MARCH 2, 2014 LEAVE A COMMENT

ለዛሬው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ቃለ ምልልስ የሰጡት አይተ ስብሃት ነጋ ሕወሃት ዴሞክራሲያዊ መሆኑን በማስመር ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት በድርጅቱ የተለመደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡‹‹ሕወሃት ውስጥ በነጻነት መናገርና መጻፍ ይቻላል››ብለውናል፡፡መቼም አቦይ ላለፉት 22 ዓመታት ስልጣን ላይ ስለቆየው ሕወሃት የተናገሩ ከሆነ አስገራሚ ነው፡፡ምናልባት አንድ እኔ ስላላወቅኩት በሌላ አገር ስለሚገኝ ሕወሃት ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡
የእኛ አገሩ ሕወሃት ስብሃት የሚሉት ቁመና እንደሌለው ለማወቅ የድርጅቱ የፖሊት ቢሮ አባል መሆንን አይጠይቅም፡፡ሕወሃት ለተለየ ሐሳብ ቦታ የሌለው አባላቱን እንደ አንድ የፋብሪካ ሳሙና አንድ አይነት መልክ እንዲላበሱ የሚያደርግ አዲስ ሐሳብ ይዘው የሚመጡበትን እነ እከሌ ‹‹የድርጅቱ ጋንግሪን ሆነዋል››እያለ ከመቁረጥ የማይመለስ፡፡አመራሮቹንና አባላቱን እንደ ገደል ማሚቶ በሊቀመንበሩ የተባለውን ብቻ እየተቀባበሉ እንዲያስተጋቡ የሚያዝ ውስጣዊ ዲሞክራሲን የማያውቅ ለመሆኑ ድርጅቱን የተሰናበቱ ሰዎችን በመጠየቅ መረዳት ይቻላል፡፡
የአረና ሰዎች በትግራይ ክልል ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንቅፋት እየፈጠረ አረናዎችን በድንጋይ ማስደብደቡና ለእስር መዳረጉ የሚያሳየው ድርጅቱ የተለየ ሐሳብ ለህዝቡ መቅረቡን ምን ያህል እንደሚፈራ ነው፡፡
ስዬ አብርሃ፣አስገደ ገብረስላሴ፣አረጋሽ፣ገብሩ አስራትና ሌሎችም የሕወሃት የቀድሞ አመራሮች ከድርጅቱ የወጡት ከሊቀመንበሩ የተለየ አቋም በማራመዳቸው ነበር፡፡በሀሳብ የተለዩትን ሰዎች ሕወሃት የሚሸከምበት አቅም በማጣቱም አመራር ሲሰጡለት የከረሙትን ለእስር በመዳረግ የሐሳብን መንገድ ፈጽሞ እንደማያውቃት አሳይቷል፡፡ዛሬ ደርሶ አቦይ ሕወሃትን ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ መሞከራቸው አስቂኝ ይሆናል፡፡

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar