና ጊታሪስት ወዲ ሰቦቃ (በአሜሪካ ፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ)፣
3ኛው ሃይሌ በአሜሪካ – የኢትዮጲያ ኤምባሲ የብርሃነ ገ/ክርስቶስ ሹፌር የነበረና በአሁኑ ወቅት በቪዛ ክፍል የሚሰራ ናቸው።
አክቲቪስት መስፍን ለደረሰበት ድብደባ ሕክምና የተከታተለ ሲሆን ጉዳዩን በሕግ እንደሚጠይቅ አስታውቋል። በሌላ በኩል የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን አንድ የቨርጂኒያ ጠበቃ አነጋግሮ ባቀረበው ዘገባው ስብሃት ነጋን ጨምሮ እነዚህ ግለሰቦች ሰውን በመደብደብና የሰው መኪና ገጭቶ በማምለጥ ወንጀሎች ከተከሰሱና ፍርድቤትም ጥፋተኛ ካላቸው በ እያንዳዱ ክስ እስከ አንድ አመት የሚያስቀጣ ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል። ስብሃት ነጋም የወንጀል ተባባሪ፣ እንዲሁም የሰው መኪና ገጭቶ ባመለጠ መኪና ውስጥ በመሄዳቸውና ወንጀልን በመተባበር ክስ በአሜሪካ ህግ በወንጀል ተባባሪነት ሊከሰሱ የሚችሉበት ህግ አለ።
የሃገራችንን ህልውና የሕዝባችንን
 ነፃነት እናስመልስ!!!
ከኤደን መስፍን(ኖርዌይ) 29. 08. 2013
ለአንድ ህዝብ ሃገር ማለት የመኖር ዋስትናው ተጠብቆ ሳይሸማቀቅ፣ ሳይበደል፣ ፍትህ ሳዩጓደል፣ የዜግነት
መብቱ ተጠብቆ የህግ ከለላ አግኝቶ በነፃነት የሚኖርብት ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን ሃገር
መሆን ከተሳናት እንሆ ሃያ ሁለት አመት ተቆጠረ፡፡ የደርግ ስርዓትን ተክቶ በትጥቅ ትግል መንበሩን
የተቆናጠጠው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ የፖለቲካ ስልጣኑንም ሆነ የኤኮኖሚ አውታሩን
በአንድ ብሄር ብቻ አደራጅቶ የተቀረውን ኢትዮጵያዊ እንደ ዜጋ የመኖር መብቱን ገፎ በግዞት ያኖረዋል፡፡
ይህ ፈላጭ ቆራጭ ግፈኛ ብድን ሰብአዊ መብት አለማክብሩ ብቻ ሳይሆን ሃገርን የማፍረስ ጭምር አላማና
ተልኮ ስላለው የሚፈልገውን ለማድረግ ማንም ምንም ተቃውሞና ትችት እንዲያቀርብለት አይፈልግም፡፡
ስለሆነም በሃገሪቱ ባለው ህገ -መንግስት፣ ያውም እራሱ ባፀደቀው መሰረት የሚንቅሳቅሱ ኢትዮጵያዊያን
የሲቪክ ማህበራት፣ የነፃው መገናኛ ብዙሃን አባላት፣ የዴሞክራሲ ተሟጋቾችን፣ የሰብአዊ መብት
ታጋዮችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እነዚህንና ሌላውን ንጹሃን ዜጎችን ሳይቀር እያዋከበና እያሳደደ ገሚሱን
ስም እያወጣ ወህኒ ሲያጉር ከፊሉን ደግሞ በሃገራቸው የመኖር መብት ነስቶ እንዲስደዱ ያደርጋል፡፡
 1997 ዓ.ም በጭላንጭል የታየውን የመደራጀት መብት ተጠቅመው ህዝብን ያደራጁና በኋላም
በምርጫው የህዝብ ይሁንታ አግኝተው በካርድ የተመረጡ የፖለቲካ ድርጅቶችን ይህው ፈላጭ ቆራጭ
ቡድን በማን አለብኝነት አለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚያውቀውን ውጤት ለውጦ እስካሁን ድረስ
ባልመረጠው ህዝብ ጫንቃ ላይ ተፈናጧል፡፡ በወቅቱም ሽንፈቱን ላለመበቀል በመቶዎች የሚቆጠሩትን
በጠራራ ፀሃይ ሲገድል፣ አስር ሺዎችን ወደ ማጎሪያ ማጋዛቸው፣ መደብደባቸው፣የተቀሩት ማሳደዳቸው
አለም የሚያቀው እውነታ ነው፡፡
ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ ያየውን መከራና ፍዳ ቅን የሆኑ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች
ተቋማት ምስክር ናቸው፡፡ይህ አምባገነን ቡድን ህዝቡን አፍኖ፣ አሸማቆና አንገት አስደፍቶ የሄደበት የአፈና
መዋቅር 2005ዓ.ም ላደረገው የይስሙላ ምርጫ ጉልበት ሆኖት ዘርፎም፣ አታሎም፣አጭበርብሮም 99.6%
አሸነፍኩ ሲል መደመጡ ብዙዎችን ያስገረም ጉዳይ ነበር፡፡
የህዝብን የነፃነት ጥያቄን ለማፈን በተለይም በሰሜን አፍሪካ ከአረቡ አብዮት ጋር በተያያዘ ህዝብ
ይነሳብኛል ብሎ የሰጋው የወያኔ ቡድን የተለያዩ አፋኝ ህጎች ሲያወጣ ከርሟል፡፡ ከዚህም አንዱ የፀረ-
አሸባሪ ህግ ነው፡፡በዚህ ህግ ብዙሃን የነፃነት ታጋዮች ከሞት እስከ እድሜ ይፍታህ ተፈዶባቸዋል ፡
ይተቀሩትም የህሊና እስረኞች አሁን ባለንበት ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በየቀኑ የሚገደሉባት፣
የሚደበደቡባት ቶርች የሚደረጉባት ስብእናቸው እየተዋረደ በዘራቸው የሚሰደቡበት በተለያዩ ቦታዎች
ታጉረውና ያለፍርድ ተረስተው የሚገኙባት በአጠቃላይ ለፍትህ እና ለነፃነት ለሚታገሉ ንፁሃን ዜጎች
የምድር ሲኦል የሆነች ሃገር አርገዋታል፡፡ ገዥው ብድን የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ከሚጠቀምባቸው
መንገዶች አንዱ የህዝብን የማወቅ መብት መገደብና እሱ ከሚለው ውጪ ምንም እንዳይሰማ፣ እንዳያይ
አማራጭ የመገናኛ ብዙሃንን ማፈን ትልቅ ስራ አድርጎታል፡፡ ስለዚህም ለአገዛዙ እንዲመቸው ለ90
ሚሊዮን ህዝብ አንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ፣ አንድ ሬድዮና፣ አንድ በሁለት ቋንቋ የሚታተም ጋዜጣ ብቻ
በዚህ ዘመን አለም በመረጃ መረብ በተጥለቀለቀችበት ጊዜ ከራሱ ውጪ ለህዝብና ለሃገር ደንታ የሌለው
አምባገነን መንግስት ሌሎች አማራጮችን ዘግቷል፡፡
ከዚህ ሁሉ የወያኔ አፈናና ግፍ በኋላ ቢዘገይም(ቢረፍድም) በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከተደራጁ
ለቁጥር ከሚታክቱ ድርጅቶች ውስጥ የሃገሪቱ ህገ-መንግስት በሚፈቅደው መብታቸውን ተጠቅመው
ህዝብን በንቃት በማደራጀት ትግላቸውን እያፋፋሙ ያሉት ሰማያዊ ፓርቲና አንድነት የወያኔ የእግር እሳት
እየሆኑ በት እንዳለ ሰሞኑን በተለያዩ የሃገራችን ክልሎች እየሆነ ያለውን እልህ አስጨራሽ ትግል እያየን
ነው፡፡
ይህ ሲጀመር በሰማያዊ ቀጥሎም በአንድነት ፓርቲ የተጀመረው ፍርሃትን የሰበረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ
ዘርኛውን የወያኔ ስርዓት ምን ያህል እርቃኑን እንዳስቀረውና ኢትዮጲያን እየመራ ያለው ስርዓት ለህግ
ተገዢ እንዳልሆነ ፍንትው አርጎ ያሳየን አጋጣሚ ነው፡፡ የመንግስት ስልጣን ብቻ ሳይሆን በዘረፋ
ያካበቱትን ሃብትና ንብረት ለማስጠበቅ ፍጹም ስርዓት በጎደለው መልኩ የእውር ድንብራቸውን
የሚወራጩት የወያኔ ካድሬዎች ላለቆቻቸው ለመታመን ንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሱ ያሉት ወከባና
እንግልት የስርዓቱን ሃላፊነት የጎደለው ተራ የውንብድና ተግባር ያሳያል፡፡
ስለሆነም ሁል ጊዜ ስለበደላችን፣ በሃገራችን ህልውና ላይ እያንዣበበ ስላለው አደጋ ስንተርክና ስንቆዝም
አንድም ጠብ የሚል ነገር ሳይገኝ ሁለት አስር አመታት ተቆጠረ፡፡ ጊዜው የተግባር ነው አሁን ያለውን
የህዝባችንን ለነፃነቱ፣ ለመብቱ ለትግል መነቃቃት፣ የወያኔና መዝረክረክና በእቅድ ሳየሆን በግምት
መዳከርን ከግምት በማስገባት ልዩነታችንን አቻችለን በአንድነት በኢትዮጲያዊ ጥላ ስር ተከልለን ለለውጥ
እንነሳ፡፡ ከፍርሃት ድባብ ወጥተን በውስጥም በውጪም ካሉት ጠንካራ ድርጅቶች ጎን በምቆም የሃገራችንን
ህልውና የህዝባችንን ነፃንት እናስመልስ፡፡
ኢትዮጲያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
adugenet2000@gmail.com

tirsdag 8. oktober 2013

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በግዴታ ስለ አክራሪነት እና ሽብረተኝነት ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ ነው

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በ2006 ዓም ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉ የትምህርት ተቋማት ስለ አክራሪነት፣ ሽብርተኝነት እና ጸረ ሰላም ሀይሎች ትምህርት ለመስጠት የጀመረውን እቅድ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጀምሯል።
ከሁለት ሳምንት በፊት በክልል ለሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞችና መምህራን ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት፣ በርካታ ተሳታፊዎች እድሜያቸው ከ15 አመታት በታች የሆኑ ተማሪዎች ስልጠናውን እንዳይወስዱ ጠይቀው ነበር።
ባለፈው  አርብ እና ቅዳሜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ፋኩልቲ ተማሪዎች በአዲሱ የትምህርት ዘመን ለመመዝገብ ወደ ግቢ በገቡበት ሰአት፣ ምዝገባ ቆሞ ተማሪዎች ስድስት ኪሎ ወደሚገኘው የስብሰባ ማእከል እንዲያቀኑ ታዘዋል።
ተማሪዎች ” ለምን?’ የሚል ጥያቄ ባነሱበት ወቅት፣ የዩኒቨርስቲ ሀላፊዎች ከመንግስት የመታ ትእዛዝ በመሆኑ ምንም ማድረግ አንችልም የሚል ምላሽ ሰጥተዋቸዋል።
ተማሪዎች ከግቢ እንዳይወጡ በሩ የተዘጋባቸው ሲሆን፣ በቀረቡላቸው 2 አውቶቡሶች ተጭነው ስልጠናውን እንዲወስዱ ተደርጓል።
መንግስት ለስልጣኑ አደጋ ይፈጥራሉ ብሎ የሚገምታቸውን እንደ ግንቦት7፣ ኦነግና ኦብነግ የመሳሰሉትን  ድርጅቶች በጸረ ሰላምነት እና በአሸባሪነት ይፈርጃቸዋል።

mandag 7. oktober 2013

ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ አዲስ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት በመሆን ተመረጡ

Mulatu teshome
ፓርላማው በዛሬው ውሎው አዲሱን የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት አሳወቀ። ፕሬዝደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ክዚህ በፊት በነበሩት አመታት አንዴ ሲሾሙት ሲያወርዱት የነበረ ሲሆን ባሁኑ ሰአት ለቀጣዩ 6 አመታት ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት እንዲያገለግሉ ተሾመዋል::

søndag 6. oktober 2013

ሙስና ያጋለጠ የህወሓት አባል ተባረረ

በትግራይ እንደርታ ወረዳ ነው። የህወሓት አባላት የሆኑ የወረዳው አስተዳዳሪዎች (የዞኑ ሓላፊ ባለበት) እርስበርሳቸው እየተገማገሙ ሳለ አንድ አባል የወረዳው አስተዳዳሪ የ10 ሺ ብር ሙስና ከህዝብ መቀበሉ ያጋልጣል።
የህወሓት ባለስልጣናትም እርስበርስ ተነጋግረውና ተባብረው የ10 ሺ ብር ሙስና ያጋለጠ አባል እንዲባረር ወሰኑ። ተባረረ። አዎ! አብዛኛው አባል በሙስና ከተጨማለቀ የቅጣት ሰለባ የሚሆን ሙስና ያልሰራ ሰው ነው። 
ህወሓቶች ሙስና ያጋለጠ አባል ከአባልነት በማባረር ድርጅቱ የሙስና ካምፕ ለማድረግ ያሰቡ ይመስላል። መቼም ሙስና የሚያጋልጡ ሰዎች በማራቅ ሙስናን ማንገስ እንጂ መታገል የሚቻል አይመስለኝም።
ለነገሩ ህወሓቶች ሙስናን ላለመጋለጥ ተስማምተው የለ። ሙሰኛ መቅጣት ከተጀመረ ማን ማንን ሊቀጣ? አስቸጋሪ ነው። ሙሰኛ ለሙሰኛ እንዴት መቅጣት ይቻለዋል? እንደውም ሙሰኞች ተሰባስበው ሙሰኛ ላልሆነ አባል መቅጣት ይቀላቸዋል። እንዲህም እያደረጉ ነው።
ሙሰኛ ስርዓት ሙስናን መቃወም አይችልም። ምክንያቱም ሙስና ለማጥፋት ሙሰኞች ማጥፋት ግድ ይላል። ለገዢዎች ራስ ማጥፋት ከባድ ነው።

የትህዴን ደጋፊዎች ግንቦት-7 እያካሄደው ባለ ስብሰባ መገኘታቸውን የትህዴን የህዝብ ግንኝነት ገለጸ

11
ትህዴን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኘው ግንበት-7 ጋር ተባብሮ ለመስራት መግባባት ላይ ከመድረሱም በላይ በተግባር በተለያየ መልኩ ሲተጋገዙ የቆዩ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ የትህዴን አ ባላት የጉንበት-7 አ መራር ከአ ባላቱ ጋር በተለያዩ ሃገራት እያካሄደው ባለ ስብሰባ በመገኘት አንድነታችንን አ ጠናክረን እጅ ለእጅ
ተያይዘን እንሰራለን ሲሉ ለግንበት-7 ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣ በስብሰባው የተገኙ የትህዴን ተወካዮች አ ያይዘው እኛ በዚሁ ስብሰባ
ስንገኝ ለይምሰል ሳይሆን የህዝብን ድምጽ በAፈሙዝ ረግጦ ስልጣን የተቆናጠጠውን ከፋፋዩን የእህAዴግ ስርዓትን በሚገባው ቋንቋ በትጥቅ ትግል ከስሩ መንግሎ ለመጣል ገና ከመነሻው ትህዴን አ ምኖበት የተነሳለት በመሆኑ የድርጅቱን ዓላማ እግቡ ለማድረስ የሁለቱም ድርጅቶች Aባላትና ደጋፊዎች የIህአ ዴግ ስርዓት መለያ ከሆነው በዘር የመከፋፈል Aባዜ በመውጣት በሙሉ ልብ ድርጊቱን በማውገዝ ከሃገር ውስጥ ይሁን ከሃገር ውጭ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከመቸውም ጊዜ በላይ ግንኝነታችንን አጠናክረን ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል በማለት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፣ የግንበት-7 አመራርናአ ባላት በቡኩላቸው የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ካሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች በመሳሪያ ፤ በሰው ሃይልና በዓላማ ሲታይ ትህዴን ንካራ መሆኑን በመግለጽ እንዲህ ካለው Aስተማማኝ ድርጅት ጋር ተባብሮ ለመስራት ከመግባባት አልፈን አ ብረን እየሰራን ነው፣ ይህ መልካም ጅምር አጠናክረን እንቀጥልበትአለን ሲሉ ገልፇል::

onsdag 2. oktober 2013

አንድነት በመንግስት ዛቻ አንደናገጥም አለ

Oktober 2 / 2013

 አንድነት  ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በቀበና አካባቢ በተወሰነው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በሽብርተኝነት ጥፋተኛ ተብለው የታሰሩ ሰዎችን ይፈቱ ማለቱ፣ እንዲሁም ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያለን የሙስሊም ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ መጠየቁና ባልተፈቀደ ቦታ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጓል በሚለውን የመንግስት ምላሽ ማዘኑንና በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማል ዛቻ እንደማይደናገጥም አስታወቀ።


የፓርቲው ምክትል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ጉዳዩን በማስመልከት በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በመንግስት በኩል ሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ ፈጣን ምላሽ በአቶ ሽመልስ ከማል በኩል መገለፁን ፓርቲው መገንዘቡን ከገለፁ በኋላ በሚኒስትር ዲኤታው በኩል የተገለፀው ነገር የመንግስት አቋም ስለመሆኑ ቢያጠራጥርም ምላሹ ግን የህግ ትርጓሜን በማዛባት የቀረበ ነው ብለዋል።

“አቶ ሽመልስ ከመዛት ግላዊ ባህሪያቸው ተነስተው “ሕግ የሚያመጣውን መዘዝ ለመቀበል ይዘጋጁ” ማለታቸው ሁላችንንም ያሳዘነ አገላለፅ ነው። እኛ ሕግ አስተማሪና ቀጪ መሆኑን እንጂ መዘዝ መሆኑን አናውቅም። ካጠፋን ልንማር እንችላለን መንግስትም ካጠፋ ከስህተቱ ሊማር ይገባል ብለን እናምናለን። ስለዚህ የህግ መዘዝ አለው ማለት ለእኛ ከዛቻ የተሻለ ትርጉም የለውም” ብለዋል። አቶ ሀብታሙ ጨምረው እንደገለፁት የሚኒስትር ዲኤታው ንግግር በፖለቲካ ይዘትም ሆነ ከህግ አንፃር መሰረት የሌለው ነገር ከመሆን በዘለለ ይሄንን ሀገር በተሻለ ብቃት የመምራት አቅም ማጣታቸውን ማሳያ ነው ብለዋል።

አቶ ሽመልስ ከማል ካነሱዋቸው ነጥቦች መካከል “ሰልፉ ባልተፈቀደ ቦታ ተካሂዷል” የሚለው ወቀሳ ነው ያሉት አቶ ሀብታሙ “በእርግጠኝነት የአዲስ አበባ አስተዳደር ለአንድነት ፓርቲ በፃፈው ደብዳቤ የሰላማዊ ሰልፉ መነሻ ከፓርቲው ጽ/ቤት ተነስቶ በቀበና አደባባይ አድርጎ፣ ወደ ጃንሜዳ አምርቶ፣ ሰልፉ እዛው ጃንሜዳ እንዲጠናቀቅ የሚል ነው። ይህ ውሳኔ የደረሰንም የእኛን ሰልፍ ለማደናቀፍ፣ ያቀረብናቸውን ዘጠኝ አማራጮችንም በመቀልበስ፣ ባልፈለግነውና ባልመረጥነው ቦታ እንዲፈፀም ነው የተደረገው። ይህ ነገር ከሞራልም ከህግም አንፃር ተቀባይነት ባይኖረውም ለህግ ተገዢ በመሆን ወደ መስቀል አደባባይ የምናደርገውን ጉዞ በፖሊስ በከፍተኛ ኃይል መጥቶ መንገድ በመዘጋቱ፤ ከፖሊስ ጋር ግብግብ መፍጠሩን በመተው ወደቀበና አደባባይ በመዞር ቀበና አደባባይ ላይ ሰልፉን ለማጠናቀቅ ተገደናል። ወደጃንሜዳ ያልሄድንበት ምክንያት ኢህአዴግ ህግ እንድንጥስ በር ሲከፍትልን ህግ ላለመጣስ ብለን ወደጃንሜዳ አልሄደንም። ጃንሜዳ ያልሄድነው ቦታው ከጦር ካምፕ በ20 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ የሀገሪቷ ህግ ደግሞ ማናቸውም ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከጦር ካምፕ ካለበት ቢያንስ 500 ሜትር ርቆ መካሄድ አለበት ስለሚል ነው” ብለዋል። ይህም ባልተፈቀደ ቦታ ሰልፍ ማካሄድ ሳይሆን ለሀገሪቱ ህግ ያለንን ተገዢነት ያሳየንበት ስለሆነ ሁኔታው የእኛን ሕጋዊነት ያሳየ ሲሆን በአንፃሩ እነ አቶ ሽመልስ የሚመሩት መንግስት ሕገ-ወጥነት ማረጋገጫ እንደሆነ ጠቅሰዋል። በሕግ አግባብ ሲታይ ሃያ ሜትር የጦር ካምፕ ስር ሄዶ መሰለፍ ነው ወይስ እንዲሰለፉ ፈቃድ የሰጠው አካል  የሚጠየቀው? ሲሉ ጥያቄውን በጥያቄ መልሰዋል።


























“ሌላው በነፃ ፍርድ ቤት አሸባሪ የተባሉትን ሰዎች እንደ ሰማዕት አስመስለው “መልዕክቶቻቸውን አንብበዋል” የሚለው የአቶ ሽመልስ ማስፈራሪያ ከሀገሪቱ ሕገ-መንግስት ጋር ይጋጫል የሚሉት አቶ ሀብታሙ የሀገሪቱ ሕገ-መንግስት በግልፅ እንዳስቀመጠው ማንኛውም የፍርድ ቤት ውሳኔ ከፍርድ ውሳኔ በኋላ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ መቃወም ወንጀል ሳይሆን መብት ነው ብለዋል። እንኳንስ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ቀርቶ አንድ ግለሰብ ከፍርድ ውሳኔ በኋላ ውሳኔውን መቃወም መብት ሆኖ ሳለ አቶ ሽመልስ ግን ነፃ በሚሉት ፍርድ ቤት የተወሰነውን ውሳኔ ጥሳችኋል ማለታቸው ተገቢም ተቀባይነትም የለውም ብለዋል።

“አቶ ሽመልስ የሚመሩት ድርጅት በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ነፃ ናቸው ብሎ ያምናል። በአንፃሩ የእኛ ፓርቲ ደግሞ ነፃ ፍርድ ቤት የለም ብሎ ያምናል። በዚህ ረገድ የአቋም ልዩነት አለን። ነፃ ፍርድ ቤት የለም ብለን አቋም መያዝ የፖለቲካ መብታችን ነው። አቶ ሽመልስ ይሄ የፖለቲካ መብት መሆኑ ካልገባቸው በቀር ነፃ ፍርድ ቤት የለም ብለን ስናበቃ፤ ነፃ ያልሆነ ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ አንቀበልም ማለት በእኛ እምንት ተገቢ ነው። ህግ መጣስ የሚመጣው ያ ነፃ አይደለም ያልነው ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ በኃይል ለመቀበልስ ከሄድን ብቻ ነው። እኛ ግን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በሰላማዊ መንገድ ነው የተቃወምነው። ይሄ ደግሞ መብት ነው እንጂ ወንጀል አይደለም” ሲሉ አቶ ሀብታሙ መልሰዋል።

በተጨማሪ አቶ ሽመልስ “በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ሽብርተኝነት አበረታተዋል” ሲሉ ከሰውናል ያሉት አቶ ሀብታሙ በመጀመሪያ ደረጃ እኛ የታሰሩት ሰዎች ሽብርተኛ ናቸው ብለን አናምንም። አለማመን ደግሞ መብት ነው። ፍርድ ቤቱ የሰጠውንም ውሳኔ ተገቢ ነው ብለን አናምንም። እንደ ፓርቲም መቃወማችንን እንቀጥላለን። እነሱ ሽብርተኛ ያሉዋቸው ሰዎች ቀደም ሲል እስር ቤት ሆነው ኀሳባቸውን በተለያዩ ጋዜጦችና መፅሔቶች ሲገልፁ ቆይተዋል። ነገር ግን ለኢህአዴግ ህመም የፈጠረበት በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ሲገለፅ ነው። ይሄ ደግሞ የሰልፉ ውጤት ኢህአዴግን ስላስከፋው እንጂ ህግ መጣስ አይደለም። በተጨማሪም አንድ ሰው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ኃይሉ ዜሮ በሆነበት ሁኔታ “አበረታታችኋል” ማለቱ ትርጉም የለውም። ስለዚህ ሽብርተኝነትን የምናበረታታበት ምንም ዕድል የለም ብለዋል።

የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በተመለከተም በትክክልም በፍርድ ሂደት ላይ ያለ ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሀብታሙ በፍርድ ሂደት ላይ ያለን ነገር መቃወም ተገቢ አይደለም ብለዋል።

“ነገርግን አቶ ሽመልስ የተረዱን አይመስለኝም” ያሉት አቶ ሀብታሙ እኛ እየተቃወምን ያልነው ፍ/ቤቱን ሳይሆን ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን “ጀሀዳዊ ሀረካት” የሚል ዘጋቢ ፊልም ሰርቶ ተጠርጣሪዎቹን “አሸባሪ” ብሎ ከፍርድ ቤቱ በፊት መወሰኑን ነው። ይሄንን ደግሞ በአደባባይ መቃወም አሸባሪን መደገፍ አይደለም። ፍርድ ቤቱ የሚወስነውን ከወሰነ በኋላ ደግሞ የምንይዘውን አቋም እንይዛለን። ነገር ግን አሁን ፍርድ ቤቱ “ተጠርጣሪ” እያላቸው ኢቲቪ ግን “አሸባሪ” ብሏቸዋል። እኛ ደግሞ “የለም እነዚህ ሰዎች ተጠርጣሪ እንጂ አሸባሪ አይደሉም” ብለን ተሟግተናል። የምንቃወም ይሄንኑ ነው በማለት አስረድተዋል።

“ሌላው በሽብርተኝነት የታሰሩ ይፈቱ ብላችኋል” የሚለው የአቶ ሽመልስ ከማል ክስ በተመለከተም ፍ/ቤት በነፃነት የመወሰን መብቱ ኢቲቪ ባስተላለፈው ፊልም ነፃነቱን በመጋፋቱ በተያዙት ሰዎች ላይ ነፃ ፍርድ ይሰጣል ብለን አናምንም። ስለዚህም ሰዎች በነፃ ይለቀቁ ብለን መጠየቃችንን የሕግ መዘዝ ያመጣል ማለት የመንግስት ስልጣናቸውን ከመመካት የሚመነጭ እንጂ የሕግ መሰረት የለውም ብለዋል። በአጠቃላይ የአቶ ሽመልስ ምላሽ በግብታዊነት ፓርቲው ላይ እርምጃ ለመውሰድና ሰላማዊ ትግሉን ለማዳፈን በመሆኑ መዘዙ የከፋ ነው ሲሉ በበኩላቸው መልሰዋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማል እሁድ ዕለት ማምሻውን ለኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት በሰጡት ማብራሪ አንድነት ፓርቲ ባልተፈቀደለት ቦታ ሰልፍ ማካሄዱን እንዲሁም በሰልፉ ላይ በሽብርተኝነት ጥፋተኛ ተብለው የታሰሩ ሰዎችን በማወደስና እንዲፈቱ በመጠየቅ ሽብርተኝነት ማበረታታቱን በመግለፅ ህገ ወጥ ተግባር መፈፀማቸውንና ፓርቲውም ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ መጠየቃቸው አይዘነጋም።

ከሕግ በላይ ያበጡ የወያኔ ካድሬዎች!!

ከሕግ በላይ ያበጡ የወያኔ ካድሬዎች!!!
መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በደሕንነት ኃይሎች ታፍነው የተወሰዱት የሰማያዊ ፓርቲ የብ/ም/ቤት አባል የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ እና አቶ ስሜነህ ፀሀይ በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቢቀርቡም የከሳሽ ፋይል ባለመቅረቡ አንድ ተጨማሪ ቀን በእስር እንዲቆዩ ተደርገው እንደገና ዛሬ መስከረም 21 ቀን 2006 ዓ.ም. የዋለው የአራዳ ምድብ ችሎት በአንድ መቶ ብር (100.00 ብር) ዋስትና የለቀቃቸው ቢሆንም በደህንነቶች ስውር ትዕዛዝ የሚመራው የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለፍርድ ቤቱ ውሳኔ አልገዛም በማለት ወደአልታወቀ ስፍራ የሰወራቸው መሆኑንና ባለፉት ሁለት ቀናት በሁለቱም ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፖሊስ እንዳካሄደባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡