søndag 21. juli 2013

ለሀገርህ ስትል አጥብቀህ አስብ

ኢትዬጵያ አገራችን ስሟ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቀስላት በውስጧ ከ 82 በላይ ቋንቋ ያላት ከ 85 ሚሊዬን በላይ እንዳላት የሚነገርላት ከዛሬ 6400 ዘመናት በፊት ጀምሮ የሰው ልጆች እንደሰፈሩባት በታሪክ የሚታወቅ ናት ። በተለይም በዓለም ሕዝቦች እጅ በሚገኝው መጽሐፍ ቅዱስ እንደጠቀሰው በስልጣኔና በንግድ ዘርፍ እንዲሁም በብልፅግናና በመንግስት ደረጃ ከታወቀች ሶስት ሺህ ዘመናት አስቆጥራለች ። ኢትዬጵያ ከድሮ ጀምሮ የነፃነት ምድር የተረጋጋ ሠላም የሰፈነባት አገር መሆኗ ከባህር ማዶ በተለያየ ጊዜ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ መሸሸጊያቸውና መጠጊያቸው ኢትዬጵያ ነበረች።እንዲሁም በአምስተኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ለምሳሌ ያክል ቀደም ባሉት ዘመናት በሐይማኖትና በባሕል የሚመሳሰሉትን ቤተ እስራኤሎች አገራቸው በተለያየ ጠላት ስትወረር ነፍሳቸውን ለማተረፍ ከግብፅ እና የሱዳንን በረሃ አቋርጠው የመጡት ወደዚች ምድር እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ብቻ ሳይሆኑ የትውልዳቸው እርዝራዥ የአካል ምስክር ነው።እንዲሁም በ 5ኛው መቶ ክ/ዘመን በእስያና በአካባቢው በጣኦት አምላኪዎች እንደ ባይተዋር ተቆጥረው ነፃነታቸውን ተገፍፈው ስቃይ በበዛባቸው ጊዜ ከስለትና ከሰይፍ አምልጠው የመጡትን በደስታ ተቀብላ ማረፊያ ቦታ እና የአምልኮ ቦታ መስጠቷ የአቡነ አረጋዊ ደብረዳሞ ገደላቸው ምስክር ነው።እንዲሁም በ 7 ኛው ክ/ዘመንም በመካከለኛው ምስራቅ የእስልምና ሐይማኖት ሲመሠረት በተፈጠረው አለመግባባትና በተነሳው ጦርነት አገራቸው በደም ስትነከር አይተው ተስፋ የቆረጡ መሀመዳውያን ነፍሳቸውን ለማትረፍ አማራጫቸው ኢትዬጵያ ብቻ በመሆኗ ቀይ ባህርን አቋርጠው ሲመጡ በሯን ከፍታ የተቀበለቻቸውና ነፍሳቸውን ያዳነችውና የክፉ ቀን ባለውለታቸው መሆኗን አፉቸውን ሞልተው ይመሰክሩላታል።ይህ ሁሉ የሚያሳየው በቋንቋና በዘር እንዲሁም በሐይማኖት የማታምን አገር መሆኗን ነው በአጠቃላይ ኢትዬጵያ የሠላምና የነፃነት አምባ የሁሉም ነገድ ስብስብ የብሄረሰቦች መገኛ ስትሆን ሕዝቦቿም በቋንቋ በዘር በሐይማኖት በባህል እንቅፋት ሳይሆንባቸው ተስማምተው፣ተቻችለው፣ተሳስበው፣ተፈቃቅረው በጋብቻ ተቀላቅለው የሚገኙባት አገር ናት።ያለፉት መሪዎቿም በአንድ ኢትዬጵያዊ እንጂ በዘርና በጐሳ የታሰረ መንፈስ ሳያስቀመጡላት ማለፉቸው የማይካድ ሃቅ ነው ዳር ድንበሯን ጠብቀው በኪነ ጥበብ አስውበው ፊደል ቀርፀው የዘመን መቁጠሪያ ቀምረው የማንም ጥገኛ እንዳትሆን አድርገዋት አልፈዋል ግን ይህ እስከ 1983 ዓ/ም ያለው ታሪክ ነው።ከላይ ብዙ የተነገረላትና የተዘመረላት ኢትዬጵያ በ 1983 ዓ/ም የአሁኑ ገዢ መንግስት መንበረ ስልጣኑ ላይ ከተቀመጠ ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ባለው ጊዜ የ 21 ዓመት ጉዞ ውስጥ የብሔራዊ አንድነቷ ፈርሶ ሰላሟ ደፍርሶ ታሪኳ ተበላሽቶ ድንበሯ ተቆራርጦ ክብሯ ተጥሶ የታየበት አሳፉሪ ዘመን ነው።የአሁኑ ገዥ መንግስት የኢትዬጵያን ዳር ድንበር እንደ ባቢሎን ሰዎች ከመግባባት ወደ አለመግባባት ከመፏቀር ወደ መቃቃር ከመከባበር ወደ መናቆር ከአንድነት ወደ ልዩነት ከኢትዬጵያ ህብረት ወደ ክልላዊ ስሜት እንዲያዘነብሉ ያደረገ የጥፋት መንግስት ነው።ይህ መንግስት ቀደም ያሉት ታሪካዊና ወርቃማ ዘመናት በትውልዱ ዘንድ እንዲጠሉ ለማድረግ አነዱን ጨቋኝ ሌላውን ተጨቋኝ በማስመሰል ጥላቻን እየሰበከ ያቀዘቀዘ ብሔርን ከብሔር ጐሳን ከጐሳ በማናከስ ተዋልደው በደም የተሳሰሩትን ደም ያቃባና ያፋታ መንግስት ነው።ለምሳሌ ያህል ጥቂቶቹን እናስታውስ የጋምቤላን ህዝቦች እርስ በእርሳቸው በማጋጨት የኮንሶንና፤የቦረናን ብሔረሰቦችን የጉጂንና፤የደራሳን ብሔረሰቦች በወለጋ የኦሮሞንና፤የአማራውን ህዝብ በማጋጨት በሺህ የሚቆጠሩ ህዝቦችን ያስጨፈጨፈና ያጫረሰ እጁን በደም የታጠበ መንግስት ነው።የቅርብ ጊዜ ትውስታችን እንኳን የሚረሳ አይደለም በ1997 ዓ/ም  በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ የሰጠነውን ድምፅ ተነጥቀናል ድምፃችን ይመለሰ በሚሉ ንፁሐን ዜጐች ላይ በጠራራ ላይ በወሰደው እርምጃ ከ 284 ሰው በላይ ህይወት የቀጠፈና የፈሰሰው ደም በተመለካች ህሊና ውስጥ አልደረቀም ።በሐይማኖት በኩልም ብንወስድ ገዥው መንግስት ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በአሰቦት ገዳም በመነኰሳቱና በአካባቢው ህዝብ ላይ የደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ አርባ ምንጭ ላይ ፕሮቴንስታቱን ከኦርቶዶክሱ በጅማና በኢሉባቦር በስልጤና በጋምጐፋ በማጋጨት የፈሰሰውን ደም ሁሉ በዓይን ላየው ሁሉ መፈጠሩን የሚጠላበት ክስተት ነው ።እንዲሁም በጅማ ከ 50 ያላነሱ የፕሮቴንስታት ቤተከርስቲያኖች ከነሙሉ ንብረታቸው መውደማቸው የሚታወቅ ነው ።ይህ መንግስት ሙስሊሙን ከኦርቶዶክሱና ከፕሮቴንታንቱ ተፋቅሮና ተቻችሎ እንዳይኖር አንዱነን በአንዱ ላይ እያነሳሳ የሐይማኖት ተቋማትን ሲያቃጥሉ ዳር ቆሞ እሳት የሚሞቅ መንግስት ነው።እነዚህ ተቋማት እርስ አልጋ አልጋጭ ቢሉት እንኳን እርስ በእርሳቸው እንዲጋጩ በውስጣቸው እንዲጋጩ ሙስሊሙን ከሙስሊሙ ኦርቶዶክሱን ከኦርቶዶክሱ ፕሮተንስታንቱን ከፕሮቴንታንቱ በማጋጨት በውስጣቸው በውስጣቸው ሰላም እንዳያገኙ እያደረገ ይገኛል።ከዚህም አልፎ ለዘመናት በነበሩት መንግስታት ተከብሮ የቆየውን የዋልድባን ገዳም በማፈራረስ በውስጡ ቅጠላ ቅጠል እና ፍራፍሬዎች እየተመገቡ ለመላው ዓለም ፀሎት የሚያደርጉ የበቁ አባቶች ይኖሩበት ዋሻ በማፈራረስ መነኰሳቱንም እያሳደደ በእጁ የገቡትን አስሮ እያሰቃየ እና እየገደለ ይገኛል በገዳማቱ ውስጥም የሚገኙትን ቅርሶችንም ያለ ውርስ እየሰረቀና እያጠፋ ይገኛል በዚህ ከቀጠለ በአገራችን ውስጥ ታሪክም ቅርስም ህዝብም ሐይማኖትም ተሟጥጠው ያልቃሉና ውድ የሀገሬ ልጅ ሆይ ለኢትዬጵያና ለህዝቧ ስትል አጥብቀህ አስብ።

ኢትዬጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!                                        

ተጻፈ በዳዊት ደመላሽ ( ኖርዌይ )

Madenate.dawit@gmail.com

የእስክንድር ነጋ ደብዳቤ ከቃሊቲ እስር ቤት ለባራክ ኦባማ የተፃፈ

     ግልፅ ደብዳቤ ለኦባማ አስተዳደር!

          እስክንድር ነጋ

        ከቃሊቲ እስር ቤት






 ሁላችንም እንደምናውቀው በሀያኛው ክፍለ ዘመን የመጨረሻ ዓስርታት በተለያዩ ክፍለ አህጉራት ውስጥ ባለ ታዲጊ ሀገር  ህዝቦች የተነሱ የፖለቲካ እና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች በቀዳሚነት በጠመንጃ ኃይሌ የተደገፉ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያም በተመሳሳይ  የታሪክ ክስተት ማለፏን የሚመሰክረው ዛሬም ወታደራዊ ስርዓቱን ብቻ ሳይሆን፣ ይህንን መንገዴ የመረጡትን ጥቂት  የተቃዋሚ ድርጅቶችንም በጦር ኃይል ድል አድርጎ ስልጣን ላይ ያለው ኢህአዴግ መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና የቀዝቃዛው ዓለም  ጦርነት ማብቃትና የአሜሪካ ብቸኛ ሌዕለ ሀያል ሀገር ሆኖ መውጣት በኃይል የሚደረጉ ‹‹ፀረ-አምባገነን›› ንቅናቄዎች  ሰላማዊውን መንገዴ ብቻ እንዲከተሉ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡ የለውጡም ዋነኛ መፍትሄ አሜሪካ ለሰላማዊ ትግል  የምትሰጠው ከፍ ያለ ቦታ ብቻ ሳይሆን የምታደርገው እገዛም መሆኑ አከራካሪ አይደለም፡፡ በእርግጥ የአሜሪካ አስተዳደር  በሰላማዊ ትግል ላይ ያለው አቋምና ለትግሉ የሚያደርገው ቀጥተኛ አበረታችነት የሀገሪቱ መስራች አባቶች ካነፁት የሞራሌ እና  የፖለቲካ እሴት እንደሚነሳም አውቃለሁ፡፡

 ሙሉውን ደብዳቤው ሊንኩን በመጠቀም ዳውን ሎድ በማድረግ ያንብቡት!

https://docs.google.com/file/d/0B6jhgT-afGuONWtmWlBWeXBqWGM/edit?pli=1


መድረክ በመቀሌ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አደረገ

መድረክ በመቀሌ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በስኬት እንደተጠናቀቀ የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡

የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ አቶ ክብሮም ብርሃነ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት መድረክ ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2005 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ያካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች የተገኙበት ነበር፡፡ በአብዛኛው ወጣት የሆኑ የመቀሌ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይህ ስብሰባ የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር በሆኑት በአቶ ጥላሁን እንደሻው፣ በአቶ ገብሩ አስራትና በአቶ ብርሀኑ በርኸ የተመራ ሲሆን ተሰብሳቢዎቹም የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ስብሰባውን ስኬታማ አድርገውታል፡፡

በተሰብሳቢዎቹ በትግራይ ክልል የሚታዩትን የመልካም አስተዳደር፣የሙስናና የግብር አሰባሰብ ችግሮችን በመንቀስ በመንግስት ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ቅሬታ ማንፀባረቃቸውንም አቶ ክብሮም አስረድተዋል፡፡ “መድረክ ላይ የነበሩት ተናጋሪዎች ሞቅ ባለ ጭብጨባ ታግዘው ተናግረዋል” ያሉት አቶ ክብሮም ስብሰባውን ለማደናቀፍ በአዳራሹ ውስጥና ውጪ በተደራጀ ሁኔታ ተሰብስበው የነበሩት ከየቀበሌው የተውጣጡ ካድሬዎች የተሰብሳቢው ሁኔታ አስደንድጧቸው እንደተበተኑም ተናግረዋል፡፡ በትላንትናው እለት የመኪና ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የነበሩ ሁለት የአረና ትግራይና አንድ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች መቀሌ ውስጥ ከነመኪናቸው በህገወጥ መንገድ ታስረው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

fredag 19. juli 2013

አሸባሪዉ ኢህአዴግና የፀረሽብር ህጉ መወገድ አለባቸዉ

ከተስፋዬ ተካልኝ

ኢትዮጵያንና ህዝቧን የአብሮነትን መሠረት ለመሸርሸርና ብሎም ለማጥፋት ሌተ ቀን የማይተኛዉ የህወሀት ኢህአዴግ አሸባሪ መራሹ መንግስት በህዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጦ ዜጎችን ማሰቃየት ከጀመረእነሆ ፪፪ አመት ተቆጥሮዋል።ነገር ግን የ፪፪ አመት ቆይታዉ ህዠብን ከማሸበር፣ ከመግደል፣ከማሰር ከማሰደድ፣ከመግረፍና ከማፈናቀል አልፎ በተመቸዉና የጥፋት ምርቃናዉ በመጣለት ቁጥር በዘረኞች መሪዎቹአማካይነት በፈለገዉ ሰዐት ከራሱ ህግና ስርአትዉጪ ከእንቅልፋ እንደሚነቃና የሚያደርገዉን እንደማያቅ ህፃን ልጅ የተለያዮ ህጎችን በማዉጣት ጭምር ህዝባችንን ከህዝባችን እንዲሁም ሀገሪቱዋን ባለቤትየሚያሳጣ አስነዋሪ ህጎች በማርቀቅና ድራማ በመስራት ማፍያ ስርአት መሆኑ ይታወቃል።

ከእነዚህ የህወሀት ኢህአዴግ አስነዋሪ ህጎች አንዱ እኤአ ፪፻፱ በሙዋቹ ቀንደኛ ማፍያ መሪያቸዉ መለስ ዜናዊ መሪነትና በሌሎች አጭበርባሪ ሆዳም የሀገር ፍቅር በሌላቸዉ ተከታዮች አማካይነት የፀረ ሽብርህግ አዉጥቶ ፭፬፩ እጅ በሚያነሱለት የፓርላማ አሻንጉሊቶቹ ድጋፍ ማፀደቁ የሚታወቅ ነዉ።

ይህ ህግ አሁንም በባለ ጥፋቱ መሪያቸዉ የሙት መንፈስ ራእይ ስምና በተተካዉ አሻንጉሊት መሪ ሀይለማርያም ደሳለኝ ህጉ እንደቀጠለ ሲሆን ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚያሸብረ ወያኔ ሆኖ ሳለ ነገር ግን በመሣርያየበላይነት በሀገሪቷ ዉስጥ ከወያኔ የተለየ ሀሳብ ያላቸዉ በህጉ የስቃይ ሰለባ እየሆኑ ነዉ ዛሬም።

ለዚህም ማስረጃ ሰሞኑን ወገናችን ተስፋዬ ተካልኝ በአንድነት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዉስጥ የሚሊዮኖች ድምፅ በሚል በሰጠዉ ቃለ ምልልስ ፪፫ ወራት፣ ለ፫ ወር ማዕከላዊ ለ፩፱ ወር ደግሞ በዝዋይ እስርቤት በወያኔ ኢሰብአዊና አረመኔያዊ የጭካኔ በደል ፍዳዉን አብልተዉ የቁም ሞት ገለዉ ከለቀቁት በዉኃላ በዚህ የፀረ ሽብር ህግ ምክንያት ህይወቱ ጉዳና ላይ ወድቋል ንፁሀን ዜጎች ከሱ ጭምር የህጉ ሠለባመሆናቸዉን ከአንደበቱ ሰምተናል።

ስለዚህ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት ዛሬ ነገ ሳይል እንደ ተስፋዬ ተካልኝ እይነት ሚሊዮኖችን ከተለያዮ ግልፅና ስዉር የማሰቃያ ቦታዎች ሊታደጋቸዉ እንዲሁም አሸባሪዉ ህወሀት ኢህአዴግንና ፀረሽብር ህጉን ከኢትዮጵያ ማስወገድ አለበት።

እኔ ተስፋዬ ተካልኝ ነኝ እናንተስ?

በህወኃት ወያኔ ሞት!

የኢትዮጵያ ነፃነት!

የእስልምና ፅንፈኝነት ለሃይማኖት ወይስ ለፖለቲካ ነፃነት

ዛሬ ወደ ቢሮየ የ15 ደቂቃ ጉዞ ሳደርግ በአእመሮየ እየተመላለሰ በእንግሊዘኛ ሃሳቡ ይረብሼኝ ጅምሮዋል፡፡ ‹‹Islamic extremism freedom for politics or religion>> የሚል ሃሳብ እያብሰለሰልኩ ቢሮየ ደርሼ በጥዋቱ ስብሰባ ምሃል ወደ አራት ገጽ የሚደርስ ‹‹Islamic extremism freedom for politics or religion in Ethiopian context >> ብየ በእንግሊዘኛ ሃሳቤን አሰፈርኩ ግን አንባቢየ ማነው መረጃየስ ስል ወደ አማረኛ አለዝቤ ከኢንተርኔት መረጃዎች ተናብቤ ይህች የሰላም ምድር እንደ ድሮው ሰላም ትሆን ዘንድ ሃሳቤ አሰፈርኩ፡፡ ራሚደስ ከተባሉ የመጣጥፍ ጽሃፊ ጋር ሃሳቤ ይቀራረባል መጅመሪያ ለኔ የእስልምና “ፅንፈኛ አክራሪነት” ምን ማለት ነው የሚለውን ላይ መግባባት መቅደም ይኖርበታል፡፡  እስላሞቹ ሱሪያቸውን አሳጥረው፣ ፂም አሳድገው ሲሄዱ፣ ሴቶቹ ሲሸፋፈኑ፣ በቀን አምስት ጊዜ  ሲሰግዱ፣ የሮመዳን ወር ሲፆሙ፣ መካን ጨምሮ ወደተለያዩ የሀገራችንና የአለማችን ክፍሎች መንፈሳዊ  ጉዞ ሲያደርጉ ስንመለከት እከሌ/እከሊት እኮ አክራሪ ሆነ/ች ሲባል መስማቱ እንግዳ አይደለም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አንድ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ቤተሰብ ነጠላውን አገልድሞ ጎህ ሲቀድ ቤተ  እምነቱን ተሳልሞ፣ የመላእክትና የፃድቃን መታሰቢያ በአላት ላይ ጧፍ አብርቶ፣ ዳቦ ቆርሶ፣ሰንበትን  አክብሮ፣የሁዳዴን፣የሰኔን፣የፍልሰታን ፣የገናን፣የነነዌንና አርብ እሮብ ቀናትን በፆም በፀሎት ሲያሳልፍና  እየሩሳሌምን ጨምሮ ወደተለያዩ ገዳማት ሀይማኖትዊ ጉዞ ሲያከናውን ሲታይ እንዴት ያለ ፈሪሀ- እግዚአብሔር ያደረበት፣ ለሀይማኖቱ ቀናኢ የሆነ ቤተሰብ ነው ይባላል፡፡ በሙስሊሙ መነፅር ግን ይህ  ቤተሰብ በአክራሪ ኦርቶዶክስነት ሊመሰል ይችል ይሆናል፡፡ እዚህ ጋር ነው ችግሩ፡፡

በተለያዩ የማንነት እሴቶች ዙሪያ የተሰበሰቡ ወገኖች “ሌላውን” የሚመለከቱበት መነፅር ”የራሳቸውን” ከሚመለከቱበት ለየት ማለቱ ነው ችግሩ፡፡ ከዚህ በላይ በተነፃፃሪ የቀረቡት የእስልምና እና የኦርቶዶክስ ክርስትና ሀይማኖታዊ ክንዋኔዎቻቸውን አንዳንዱ በለዘብተኝነት ሲያከናውናቸው አንዳንዱ ደግሞ ከረር አድርጎ ይይዘዋል፡፡ ያከረረው ክፍል የራሱን እምነት አጠንክሮ መያዙ የሀይማኖቱ አጥባቂ እንጂ ፅንፈኛ አክራሪ ሊያስብለው የሚገባ አይመስልም፡፡ የየትኛውም እምነት ተከታይ በመሰለው መልኩ ሀይማኖቱን ቢያጠብቅ የሰው ልጅ መሰረታዊ መብት መሆኑን በዚህ በስልጣኔ ዘመን ለማስረዳት መሞከሩ ከንቱ ልፋት ይሆናል፡፡ የፅንፈኝነት አባዜው የሚመነጨው ከእኔ እምነትና አስተሳሰብ ውጭ ያሉት በሙሉ ትክክል አይደሉም፡፡ ትክክል አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን በወድም በግድም ወደ እኔ እምነት መቀላቀል ይኖርባችኋል፡፡ ሀገሪቱም መተዳደር ያለባት በእኔ ሀይማኖትና የአስተሳሰብ ፍልስፍና እንጂ በሌላ በማናቸውም መንገድ ሊሆን አይችልም፡፡ እምቢ አሻፈረኝ ባዮን ደግሞ ምድራዊ ቅጣት የመስጠት
መለኮታዊ ሀላፊነት አለብን ብሎ የሚያስብ መሰረታዊ የሰው ልጆችን የዜግነት፣ የእምነት፣ የመምረጥ  እና የአስተሳሰብ መብቶች ማፈን ሲጀምር ነው፡፡ ኢትዮጵያ በሸሪአ ህግ መተዳደር አለባት የሚል አስተሳሰብ ፅንፈኝነትን ገላጭ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት እንጂ ሌላ የማንም አይደለችም ባዩም ፅንፈኝነትን በትከሻው አዝሎ እየሄደ ነው፡፡ ፅንፈኛ አክራሪነት በሀይማኖት ስብስብ ብቻም አይገለፅም፡፡  ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው (በፖለቲካ ስልጣን፣ በንግድ እንቅስቃሴ፣ በሃገር መከላከያና የደህንነት መዋቀር በሙሉ) የእኔ ብሄርና ጉጥ ብቻ ነው የሚለውም የብሔር ፅንፈኛ አክራሪነት በሽታ በሰራ አካላቱ እንደተንሰራፈበት ገላጭ ምልክት ነው፡፡ በመሆኑም የአጥባቂነትን ከፅንፈኛ አክራሪነት ለይቶ ማየቱ ተገቢና አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑ ማስረገጥ ይኖርብናል፡፡

ከእስልምና እምነት አስተምህሮ መጀመር በፊት ከጣኦትና ክዋክብት አምልኮ ጀምሮ አለማችን ቡዲዝም፣ ጃይኒዝም፣ ሲኪዝም፣ ሂንዱዊዝም፣ የኮንፌሸንና ሌሎች ሀይማኖቶችን ስታስተናግድ ከርማለች፡፡ በተለይ በተለይ በአንድ አምላክ፣ በመላእክቶችና ተፃራሪ ሀይል ሆኖ በሚታመነው ሰይጣን መኖርን እንዲሁም ከሞት በኋላ ስለሚኖር ህይወት የገነትና የገሀነም ፅንስ ሀሳቦችን የሚሰብከው የቀድሞው የፐርሽያ ታዋቂ ገጣሚና ፈላስፋ ዞራስተር (ዛራቱሰቱራ) አስተምህሮ ከእየሱስ ልደት ወደ ሺህ አምስት መቶ አመታት በፊት የነበሩትን ህዝቦች ከማሳመኑና ከማስከተሉም ባለፈ የዞራሰትሪዝም አስተምህሮዎች በአምላክ አህዳዊነት (Monotheism) ላይ መሰረት ባደረጉ ሀይማኖቶች በተለይም ለይሁዳ፣ ክርስትናና እስልምና እምነቶች የአስተሳሰቦች አወቃቀር ሂደት ላይ ማገር ማቀበሉ የማይታበል ሀቅ ነው፡፡ የዞራስትሪዝም ተከታዮችን ማሳደዱና መጽሀፍቶቻቸውንም ማቃጠሉ ከአራተኛው አመተ-አለም ከታላቁ አሌክሳንደር የፐርሽያ ግዛትን መውረር አንስቶ የተከናወነና በመጠኑም አገግሞ የነበረውን የዞራስተሪዝም እሴቶች ከሰባተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ መስፋፋት የጀመሩት የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች እንዳያንሰራራ አድርገው መምታታቸው በታሪክ የተመዘገበ እውነታ ነው፡፡ በግዜው ወደ ህንድ የተሰደዱ የዞራስትሪዝም ተከታዮችና እዛው ኢራን አካባቢ ቀርተው ይኖሩ የነበሩ የእምነቱ ተከታዮች
በድብቅ ካስቀመጧቸው መፅሀፍቶቻቸው መረዳት እንደተቻለው የAhura Mazda (የበጎ መንፈስ) እና የAngra Mainyu (የክፉ መንፈስ) እሳቤዎች ለዛሬው የይሁዳ ኦሪት የክርስትና ወንጌልና የእስልምና ቁርአን የሚጋሩትን መሰረታዊ የሀይማኖቶቹ አስተምህሮዎች ምንጭ ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል፡፡ የይሁድና የክርስትና ሀይማኖቶች ታሪካዊ የአመሰራረት ዳሰሳ ለጊዜው ወደ ጎን አድርገን በዚህ ፅሁፍ ጭብጥ ማጠንጠኛ ስለሆነው የእስልምና ሀይማኖት ጥንሰሳ በወፍ በረር ቅኝት ብናደርግ ይመረጣል፡፡

torsdag 18. juli 2013

ኢህአዴግ በሩን እንዲከፍት የዓለም ባንክ አዘዘ

የማነቂያው ገመድ ከርሯል፤ “ትግሉ ይቀጥላል” ኦባንግ ሜቶ

ኢህአዴግ ለሚገዛት ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው ዕርዳታ የሚሠጠው የዓለም ባንክ፤ ለዕርዳታና ልማት የሚልከው ገንዘብ ኢህአዴግ የሕዝቡን ሰብዓዊ መብት ለመጣስ ተጠቅሞበታል በሚል ሙሉ ምርመራ እንዲካሄድ አዘዘ፡፡ የባንኩ ውሳኔ ኢህአዴግን የማነቂያው ገመድ እንደሚያከረው ተገለጸ፡፡ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል በሰጡት መግለጫ “ይህ በጥናት ከምናካሂደው ትግል አንዱ ውጤት ነው፤ ገና ጅማሬ ነው፤ ጠንክረን እንሠራለን” አሉ፡፡

የዓለም ባንክ ለልማት ሥራዎች የሚሰጠው የእርዳታ ገንዘብ በኢትዮጵያ በተለይም በጋምቤላ ክልል የሚኖሩትን ዜጎች ሰብዓዊ መብት በመጣስ ላይ ውሏል በሚል ከዚህ በፊት ክስ ቀርቦበት እንደነበር ይታወሳል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጉዳዩን ከ9 ወራት በፊት በዘገበበት ወቅት ተጠቂዎቹ ዜጎች ያቀረቡትን ማስረጃና የኢንስፔክተር ቡድኑ የሚያደርገውን ምርመራ በዝርዝር ሰፍሮ ነበር፡፡ በወቅቱ ምርመራውን ያደረገው የመርማሪ ቡድን (ኢንስፔክሽን ፓናል) በአካባቢው የሚገኙትን ተጠቂዎች ካነጋገረ በኋላ ለባንኩ የሥራ አመራር ቦርድ በሰጠው ሪፖርት በዕርግጥ የዕርዳታው ገንዘብ በሰብዓዊ መብት ረገጣ ላይ መዋሉን ይፋ አድርጓል፡፡

መንግስት ያደረሰበትን ሰቆቃ በፍኖተ ነፃነት ያጋለጠው ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ የገባበት ጠፍቷል




ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ የገባበት ጠፋ

ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት በመንግስት የደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በማዕከላዊና ዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ የደረሰበትን በደል ይፋ ቢያደርግ እንደሚገድሉት እንዳስጠነቀቁት ለፍኖተ ነፃነት አስረድቶ ነበር::

አሁን ተስፋዬ ተካልኝ በየቀኑ ይመላለስበት ከነበረዉ የአንድነት ቢሮ ከቀረ አንድ ሳምንት ሞልቶታል::የግል ተንቀሳቃሽ ስልኩም አይሰራም:: ተስፋዬ ተካልኝ ያለበትን ወይም የደረሰበትን አዉቃለሁ የሚል አንድ ይበል::

ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት

“እምዬ ኢትዮጵያ ግደይኝ”

ሰሞኑን እነዚህ እንግሊዞች ፀሀይ ቶሎ አትጠልቅባቸውም ከሌሊቱ 10 ሰዓት የበራች እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ሰማይ ላይ ተሰቅላ ትውላለች፡፡ መቼም እንደ እኔ ቀን እና ሰዓቱ እኩል እኩል ከተስተካከለባት አዲሳባ ለመጣ ሰው ይሄ እንግዳ ነገር አጃኢብ የሚያሰኝ …ድንቅ ነው፡፡

በአንድ ወቅት ሰዎቹ “በእንግሊዝ ምድር ፀሀይ አትጠልቅም” ያሉት ይቺን ወቅት አይተው ነው መሰለኝ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ይመጣል ከከሰዓቱ 10 ሰዓት ላይ ጨልሞ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት እንኳ የማይነጋበት ጨለማ ወቅት፤ ይሄኔ ነው “እምዬ ኢትዮጵያ ግደይኝ” የሚያሰኘው፡፡

በእኛ ሀገር የሰዎች እኩልነት ተቸገርን እንጂ፤ ቀን እና ሌሊቱ ዝንፍ አይልም እኩል ለእኩል ነው፡፡ በእርግጥ አልፎ አልፎ የገና ጀንበር እንደጎረምሳ በግዜ አልገባም ብላ ታመሻለች፡፡ እርሷም ብትሆን ግን ብዙ አይደለም ከወትሮዋ ሰላሳ ደቂቃ እንኳ መቆየቷን እንጃ! ትንሽ አምሽታ “አረ ቤተሰቦቼ ይቆጡኛል” ብላ ክትት ነው የምትለው!

ታድያ የሰሞኗ የእንግሊዞች ጀንበር በግዜ አልሰበሰብ ማለት ለምን አሳሰበህ ያላችሁኝ እንደሆነ ለሙስሊም ወንድሞቼ እና እህቶቼ እላችኋለሁ፡፡

እንግዲህ የረመዳን ፆም እየተፆመ አይደል… ታድያ እኮ በረመዳን አፍጥር የሚባለው (ምግብ የሚቀመሰው) ፀሀይ ስትጠልቅ ነው፡፡ ይቺ ዘልዛላ የእንግሊዝ ፀሀይ ደግሞ ወደ ሃያ ሰዓት ሰማይ ላይ ተሰቅላ ትውላለች… አስቡትማ የፆሙ ርዝመት!

በእንግሊዝ እና መሰል ሀገር ያላችሁ ሙስሊም ወዳጆቼ፤

አቦ አላህ ያበርታችሁ!

በአቤ ቶክቻው

lørdag 13. juli 2013

የነገው አበባ ለምን ለፌደራል ፖሊስ ይሰጣል?

አበባ የሰው ልጆች በአንድ ድምጽ ፍቅራችንን ወክልልን በማለት የመረጡት ይመስል የፍቅርን አደራ ተሸክሟል፡፡ከሶስተኛው አለም እስከ አንደኛው የሚገኙ የአዳም ልጆች ‹‹አበባን››የፍቅር ስጦታ በማድረግ ለሚወዱት ይቸሩታል፡፡የሚወዱት ሲሞትባቸውም ፍቅራቸውን ለሟቹ ለመግለጽ አስከሬኑ ላይ አበባ ያኖሩለታል፡፡

ወደ ደሴና ጎንደር እንምጣ፣ ነገ ከሌላው ጊዜ በተለየ አበቦች ለፌደራልና ለክልል ፖሊሶች በሰላማዊ ሰልፈኞች ይበረከታሉ፡፡እኛ ኢትዮጵያዊያን የጦርነት ታሪክ የከበበን በመሆኑ ለወታደር ያለን ፍቅር የተለየ ነው፡፡ዛሬ ድረስ ወታደራዊ ዮኒፎርም የለበሰ ሰው ሲመለከቱ ልባቸው ወከክ የሚልባቸው ቆነጃጅት ቁጥር የትየለሌ ነው፡፡

እንዳለመታደል ሆኖ ግን እንዲህ በስስት የምንመለከተው ወቴ በውስጥ ጉዳይ በአብዛኛው የገዢዎች መገልገያ ሆኖ በእናቱ ልጅ ላይ ቃታ ሲስብ አይኑን አያሽም፡፡ አዛዦቹ ያሉትን ካልተገበረ ምን እንደሚጠብቀው ስለሚያውቅ ድንጋይ ለወረወረ ሁሉ አጠፋውን በጥይት ከማድረግ አያመነታም፡፡ለዚህ አንገት ደፊ ታሪካችን ብዙ ማጣቀሻዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡

የነገው ሰልፍ አበባ የሚበረከትበት ዋነኛ አላማ ፍቅርን ለመስበክ ነው፡፡በወታደሩ፣በፖሊሱ፣በደህንነቱና በመንግስት ታማኝ ላይ የምንመዘው ሰበዝ ቢኖርም ነገ ግን ፍቅርን እንሰጣለን፡፡ምላሹ ምንም ይሁን ምን የአበባው መልዕክት ፍቅር ነው፡፡ የአበባ ቀን እንበለው ይሆን?

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!
አንድነት ኃይል ነው!! አንድነት ፍቅር ነው!! ፍቅር ያሸንፋል!!

‪#‎millionsofvoicesforfreedom‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬ ‪#‎Gonder‬ ‪#‎Dessie‬

ነጻነት ለተጠማ፤ምክር ለሚሰማ (ኢሕአፓ)

ሰባት ዓመት እንዳይማሩ ሰባ ዓመት ይደናቆሩ እንደተባለው ዛሬ ድርጅቶችና በፖሊቲካው መድረክ አለን ቁጠሩን የሚሉ ቡድኖች በፈሉበት ወቅት ካለፈው ትግልና መስዋዕትነት ተመክሮን መቅሰሙ ከብዶ ስህተቶችን መደጋገሙ ሰፍኗል። የዚህ ስህተት ዓይነታ መለያው ደግሞ ገና ሀ ብለው መቦደን ወይም መደራጀት ሲጀምሩ በሀገራችን በዘመናዊ የፖለቲካ ድርጅትነት የመጀመሪያው ሆኖ ስንት ተመክሮ የቀሰመውንና ዛሬም ህልውናውን ጠብቆ ያለውን ኢሕአፓን ማጥቃትና መወንጀልን አምርረው ይያያዙታል። ድርጅት ሲሉ ድርጅት ስንል በሚል በተደጋጋሚ የተቸን ቢሆንም ዛሬ ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ ኢሕአፓን ልዩ ያደረጉትን መሠረታዊ ይዘቶችና ተግባሮች፤ አቅዋሞችና መርሆዎች መጥቀስ እንፈልጋለን ።

Read more: http://www.ethiolion.com/Pdf/07062013Demo_Sene2005.pdf

Source: EPRP.com

የ600 ግለሰቦች የባንክ ሂሳብ በኮሚሸኑ ታግዷል

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መረጃ እየተሰባሰበባቸው በጊዜ ቀጠሮ ላይ የሚገኙ ባለሃብቶች በፀረ ሙስና ኮሚሽን የታገደባቸው የባንክ ሂሳብ እና ንብረት እንዲለቀቅላቸው ባለፈው ማክሰኞ ለችሎቱ አመለከቱ፡፡ ባለሀብቶቹ የባንክ ሂሳባቸው በመታገዱ በኩባንያዎቻቸው ተቀጥረው ለሚሠሩ ሠራተኞች ደሞዝ መክፈል እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡ የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን፤ እስካሁን የ600 ሰዎች የባንክ ሂሳብ መታገዱን ገልጿል፡፡ በእነ አቶ መላኩ ፈንታ መዝገብ ስር የተካተቱት የኬኬ ኃላፊቱ የተወሠነ የግል ኩባንያ ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ፣ የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባለቤት አቶ ስማቸው ከበደ፣ የአዲስ ልብ ሆስፒታል ባለቤት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ እንዲሁም በእነ አቶ ገ/ዋህድ መዝገብ ስር የተካተቱት የነፃ ትሬዲንግ እና ባሰፋ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገ/እግዚብሔር እና የአልትሜት ፕላን እና የኢትባ ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ በእግዚአብሔር አለበል በጠበቆቻቸው በኩል የእግድ ይነሳልን ጥያቄያቸውን ለፍ/ቤቱ አቅርበዋል፡፡

የኬኬ ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ በጠበቃቸው በኩል ባቀረቡት አቤቱታ፤ ኩባንያቸው ከ600 በላይ ሠራተኞችን እንደሚያስተዳድርና ድርጅቱ የባንክ ሂሳም በመታገዱ ለሠራተኞች ከግንቦት ወር ጀምሮ ደሞዝ መክፈል እንዳልቻለ፣ ኩባንያው መደበኛ ስራውን መስራት ባለመቻሉም መንግሥት በሁለት ወር ውስጥ ከግብርና ከታክስ ያገኝ የነበረው ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማጣቱን በመጥቀስ፣ በሀገር ኢኮኖሚና በሦስተኛ ወገኖች ላይም ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የአዲስ ልብ ሆስፒታል ባለቤት ዶ/ር ፍቅሩ በጠበቃቸው በኩል ባቀረቡት አቤቱታም የሆስፒታሉ ሂሳብ በመታገዱ ለሠራተኞች ደሞዝ አለመከፈሉን፣ መገዛት ያለባቸው የህክምና ቁሳቁሶች አለመገዛታቸውን እንዲሁም ሆስፒታሉ የስራ ማስኬጃ ገንዘብ መቸገሩን ያመለከቱ ሲሆን ተጠርጣሪው ራሳቸው ስለ ጉዳዩ እንዲያስረዱ ችሎቱን ጠይቀው ሲፈቀድላቸውም፤ በራሳቸው ስም የተመዘገበ አንድም ገንዘብ አለመኖሩንና ሆስፒታሉ በውጭ ድርጅት የሚተዳደር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

30 ሺህ በሽተኞችን የሚያክመው

torsdag 11. juli 2013

ሰበር ዜና: ከደሴ

አንድነት ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የከተማው መስተዳደሮችና የፀጥታ ኃይሎች ፓርቲው ህጋዊ የማሳወቅ ስራውን መስራቱን ገልፀው ሰልፉን መከልከል እንደማይችሉ ካረጋገጡ በኋላ በከተማው ያሉ የቀበሌ ሰራተኞች መደበኛ ስራቸውን ጥለው በሰላማዊ ሰልፉ ዙሪያ በየቤቱ እየዞሩ ማስፈራራትና ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ማንም እንዳይገኝ፣ ሰልፉ ህገወጥ ነው በሚል ቅስቀሳ እየሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ ነዋሪው በበኩሉ የፓርቲው ጥያቄ የእኛም ጥያቄ ስለሆነ በሰልፉ ላይ እንገኛለን፣ ፓርቲው የሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ህገወጥ ከሆነ እነሱን (ፓርቲውንና ቅስቀሳ የሚሰሩትን ) ለምን አታግዷቸውም የሚል ጥያቄ ሲያነሱባቸው፤ ለቅስቀሳው የተሰማሩት የቀበሌ ሰራተኞች እምቢ ብለው የሚወጡ ካሉ እስራት ይጠብቃቸዋል፤ በሚደርስባቸው ችግር ኃላፊነቱን አንወስድም ሲሉ ማስፈራሪያና ዛቻ መፈፀማቸው ተጠቁሟል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ብስራት አቢ ቅስቀሳ በማድረግና በራሪ ወረቀት ሲበትኑ መጀመሪያ የደሴ ከተማ 4ኛ ፖሊስ ጣቢያ ያለምንም ምክንያት አስሯቸው የጣቢያው አዘዦች ከሰዓታት በኋላ ሲለቋቸው 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ በድጋሚ ምክንያቱን ሳይገልፅላቸው ለአንድ ሰዓት አስሮ እንደለቀቃቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ብስራት አሁንም ድረስ መስተዳደሩ ከፈቀደ በኋላ በጎን ህገወጥ ስራ መስራቱ እንዳሳዘናቸውና ሰላማዊ ሰልፉ ህገወጥ ነው ካለም ደብዳቤ መፃፍና እንዲቀር ማድረግ ሲችሉ ከላይ ፈቅደው እታች ላሉት መመሪያ አላስተላለፉም፤ ይሁን እንጂ ሰላማዊ ሰልፉ ህጋዊና ሰላማዊ ስለሆነ እንቀጥልበታለን፣ ህገወጥ ናችሁ የሚል አካል ካለ ሰልፉን ለማድረግ የሚያስችል ህጋዊ ሰነድ የያዙ መሆናቸውን በመግለፅ አሁንም ቅስቀሳ ላይ እንደሆኑ ማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ የከተማው ፅጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ በላይ በበኩላቸው እኛ ሰልፉን ለማደናቀፍ ያሰርነው የለም፣ እኔ አሁን ከከተማ ውጭ ስለሆንኩ አረጋግጬ እነግርሃለው፤ የእውነት የታሰረ ካለም አንተም አረጋግጥ ቢሉኝም ዳግም ላገኛቸው አልቻልኩም፡፡

የከተማው ከንቲባ አቶ አለባቸው የሱፍን በጉዳዩ ዙሪያ ትናንት ሐምሌ 3 ቀን 2005ዓ.ም. ሳናግራቸው ምንም የሚፈጠር ችግር እንደሌለና ከፓርቲው አመራሮች ጋርም ለመመካከርና ለመወያየት ቀጠሮ ይዘናል፣ ፓርቲው ህጋዊ በሆነ መንገድ አሳውቆናል፣ መከልከልም ሆነ ማገድ አንችልም፤ ነገር ግን በፀጥታው ጉዳይ ለመነጋገር ነው ያሰብነው ሲሉ ነግረውኝ ነበር፡፡ ዛሬ በቀበሌ ሰራተኞችና በየቀጠናው ባሉ ፖሊሶች እየተደረገ ስላለው ምላሽ እንዲሰጡኝ ወደ ቢሮአቸው ባቀናም ከቢሮ ውጭ ስብሰባ ላይ መሆናቸው ስለተነገረኝ ከሰዓት በኋላ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ብደውልም ሊያነሱልኝ አልቻሉም፤ስለዚህ ምላሻቸውን ማካተት አልቻልኩም፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች መካከል የመጨረሻው ዙር ከአዲስ አበባ አቶ ግርማ ሰይፉ(ብቸኛው የተፎከካሪ ፓርቲ የፓርላማ አባል)፣ አቶ በላይ ፈቃዱን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ለእሁዱ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. ሰላማዊ ሰልፉ ዛሬ ደሴ ከተማ ገብተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከሼህ ኑሩ ይማም መገደል ጋር በተያያዘ በርካት ወጣቶች አሁንም እየታሰሩ መሆኑን 4ኛ ፖሊስ ጣቢያ የተመለከትኩ ሲሆን ይህ በሌሎችም ጣቢያዎች እየተከናወነ መሆኑም በከተማው ያነጋገርኳቸው ነዋሪዎች አረጋግጠውልኛል፡፡

ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲዘጋ ተማሪዎቹም ከግቢ እንዲወጡ ፓትርያርኩ ደብዳቤ መጻፋቸው ተሰማ

ደብዳቤውን ተከትሎ አባ ሉቃስና አባ ጢሞቴዎስ ዱላ ቀረሽ መዘላለፍ ውስጥ ገቡ

ሰሞኑን ተጠናክሮ የቀጠለውን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን ጥያቄ አልቀበል ያሉትና ሲኖዶሱ የወሰነውን ውሳኔ ለማስፈጸም ዝግጁ ያልሆኑት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን አባ ጢሞቴዎስ ወዳጃቸውን ፓትርያርክ ማትያስን ደብዳቤ በማጻፍ ኮሌጁ እንዲዘጋና ተማሪዎችም ግቢውን እንዲለቁ፣ ምረቃም እንደማይኖር እንዲደረግ ትእዛዝ ማስወጣታቸው ተሰማ፡፡ ደብዳቤው ተግባራዊ መሆኑ ግን አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ ፓትርያርኩ የጻፉት ደብዳቤ ዛሬ የተሰበሰበውን ቋሚ ሲኖዶስ ያጨቃጨቀ ሲሆን በዋናነት ኮሌጅን መዝጋት የሚያበቃ ችግር አልተፈጠረም፡፡ የተፈጠረ ቢሆንም እንኳ በሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንጂ በእርስዎ ደብዳቤ ኮሌጁ ሊዘጋ አይችልም የሚል ጠንካራ ተቃውሞ ከጳጳሳት በኩል ቀርቧል፡፡ በተለይም አባ ሉቃስ ደብዳቤውን ከተቃወኑት መካከል ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎም አባ ጢሞቴዎስ በአባ ሉቃስ ላይ የስድብ ውርጅብኝ ያወረዱባቸው ሲሆን “አንተ ሰዶማዊ አዋሳ ላይ ስታሳድም የኖርህ ባለፈውም ቀሚስ አሰፍተህ ፓትርያርክ እሆናለሁ ብለህ ስታሳድም አልነበርህም?” ማለታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በአጸፋውም አባ ሉቃስ “አንተ መሃይም እውር መቼም ከትምህርቱ የለህበት ለዚያ ነው ኮሌጁ ይዘጋ የምትለው” ማለታቸውን ምንጮቻችን አክለዋል፡፡ ይህን ዱላ ቀረሽ መዘላለፍ ተከትሎ ፓትርያርኩ ቆመው “ኧረ ስለ ማርያም ብላችሁ ተዉ” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

“ባለቤቷን የተማመነች በግ…” እንደሚባለው ከፓትርያርክ ፓትያስ ጋር ባላቸው የጠበቀ ወዳጅነት ተመክተው ከሚገኙበት የጤንነት ሁኔታ የማየት ችግር አንጻር ጡረታ መውጣት ያለባቸው አባ ጢሞቴዎስ ኮሌጁን በርስትነት ይዘው ለዛሬዪቱም ቤተክርስቲያን ተስፋ የሆኑትንና የነገዪቱም ቤተክርስቲያን ወራሾች የሆኑትን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን በማባረር ኮሌጁን የሚያዘጋ ደብዳቤ ማጻፍ ለቤተክርስቲያኒቱ ትልቅ ውድቀት እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ ደብዳቤውን የጻፉት ፓትርያርክም በምን መነሻነት ይህን እንዳደረጉ ግራ አጋቢ ሆኗል፡፡ ምንም ወዳጅ ቢሆኑ ወዳጅነት የሚገለጸው በሌላ በግል ጉዳይ እንጂ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቁር ጠባሳ የሚጥልና ራሳቸውንም ትዝብት ውስጥ የሚከት ይህን መሰል ደብዳቤ በመጻፍ መሆን አልነበረበትም የሚሉ አሉ፡፡

 እንደአንዳንድ ተንታኞች የቅድሰት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በፓትርያርኩ ጥርስ ውስጥ የገቡት ፓትርያርኩ ወዳጄ አባ ጢሞቴዎስ ለምን ተነኩ በሚል ብቻ ሳይሆን ለፕትርክና እጩነት እኔን ትታችሁ አባ ሳሙኤልን ደግፋችኋል በሚል ሳይሆን እንዳልቀረ ይናገራሉ፡፡ ኮሌጁንና ተማሪዎቹን የመናፍቃን መፈልፈያ ሆኗል ሲሉ ይተቹ የነበሩት የማቅ ብሎጎችም አሁን ተማሪዎቹን ደግፈውና ቀድሞ ይደግፏቸው የነበሩትን አባ ጢሞቴዎስን እየተቹ መጻፋቸው ደግሞ ምን አይተው ይሆን እያሰኘ ነው፡፡

 ለተማሪዎቹ የአካዳሚክ ነጻነት ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ለጥያቄዎቹ ሌላ መልክ በመስጠት የመማር ማስተማሩን ሂደት ሲያስተጓጉሉ የቆዩት አባ ጢሞቴዎስና አስተዳደራቸው ኮሌጁን በመዝጋትና ተማሪዎቹን በማባረር መፍትሄ የሚያመጡ መስሏቸው ከሆነ እጅግ ተሳስተዋል የሚሉት ምንጮች ችግሩን ከስር አጣርቶ ተገቢው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በወዳጅነት ምክንያት በጭፍን ደብዳቤ ጽፎ ኮሌጅን ያህል ነገር መዝጋት ከበድ ያለ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል ይላሉ፡፡ የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ተማሪዎች አሉብን የሚሏቸውን ችግሮች ማዳመጥና ተገቢውን መፍትሄ መስጠት ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡

 የአንድን ጳጳስ አንባገነናዊ አስተዳደር እድሜ ለማራዘም በሚል በግብታዊነት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ግን የኮሌጁን ተማሪዎች ልብ በእጅጉ የሚያሻክርና ያስተማረቻቸውን ቤተክርስቲያን እንዲጠሉና ከዚህ ቀደም ብዙዎቹ ደቀመዛሙርት እንዳደረጉት ወደሌሎች መንግስታዊና የግል ተቋማት እንዲፈልሱ ያደርጋል፡፡ ቤተክርስቲያንንም ለፍቶ መና ያስቀራታል፡፡ ስለዚህ ለደቀመዛሙርቱ ከኮሌጅ ጀምሮ በአገልግሎት ላይ እስኪሰማሩ ድረስ ተገቢውን ጥበቃና የኑሮና የአገልግሎት ዋስትና መስጠት ይገባል፡፡ ፓትርያርኩ በቅርቡ በተናገሩት መሰረት ቤተክርስቲያን ትልቁን በጀት መበጀት ያለባት ለስብከተ ወንጌል ከሆነ በዋናነት የኮሌጅ ምሩቃንን ደመወዝ ከጊዜው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ማሳደግና ወደሌላ እንዳይሄዱ በሚያደርግ መንገድ ማደላደል ያስፈልጋል፡፡

aba selama

የ ‘ሕዳሴው ግድብ’ ፕሮጀክት በአምስት አመቱ የ’እድገትና ትራንስፎርሜሽን’ እቅድ ውስጥም አልነበረም።

የ’ሕዳሴው’ ግድብ፤ የቱኒዥያውን ቤን አሊ፣ የግብጹን ሆስኒ ሙባረክ፣ እንዲሁም የሊቢያውን ጋዳፊ የጠራረገው የሰሜን አፍሪካው ህዝባዊ ማእበል የወለደው ሃሳብ ነው። ለችግር ጊዜ ተቀምጦ የነበረ ጆከር ነው የሳቡት። ይህ ደግሞ የወጣቱን አንደበት ከያዘው የኮብል ስቶን ፕሮጀከት ጋር በመታገዝ እነ መለስን ከማዕበሉ ጠብቋቸዋል።

የ ‘ሕዳሴው ግድብ’ ፕሮጀክት በአምስት አመቱ የ’እድገትና ትራንስፎርሜሽን’ እቅድ ውስጥም አልነበረም። እንደ እንጉዳይ ተክል ከመቅጽበት ብቅ ያለ ነገርም አይደለም። ለዘላቂ ሳይሆን ይልቁንም ላጭር ጊዜ እንደሚወሰድ የእድሜ ማራዘሚያ መድሃኒት አይነት ነው። አቶ መለስዜናዊ የግድቡን መሰረት ሲጥሉ 6ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨቱ ጉዳይ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችልም ጠንቅቀው ያውቁታል።

ለዚህም አንደኛው ምክንያት በ1993 (እ.ኤ.አ.) አቶ መለስ ዜናዊ ከግብጹ ሆስኒ ሙባረክ ጋር ያደረጉት ስምምነት ነው። (የሁለቱን መሪዎች ፊርማ የያዘውን ይህንን ሚስጥራዊ ስምምነት በወቅቱ ለህትመት በማብቃቴ ለማእከላዊ እስር ተዳርጌ ነበር።) በዚህ ሁለትዮሽ ውል በአንቀጽ አምስት ላይ ‘አንዱ ሃገር ሌላውን ሃገር በሚጎዳ መልኩ ውሃውን መጠቀም አይችልም።’ በማለት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን የተፈጥሮ መብት የሚገፍ ሃረግ ተቀምጧል። ይህ ዲፕሎማሲዊ አንቀጽ በህግ ቋንቋ ሲገለጽ ‘ኢትዮጵያ አነዲት ማንኪያ ውሃ ከአባይ ላይ ብትቀዳ፡ የግብጽን ተፋሰስ ሰለሚቀንስ ከዚህ ድርጊት መቆጠብ አለባት።’ እንደማለት ነው። ከኛ አልፎ ግብፅ ምድር ላይ የሚንፏለለውን ውሃ ካይሮ ተጠቀመች አልተጠቀመች እኛ ምን አገባን?
በአለም አቀፍ ህግ፣ ሁለት ሃገሮች ተስማመተው የሚያጸድቁት ሰነድ ደግሞ ሁለቱ ተስማምተው እስካላፈረሱት ድረስ ሀጋዊ ሰነድ ሆኖ ይቆያል።

አቶ በረከት ስምዖን አልጃዚራ ላይ ባለፈው ቀርበው፤ በቅኝ ግዛት ወቅት የነበረውን ሰነድ ሲያነሱ፤ የራሳቸው ስርዓት በ1993 ያፀደቀውን ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ያላትን የተፈጥሮ እና ሀጋዊ መብት አሳልፎ የሰጠውን ውል እንደዋዛ አልፈውታል። ይህ ሰነድ በቅኝ ግዛት ዘመን ከነበሩ ስምምነቶች ሁሉ የከፋና ለክርክር እንኳን የማያመች ነው።

በአባይ ወንዝ 84 በመቶ ድርሻ ያላት ኢትዮጵያን ያላሳተፉ እነዚያን የቅኝ ግዛት ውሎች ሁሉ ውድቅ ለማድረግ የህግም ሆነ የሞራል የበላይነት አለን ብዬ አምናለሁ። ግና የ1993ቱ ምስጢራዊ ሰነድ እንዴት ነው ሊፈርስ የሚችለው? ይህ ውል ሳይፈርስ እንዴትስ ነው አባይ ሊገደብ የሚችለው? ለዚህ ጥያቄ እነበረከት በእርግጠኝነት መልስ ሊስጡን አይችሉም።

በሁለተኛ ደረጃ አባይን ከምር መገደብ ካስፈለገ፤ አባይን መገደቢያ ገንዘብ አይጠፋም። የህወሃቱ ኢፈረት ብቻውን አንድ አይደለም፤ አራት አባይን መገደብ የሚያስችል ገንዘብ አለው። ገዢው ፓርቲ እርግጥ ለኢትዮጵያ እድገት እና ትራንስፎርሜሽን ስኬት ካሰበ በፓርቲው ስም ያከማቸውን ገንዘብ አውጥቶ ለግድቡ ተግባር ማዋል ይችላል። የኢፈርት ህለቀ መሳፍርት ገንዘብ ቢያጓጓው እንኳ በአክሲዎን ሽያጭ ገንዝብ መሰብሰብ ይችል ነበር። ለግድቡ ያስፈልጋል የሚሉን 80 ቢሊየን ብር ነው። እስካሁን ከህዝብ በውዴታም ሆነ በግዴታ ተገኘ የተባለው ደግሞ 7 ቢሊየን ብር። 73 ቢሊየኑን ታዲያ ማን ሊሞላው ይሆን? ወይንስ እንዳሁኑ አይነት ያልተጠበቁ ችግሮች ሲገጥሙ ስራውን ለማቆም እንደምክንያት ሊቀርብ?

የ’ሕዳሴው ግድብ’ በዚህ ሂደት ተግባራዊ ይሆናል ወይ? የሚለውን ጥያቄ ምላሽ በቅርብ የምናየው ይሆናል። ለገዢው ፓርቲ ግዜ መግዣነት ስለማገልገሉ ግን ቅጥ ያጣው የፕሮፓጋንዳ ስራ ብቻ ምስክር ነው። ጫወታው ሳይገባቸው በሃገር ፍቅር ስሜት ብቻ የተሸውዱ እንዳሉ ሁሉ ሕዝቡን ባልተጨበጠ ነገር የሚያሞኙት ልማታዊ ጋዜጠኞች እና ልማታዊ አርቲስቶች ነገ ትዝብት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

በአንድ ጽሁፌ ለመዳሰስ እንደሞከርኩት በኡጋንዳ– ጂንጃ የነጭ አባይ ምንጭ የሆነው የቡጃጋሊ ግድብ ስራ ተጠናቋል። ኡጋንዳ የነጭ አባይ ምንጭ ነች። ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ የሃገሪቱን የሃይል አቅርቦት ችግር ለማቃለል የሚያስችል የነጭ አባይ ፕሮጀክት ዘርግተው ተግባራዊም አድርገዋል። ለዚያውም በአለም ባንክ እና በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ እርዳታ! ነጭ አባይ የሃገሪቱን የሃይል ምንጭ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይገመታል።

ይህ ግድብ ሲታቀድም ሆነ ሲሰራ ታዲያ በጩኸት እና በመፈክር አልነበረም። የሃገሪቱ አርቲስቶች አልዘፈኑለትም። ሕዝቡ ስለፕሮጀክቱ እንዲጮህለትም ሆነ እንዲጮህበት አልተደረገም። እነደ”ህዳሴ”ው መዋጮ ሁሉ የዜጎች ኪስ አልተበረበረም፤ ከወር ደመወዙ የተቆረጠ ነገር የለም። ቡጋጃሊ ሲገደብ ቦንድ አልተሸጠም፤ ወታደራዊ ማርሽም አልተሰማም። ሙሴቬኒ አንባገነን ቢሆኑም ለሃገራቸው እድገት ብልሃት በተሞላበት መንገድ ሄደዋል። ‘Think global, act local’ ነው ጫወታቸው። ‘ሞያ በልብ ነው’ ብለን ልንተረጉመው እንችላለን።

አባይን በፕሮፓጋንዳና በጩኸት ለመገደብ የተነሱት የኢትዮጵያ ገዢዎች ታዲያ ይህንን እያዩ እንኳን አልተማሩም። አባይ ሲቀለበስ በላይቭ ቲቪ ማሳየት ከፕሮፓጋንዳነቱ ባሻገር ምንድነው ጥቅሙ?ድርጊቱ ህልውናው በአባይ ወንዝ ላይ የሆነ ሕዝብን ለጦርነት መጋበዝ ይመስላል። ውግዘቱና ጫናው ሲበዛ ጉዳዩን ለማቆም ምክንያት ለመፍጠርም ያመቻል።

አለም አቀፉ ህብረተሰብ በ’ሕዳሴው ግድብ’ ጉዳይ ላይ ዝምታን ነው የመረጠው። ለዚህም ምክንያት አለው። ኢትዮጵያ ጨለማ ውስጥ ሆና ሌሎች ሃብትዋን ያላግባብ ሲጠቀሙ፤ ድልድሉ ትክክል እነዳልሆነ አለም ሳይረዳው ቀርቶ አይደለም። የመለስና ሙባረክ ፊርማ ሳይቀደድ የተጀመረው የአንድዮሽ ውሳኔም የት ተጀምሮ የት ላይ እንደሚያልቅ ያውቁታል። ለዚህም ይመስላል ለግድቡ የገንዘብም ሆነ የሞራል ድጋፋቸውን ሊነፍጉ የቻሉት። የግድቡ ጅማሮ አንደኛ አመት ሲከበር የመንግስት ባለስልጣናት እና የውጭ ዲፕሎማቶች የእግር ኳስ ግጥሚያ እንደሚያደርጉ ፕሮግራም ወጥቶ ነበር። ዲፕሎማቶቹ ግን በስፍራው ሳይገኙ ቀሩ። ለ’ሕዳሴው’ ግድብ እውቅና በመስጠት የፖለቲካ ስህተት ላለመስራት የመከሩ ይመስላል።

ክንፉ አሰፋ
ፕራግ፣ ቼክ ሪፐብሊክ

በቦንድ ሽያጭ ያልተሳካው የገንዘብ ዘረፋ በኮንደሚኒየም ሰበብ መሳካት የለበትም!!!

ወያኔ በጠመንጃ ኃይል ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ በከተሞች አካባቢ ምንም አይነት ሕዝባዊ ተቀባይነት ኖሮት አያውቅም። ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት ከተሞች በጠላትነት በተፈረጀው አማራና የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች የተሞሉ ስለሆነ ነው ይላል። ዋና ከተማችን አዲስ አበባ በዚህ ውንጀላ ዋጋ ከከፈሉት ከተሞች ግንባር ቀደሟ ናት። በተለይ በመጀመሪያው የወያኔ 10 (አሥር) የሥልጣን አመታት የከተማዋን የነዋሪዎች አሰፋፈር ስብጥር ሆን ብሎ ለመቀየር ከመሞከር ጀምሮ የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ተቋሞችን አቅም ለማዳከም በርካታ አሳዛኝ እርምጃዎች ተወስደዋል።

ታሪክን ወደኋላ መለስ ብለን እንቃኝ። የፋሺስት ጣልያን ጦር በእንግሊዝ ጦር ትብብር በኢትዮጵያ አርበኞች ከተደመሰሰ በኋላ በአሸናፊነው ወደከተሞች የገባው የእንግሊዝ ጦር ያገኘውን ንብረት በወቅቱ የቅኝ ግዛቶቹ ወደ ነበሩት ኬንያና ሱማሌ አሽሽቷል። ከብዙ ዓስርተ ዓመታት በኋላ ወያኔ ይህንኑ እኩይ ተግባር ደገመው። ወያኔ በያዛቸው ከተሞች ውስጥ ያገኘኛቸውን ውድ ዋጋና ትላልቅ ጥቅሞች የሚሰጡ በርካታ ንብረቶችን ከተለያዩ መንግሥታዊና ወታደራዊ ተቋሞች፤ ዩኒቨርስቲዎች፤ ሆስፒታሎች፤ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ አገልግሎት መስጫዎች ዘርፎ እስከዛሬ ትክክለኛ አደራሻው ለሕዝብ ይፋ ወደ አልተደረገ የሰሜን አካባቢ አይናችን እያየ በረጃጅም የጭነት መኪናዎች አጓጉዞአል። በቀድሞ መንግሥት ዘመን ምንም ዕጥረት እንዳልነበረው የሚታወቀውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የ24 ሰዓት መብራት አገልግሎትን እንኳ ሳይቀር በማስተጓጎል የከተማውን ሕዝብ ተበቅሎአል።

ወያኔ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ጥላቻ በጥቂቱም ቢሆን ረገብ ያደረገ የሚያስመስል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የጀመረው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው። አንደኛው ምክንያት በቃኝ የማያውቁት የቀድሞ ተጋዳላዮች የአገሪቱን አንጡራ ሃብት እንዲበዘብዙ በተመቻቸላቸው እድል ዘርፈው የያዙትን ገንዘብ ከውልደታቸው ጀምሮ ከሚታወቁበት አካባቢ ሕዝብ እይታ አርቀው “ለደም ካሳ” በዋና ከተማችን እምብርት በነፃ በታደላቸው የከተማ ቦታዎች ላይ ህንጻዎችን በመገንባት ንብረት እንዲይዙ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በርካታ የአለም አቀፍ ድርጅቶችና ዲፕሎማቶች መቀመጫ በሆነቺው አዲስ አበባ ምርጫ 97ን ተከትሎ ገጥሞት የነበረው ሽንፈት ባስከተለው መዘዝ የተበላሸ ገጽታውን በህንጻና መንገዶች ግንባታ ስም ለማሳመር መጣር ናቸው።

የአዲስ አበባ ኮንደሚኒዬም ቤቶቾ ግንባታ ከምርጫ 97 ቦኋላ በመኖሪያ ቤቶች እጥረት የሚሰቃየውን ሕዝብ ልብ ለማማለልና የፖለቲካ ድጋፍ ለመግዛት ያስችላል ተብሎ የታሰበ ብቻ ሳይሆን የሚከተሉት ድብቅ ዓላማዎችም አሉት።

1. በዘረፋ የከበሩ የቀድሞ ተጋዳላዮችና የጥቅም ተካፋዮቻቸው አይናቸው ያረፈባቸውን ቁልፍ የመኖሪያና የንግድ ቦታዎች ሁሉ ለዘመናት በባለይዞታነት ይዘው የኖሩትን በልማትና በእንቨስትመንት ሥም በማፈናቀል ወደ ግላቸው ላማዞር ያስችላቸዋል፤
2. በተለያዩ ሥም የተቋቋሙ የህንጻ ሥራ ተቋራጭ ድርጅቶቻቸው በግንባታው ሥራ በመሳተፍ መጠነ ሰፊ የሆነ ትርፍ ለማግበስበስ ያመቻቸዋል፤
3. የሥርዓቱን ደጋፊዎችና አቀንቃኞች ከሌላ ቦታ አምጥቶ በማስፈር በጠላትነት የተፈረጀውን የኅብረተሰብ ክፍል ተጽዕኖ ለማምከን ይረዳል፤
4. በሀብት ዘረፋው ለመሳተፍ እድል የሌላቸው የበታች ካድሬዎችና ታማኝ አገልጋዮችን ተጠቃሚ በማድረግ በአለቆቻቸው ዘረፋ ተማረው ልባቸው እንዳይሸፍት ይከላከላል ፤
5. ከተወለዱበትና ካደጉበት የግልና የቀበሌ ቤቶች ያለውደታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የኮኖዶሚኒየሙን ሂሳብ መክፈል እስከቻሉ ድረስ “ከቤታችን ተፈናቅለን ሜዳ ላይ ተጣልን” የሚል እሮሮ በማሰማት መንግስት ላይ አመጽ እንዳያስነሱ ስጋት ለመቀነስ ይረዳል፤
6. ከሰሞኑ 40 ከመቶ ተብሎ በወጣው ፖሊሲ እንደታዘብነው ደግሞ ዜጎችን በማጓጓት ተቸግረው ያጠራቀሙትን ገንዘብ ዝግ የባንክ ሂሳብ ውስጥ እንዲከቱ በማድረግ የገንዘብ እጥረት አንገቱ ድረስ የዘለቀውን አገዛዝ ለመታደግ ያስችላል (በ16 የሥራ ቀናት ብቻ ከተመዘገበው 750, 000 የኮንዶሚንዬም ቤት አመልካች 750 000 000 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን) ብር መሰብሰቡን ልብ ይሏል)

ከዚህም በተጨማሪ የኮንደሚኒዬም ቤቶች ግንባታ በቂ ጥናትና ዝግጅት ያልተደረገበት የይድረስ ይድረስ ሥራ መሆኑን የቤቶቹ ርክክብ በተፈጸመ ማግሥት ስለ ህንጻው መሬት ውስጥ መስጠምና መጣመም መጀመር እየወጥ ያሉ ዜገባዎች ዋቤ ምስክር ናቸው።

የወያኔ መሪዎችና ታማኝ አገልጋዮቻቸው ከኮንደሚኒዬም ግንባታ በተጨማሪ ከምርጫ 97 ወዲህ ከፍተኛ ገንዘብ እያግበሰበሱ ያሉት የከተማ ቦታዎችን በውድ ዋጋ የልጅ ልጆቻቸው እንኳ ሊደርሱበት ለማይችል የግዜ ገደብ በሊዝ በመቸብቸብ ነው። በዚህ የመሬት ቅሪሚያ አንዳንድ ስግብግቦች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” እንዲሉ “ወያኔዎች መሬታችንን እየተቀራመቱ ስለሆነ ተሻምተን ማስቆም አለብን” በሚል ብልጣ ብልጥነት ከሚኖሩበት የስደት አገር እየተጓዙ የወያኔን ገቢያ በማድራት ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በትዝብት ተመልክቶአል። አገርን ዘርፎ ለዘራፊ እየሰጠ ያለ መንግሥት ሴራ ተባባሪ መሆን በሞራልም ሆነ በህሊና ዳኝነት የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑ ሳያንስ እነዚህ በስግብግብነት የተጠመዱ ወገኖች ለንብረታቸው ደህንነት ሲባል ወያኔ ዓይናቸው እያየ ጆሮአቸው እየሰማ በሌሎች ወገኖቻቸው ላይ የሚፈጽማቸውን ሰቆቃዎች እንኳ ለመቃወም ድፍረት በማጣት ሌላ ትዝብት ውስጥ ሲወድቁ ተስተውለዋል:: ለመሆኑ እነዚህ ወገኖች ለፍተው ባገኙት ገንዘብ የገዙት ባርነትን ነው ወይስ የንብረት ባለቤትነትን ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ይኖራቸዋል?

የዜጎች መብት በተከበረበት አገር ከዜግነት መብቶች አንዱ የግል ሀብት ባለቤት ለመሆን ገደብ የሌለው ነፃነትና እድል መኖሩ ነው:: ወያኔ በሚያስተዳድራት ኢትዮጵያችን ግን የንብረት ባለቤት ለመሆን የሥርዓቱ ባለሟል መሆን አለያም ከፖለቲካ ባላንጣነት መራቅ ዋና መስፈርት ናቸው። በዚህ መስፈርት ከወያኔ ጋር ተሻምተው ወይም ተሻርከው የንብረት ባለቤት ለመሆን እየተሽቀዳደሙ ያሉ ወገኖች ሊያውቁት የሚገባው ሃቅ ቢኖር አድሎአዊነት በሰፈነበት መንገድ የተገኘ ማንኛውም አይነት ሀብት ወይም ንብረት ወደፊት በወያኔ ከርሰ መቃብር ላይ በሚመሰረተው ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ህገዊ ጥበቃ የሚኖረው አለመሆኑን ነው። ብሄራው የአገር ጥቅም ላይ ክህደት ከፈጸመ ፤ ዜጎችን በማፈን ሰቆቃ ካደረሰ ፤ የአገሪቷን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው በማፈናቀል መሬታቸውን ቀምቶ ለሌሎች አሳልፎ ከሰጠ ፤ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት ዘርፎ ለዘራፍ ከሰጠ ወንጀለኛ መንግሥት ጉያ ውስጥ ተወሽቆ እስከ ወዲያኛው የህግ ጥበቃ ሊደረግለት የሚችል ንብረት ባለቤት መሆን ማሰብ እጅግ ይቸግራል። ዜጎች በራሳቸው ወዝ ለፍተው ያገኙትን ንብረት ሳይቀር በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት ብቻ በሽብርተኝነት እየፈርጀ የሚነጥቅ ሥርዓት ዕድሜ እንደምንጠብቀው ረዥም ሊሆን እንደማይችል ማሰብ ብልህነት ነው።

ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የወያኔ አገዛዝ በውጭው ዓለም በስደት ከሚኖረው ወገናችን በአባይ ግድብ የቦንድ ሺያጭ ሥም ለመሰብሰብ ሞክሮ ያልተሳካለትን ገንዘብ በመሬት ሺያጭ እና በኮንደሚኒዬም ቤት ግዥ ሥም እንዲያገኝ ሊፈቀድለት አይገባም ብሎ ያምናል:: ስለዚህም እያንዳንዱ ነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ከዚህ ከኮንደሚኒዬም ቤቶች በስተጀርባ ያለውን ድብቅ አጀንዳ በማጋለጥ ጥረቱን በማምከን የሕዝባዊ እምብተኝነት ትግል አካል እንዲሆን ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያስተላልፋል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

onsdag 10. juli 2013

መንግስት ጉርምስናው ብሶበታል፡፡ (አሉ)

መንግስት ጉርምስናው ብሶበታል፡፡ (አሉ)

አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፈትህ ፓርቲ  አንድነት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል ሃይለቃል አሸባሪው “የጸረ ሽብር አዋጅ” እንዲሰረዝ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ የአንድነቱ ጋዜጠኛ ወዳጃችን ነቢዩ በፌስ ቡክ ግድግዳው ላይ ሰበር ዜና ብሎ እንዲህ ነግሮናል… ነብዩ በመንግስታችን ብስጭት ማለቱ ያስታውቅበታል፤ እስቲ ቀጥል ነቤ፤

ሰበር ዜና
—————
መንግስታዊ ሽፍታነት በኢትዮጵያ
—————–
ኢህአዴግ መንግስታዊ ሽፍታነቱን ገፍቶበታል፡፡ ዛሬ ጠዋት በደሴ ከተማ የቅስቀሳ ተልዕኳቸውን በመወጣት ላይ ከአዲስ አበባ የተጓዙትን የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃንና የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛ የሆነውን አቶ ወንደሰን ክንፈን በማገት “እንደራረር” በማለት ላይ ይገኛል፡፡
አግተው እንደራደር የሚሉት ሽፍቶች ናቸው፤ መንግስት አግቶ እንደራደር ሲል ሽፍታነቱን በአደባባይ መረጋገጡ ነው፡፡

አንድነት የፓርቲው ጽ/ቤት እስኪዘጋና አባላቱ እስርቤቶችን እስኪሞሉ ህዝባዊ ንቅናቀው ይቀጥላል፡፡ ፓርቲው ያነሳው ህዝባዊ ጥያቄ በመሆኑ የአንድነት አመራሮችና አባላት መስዋዕት ቢሆኑም ህዝቡ ትግሉን ከዳር እንሚያደርሰው አንጠራጠርም፡፡

ነብዩን እናመሰግናለን፤ መንግስትን ጉርምስናውን በቅጡ አድርገው እንላለን!

አንድነት ፓርቲ በደሴና በጎንደር በመጪው እሁድ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳውን ቀጥሎአል

ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የኑሮ ውድነት እና የፍትህ እጦት ለመቃወም ፓርቲው በጎንደርና በደሴ የጀመረውን ቅስቀሳ ወረቀቶችን በመበተን፣ እና በመኪና ላይ በመሆን በየሰፈሩ በመዘዋወር በድምጽ ማጉያ የትግል ጥሪ እያስተላለፈ ነው።

በደሴ ከተማ በማስተባበር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃንና የፍኖት ነጻነት ጋዜጠኛ የሆነዉ አቶ ወንደወሰን ክንፈ ታግተው መለቀቃቸውን ከፓርቲው ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የደሴ ከንቲባ በመጪው እሁድ ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደረግ ቢከለክልም አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን ግን ተቃውሞውን ከማድረግ የሚከለክላቸው ነገር እንደሌለ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ዜናም በአዲስ አበባ ቄራ አካባቢ የፓርቲውን  ወረቀቶች በትነዋል የተባሉ አቶ ዳንኤል ፈይሳ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮልና አቶ አበበ ቁምላቸው ተይዘው ከታሰሩ በሁዋላ  ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ፖሊስ “አንድነት የሚባል ፓርቲ መኖሩን እስከማረጋገጥ ድረስ የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ” በማለት ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ሲሆን፣ ፍርድቤቱም የፖሊስን ጥያቄ ተቀብሎ የ10 ቀናትየጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።  እስረኞቹም ወደ ማረሚያ ቤት ተልከዋል።

በየካ ክ/ከተማ ደግሞ አቶ ብሩክ አሻግሬ እና አቶ ወንድይፍራው ተክሌ የተባሉ የፓርቲው አመራሮች ታስረው በዋስ መለቀቃቸው ታውቋል።

በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር ከ450 በላይ መድረሱ ታወቀ

ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ካለፈው አርብ ጀምሮ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ተቃውሞ ከ470 ያላናሱ ሰዎች እስከ ትናንት ድረስ ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ ተቃውሞውን አስተባብረዋል ከተባሉት መካከል በዋና ከተማዋ ሰላም በር የሚኖሩ ከ13 በላይ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ተመርጠው ወደ አርባ ምንጭ እስር ቤት መወሰዳቸው ታውቋል።
ወደ  አርባምንጭ እስር ቤት ከተላኩት መካከል አቶ አማኑኤል ጎቶሮ ፣ ደፋሩ ዶሬ ፣  እዮብ ጦና፣  ሻምበል ሻዋ፣ አልመሳ አርባ፣ አቶ ባንቲርጉ ሄባና፣ ወ/ሮ ጊፍታነህ ፈርአ፣ ባሻ ፋንታሁን ታደሰ፣ አቶ አበራ ገ/መስቀል፣ መ/ር ዶለቦ ቦንጃ ፣ መምህር መሸሻ ማላ፣ አቶ ጴጥሮስ ሀላላ እና አቶ ቲንኮ አሻንጎ ይገኙበታል።

የወረዳው ፖሊስ በዛሬው እለት 15 የሚሆኑ ወጣቶችን ከእስር ለመልቀቅ መፈለጉን ቢያስታውቅም፣ “እስረኞቹ ግን መጀመሪያውኑ ለምን አሰራችሁን አሁንስ በምን ምክንያት ትለቁናላችሁ” የሚል ጥያቄ በማቅረባቸው እስካሁን እንዳልተለቀቁ ታውቋል።
በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው በከተማዋ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ተወካይ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንደተናገሩት ፖሊስ ምግብ ከሚያቀብሉ ሴቶች እና ልጆች  በስተቀር ሌሎች ነዋሪዎች ወደ አካባቢው እንዳይጠጉ በመከልከሉ የእስረኞችን ቁጥር በትክክል ለማወቅ እንዳልተቻለ ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ከ470 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን መረጃ እንደደረሳቸው ገልጸዋል።

ኢሳት ከ86  በላይ የታሰሩ ሰዎች ስም ዝርዝር ደርሶታል።  ከእስረኞች መካከል የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው በሙያቸው ረዥም ዓመታትን ያገለገሉ  ከ22 የማያንሱት ደግሞ የኢህአዴግ አመራር አባላት የነበሩ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ነጋዴዎች፣ ተማሪዎች፣ ሥራ አጦች፣ የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ ሌክቼሬሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፤ የከተማ ነዋሪዎች ናቸው፡፡

አካባቢው ዛሬም በመከላከያ እና በልዩ ፖሊስ አባላት እየተጠበቀ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል

እሁድ ሰኔ 30፣ 2005 ዓም በደቡብ ክልል በጋሞ ጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በሰላም በር ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ ከ7 ሺ በላይ ነዋሪዎች፣ የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱትልን የሚል ጥያቄያቸውን በወረዳ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ለማቅረብ በተጓዙበት ወቅት የዞንና የወረዳ ፖሊሶች በነዋሪዎቹ ላይ ድበደባ መፈጸማቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩትን ማሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የቃሊቲ ዉሎየ እና የእስክንድር ነጋ የሰላማዊ ትልግ ጥሪ

ትናንት በማለዳ ነበር ተነስቼ ከሰሚት ወደ ሳሪስ ያቀናሁት፡፡ የሐምሌን ቀዝቃዛ የጠዋት አየር እየተመገብኩ ከጓደኞቼ ጋር ከተቀጣጠርኩበት ሐበሻ ካፌ ስደርስ ሰዓቴ ከጥዋቱ 1፡30 (7፡30 AM) ይል ነበር፡፡ ሁላችንም ከየአቅጣጫዉ በዚያች አነስተኛ ካፌ ከተሰባሰብን በኋላ ቁርስ ቢጤ እንደ ነገሩቀማምሰን የዕለቱን ዕቅዳችንን ለመፈፀም ተነሳን—በልባችን ስኬትን እየተመኘን፡፡ እናም ፍራፍሬ በየአይነቱ ሸማመትን ፤ ያስፈልጋሉ ያልናቸዉን ነገሮች ሁሉ አሟልተን ጉዞአችንን ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት (በርግጥ ማረሚያ ቤት የሚለዉ ቃል ፍፁም አይገባዉም) አደረግን ፤ ለኛ ሲሉ እራሳቸዉንአሳልፈዉ የሰጡ የጭንቅ ጊዜ ልጆች ማለትም አንዱአለም አራጌን ፣ እስክንድር ነጋን እና ርዕዮት አለሙን እንዲሁም ሌሎችን ለመጎብኘትና አይዞአችሁ ሁሌም ከጎናችሁ ነን ልንል፡፡

ይሁን እንጅ እዚያ ደርሶ እነዚያን ጀግኖቻችንን አይዟችሁ ማለት ዉጣ ዉረድ ነበረዉ፡፡ ምንም እንኳን ሁላችንም ከነርሱ ፊት ለመቆም በጣም ብንጓጓም ብዙ መሰናክሎችን ማለፍ ነበረብን፡፡

የመጀመሪያዉ ፈተና ያዉ የአዲስ አበባችን መታወቂያ ለመሆን የበቃዉ የትራንስፖርት ችግር ነበር፡፡ በጠዋት በስራ ቦታዉ በሰዓቱ ለመገኘት ከቤቱ በነቂስ የወጣዉን ህዝብ አልፎ አልፎ ብቅ የሚሉት ታክሲወችና የአንበሳ አዉቶብሶች ሊያቃልሉት ስላልቻሉ አካባቢዉ በሰዉ ተጥለቅልቋል ፤ ሁሉም ከወዲያወዲህ ይሯሯጣል ፤ ይታመሳል፡፡ በዚያ ላይ ጭቃዉ፡፡ የሆነ ሆኖ ትንሽ ከተሯሯጥን በኋላ የመንገዱን አንድ ጠርዝ በመያዝ ከአንድ ኪሎ ሜትር በላይ እንደጉንዳል መንጋ የተዘረጋዉን የሰዉ ሰልፍ ተቀላቅለን እድላችንን መጠበቅ ተያያዝን፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ለረጅም ሰዓት የታክሲ ያለህ ስንልቆይተን አይደርሱ የለምና በመጨረሻ አንዲት ታክሲ አግኝተን ወደ ጀግኖች መንደር ጉዞ ተጀመረ፡፡ ያም ሆኖ በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት በየመንገዱ እየቆምን ቃሊቲ ለመድረስ ብዙ ጊዜ ወሰደብን፡፡ ሆኖም ምንም አስቸጋሪ ይሁን ምንም ጊዜ ይፍጅ እዚያ መድረሳችን በራሱ ትልቅ ነገር ነበርና ሁላችንምበደስታ እየተሳሳቅን ወደ ማረሚያ ቤቱ አቀናን፡፡

አንዱአለም አራጌ ከሚገኝበት የዞን 2 በራፍ ላይ ስንደርስ ሁለት ወጣት የፖሊስ አባላት ተቀበሉን፡፡ ሁለቱም በእጃቸዉ የያዙትን ደብተር እየገለጡ ማን ናችሁ ፣ ወደየት ናችሁ…? ሲሉ አንድ ባንድ እየጠየቁ የሚፈልጉትን መረጃ ከመዘገቡ በኋላ መታወቂያችንን አይተዉ ወደ ዉስጥ እንድንገባ ፈቀዱልን፡፡ትንሽ አለፍ ከማለታችንም በአንዲት ትንሽ ቤት ዉስጥ ለሚገኙ የፖሊስ አባላት ሞባይል ፣ ቁልፎቻችንን ፣ ዋሌታችንን ፣ ባጠቃላይ ኪሳችን ዉስጥ የተገኘን ነገር ሁሉ እስክብሪቶና ወረቀት ሳይቀር አስረክበን ወደ ዉስጥ አለፍን፡፡ አዚህ ላይ እኔን በጣም የገረመኝ የስክብሪቶዉና የወረቀቱ ጉዳይ ነበር፡፡ አሁንእስቲ ምን ይሉታል ወረቀት መቀማት ፤ የጦር መሳሪያ መሆኑ ነዉ ፣ እንደሚመስለኝ ሰዉ እዚያ የሚፈፅሙትን ግፍ በተመለከተ መረጃ ይዞ እንዳይወጣ ለመከላከል ነዉ፡፡