lørdag 1. november 2014

የተመስገን መታሠር እንዳሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በነበረው በተመስገን ደሣለኝ ላይ የተላለፈው የእሥራት ፍርድ እንደሚያሳስበው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በነበረው በተመስገን ደሣለኝ ላይ የተላለፈው የእሥራት ፍርድ እንደሚያሳስበው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አስታወቀ፡፡
ሃሳብን የመግለፅ መብታቸውን በመጠቀማቸው ታሥረዋል ያላቸውን ጋዜጠኞችም የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲፈታ ዩናይትድ ስቴትስ በድጋሚ ጥሪ እንደምታስተላልፍ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ አስታውቋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ወይም ሌላ ማንም መንግሥት ስላለ ሳይሆን ኢትዮጵያ መብቶችና ነፃነቶች የተከበሩባት ሃገር ነች፤ ሲሉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡
ለተጨማሪና ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar