የ’ሕዳሴው’ ግድብ፤ የቱኒዥያውን ቤን አሊ፣ የግብጹን ሆስኒ ሙባረክ፣ እንዲሁም የሊቢያውን ጋዳፊ የጠራረገው የሰሜን አፍሪካው ህዝባዊ ማእበል የወለደው ሃሳብ ነው። ለችግር ጊዜ ተቀምጦ የነበረ ጆከር ነው የሳቡት። ይህ ደግሞ የወጣቱን አንደበት ከያዘው የኮብል ስቶን ፕሮጀከት ጋር በመታገዝ እነ መለስን ከማዕበሉ ጠብቋቸዋል።
የ ‘ሕዳሴው ግድብ’ ፕሮጀክት በአምስት አመቱ የ’እድገትና ትራንስፎርሜሽን’ እቅድ ውስጥም አልነበረም። እንደ እንጉዳይ ተክል ከመቅጽበት ብቅ ያለ ነገርም አይደለም። ለዘላቂ ሳይሆን ይልቁንም ላጭር ጊዜ እንደሚወሰድ የእድሜ ማራዘሚያ መድሃኒት አይነት ነው። አቶ መለስዜናዊ የግድቡን መሰረት ሲጥሉ 6ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨቱ ጉዳይ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችልም ጠንቅቀው ያውቁታል።
ለዚህም አንደኛው ምክንያት በ1993 (እ.ኤ.አ.) አቶ መለስ ዜናዊ ከግብጹ ሆስኒ ሙባረክ ጋር ያደረጉት ስምምነት ነው። (የሁለቱን መሪዎች ፊርማ የያዘውን ይህንን ሚስጥራዊ ስምምነት በወቅቱ ለህትመት በማብቃቴ ለማእከላዊ እስር ተዳርጌ ነበር።) በዚህ ሁለትዮሽ ውል በአንቀጽ አምስት ላይ ‘አንዱ ሃገር ሌላውን ሃገር በሚጎዳ መልኩ ውሃውን መጠቀም አይችልም።’ በማለት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን የተፈጥሮ መብት የሚገፍ ሃረግ ተቀምጧል። ይህ ዲፕሎማሲዊ አንቀጽ በህግ ቋንቋ ሲገለጽ ‘ኢትዮጵያ አነዲት ማንኪያ ውሃ ከአባይ ላይ ብትቀዳ፡ የግብጽን ተፋሰስ ሰለሚቀንስ ከዚህ ድርጊት መቆጠብ አለባት።’ እንደማለት ነው። ከኛ አልፎ ግብፅ ምድር ላይ የሚንፏለለውን ውሃ ካይሮ ተጠቀመች አልተጠቀመች እኛ ምን አገባን?
በአለም አቀፍ ህግ፣ ሁለት ሃገሮች ተስማመተው የሚያጸድቁት ሰነድ ደግሞ ሁለቱ ተስማምተው እስካላፈረሱት ድረስ ሀጋዊ ሰነድ ሆኖ ይቆያል።
አቶ በረከት ስምዖን አልጃዚራ ላይ ባለፈው ቀርበው፤ በቅኝ ግዛት ወቅት የነበረውን ሰነድ ሲያነሱ፤ የራሳቸው ስርዓት በ1993 ያፀደቀውን ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ያላትን የተፈጥሮ እና ሀጋዊ መብት አሳልፎ የሰጠውን ውል እንደዋዛ አልፈውታል። ይህ ሰነድ በቅኝ ግዛት ዘመን ከነበሩ ስምምነቶች ሁሉ የከፋና ለክርክር እንኳን የማያመች ነው።
በአባይ ወንዝ 84 በመቶ ድርሻ ያላት ኢትዮጵያን ያላሳተፉ እነዚያን የቅኝ ግዛት ውሎች ሁሉ ውድቅ ለማድረግ የህግም ሆነ የሞራል የበላይነት አለን ብዬ አምናለሁ። ግና የ1993ቱ ምስጢራዊ ሰነድ እንዴት ነው ሊፈርስ የሚችለው? ይህ ውል ሳይፈርስ እንዴትስ ነው አባይ ሊገደብ የሚችለው? ለዚህ ጥያቄ እነበረከት በእርግጠኝነት መልስ ሊስጡን አይችሉም።
በሁለተኛ ደረጃ አባይን ከምር መገደብ ካስፈለገ፤ አባይን መገደቢያ ገንዘብ አይጠፋም። የህወሃቱ ኢፈረት ብቻውን አንድ አይደለም፤ አራት አባይን መገደብ የሚያስችል ገንዘብ አለው። ገዢው ፓርቲ እርግጥ ለኢትዮጵያ እድገት እና ትራንስፎርሜሽን ስኬት ካሰበ በፓርቲው ስም ያከማቸውን ገንዘብ አውጥቶ ለግድቡ ተግባር ማዋል ይችላል። የኢፈርት ህለቀ መሳፍርት ገንዘብ ቢያጓጓው እንኳ በአክሲዎን ሽያጭ ገንዝብ መሰብሰብ ይችል ነበር። ለግድቡ ያስፈልጋል የሚሉን 80 ቢሊየን ብር ነው። እስካሁን ከህዝብ በውዴታም ሆነ በግዴታ ተገኘ የተባለው ደግሞ 7 ቢሊየን ብር። 73 ቢሊየኑን ታዲያ ማን ሊሞላው ይሆን? ወይንስ እንዳሁኑ አይነት ያልተጠበቁ ችግሮች ሲገጥሙ ስራውን ለማቆም እንደምክንያት ሊቀርብ?
የ’ሕዳሴው ግድብ’ በዚህ ሂደት ተግባራዊ ይሆናል ወይ? የሚለውን ጥያቄ ምላሽ በቅርብ የምናየው ይሆናል። ለገዢው ፓርቲ ግዜ መግዣነት ስለማገልገሉ ግን ቅጥ ያጣው የፕሮፓጋንዳ ስራ ብቻ ምስክር ነው። ጫወታው ሳይገባቸው በሃገር ፍቅር ስሜት ብቻ የተሸውዱ እንዳሉ ሁሉ ሕዝቡን ባልተጨበጠ ነገር የሚያሞኙት ልማታዊ ጋዜጠኞች እና ልማታዊ አርቲስቶች ነገ ትዝብት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
በአንድ ጽሁፌ ለመዳሰስ እንደሞከርኩት በኡጋንዳ– ጂንጃ የነጭ አባይ ምንጭ የሆነው የቡጃጋሊ ግድብ ስራ ተጠናቋል። ኡጋንዳ የነጭ አባይ ምንጭ ነች። ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ የሃገሪቱን የሃይል አቅርቦት ችግር ለማቃለል የሚያስችል የነጭ አባይ ፕሮጀክት ዘርግተው ተግባራዊም አድርገዋል። ለዚያውም በአለም ባንክ እና በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ እርዳታ! ነጭ አባይ የሃገሪቱን የሃይል ምንጭ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይገመታል።
ይህ ግድብ ሲታቀድም ሆነ ሲሰራ ታዲያ በጩኸት እና በመፈክር አልነበረም። የሃገሪቱ አርቲስቶች አልዘፈኑለትም። ሕዝቡ ስለፕሮጀክቱ እንዲጮህለትም ሆነ እንዲጮህበት አልተደረገም። እነደ”ህዳሴ”ው መዋጮ ሁሉ የዜጎች ኪስ አልተበረበረም፤ ከወር ደመወዙ የተቆረጠ ነገር የለም። ቡጋጃሊ ሲገደብ ቦንድ አልተሸጠም፤ ወታደራዊ ማርሽም አልተሰማም። ሙሴቬኒ አንባገነን ቢሆኑም ለሃገራቸው እድገት ብልሃት በተሞላበት መንገድ ሄደዋል። ‘Think global, act local’ ነው ጫወታቸው። ‘ሞያ በልብ ነው’ ብለን ልንተረጉመው እንችላለን።
አባይን በፕሮፓጋንዳና በጩኸት ለመገደብ የተነሱት የኢትዮጵያ ገዢዎች ታዲያ ይህንን እያዩ እንኳን አልተማሩም። አባይ ሲቀለበስ በላይቭ ቲቪ ማሳየት ከፕሮፓጋንዳነቱ ባሻገር ምንድነው ጥቅሙ?ድርጊቱ ህልውናው በአባይ ወንዝ ላይ የሆነ ሕዝብን ለጦርነት መጋበዝ ይመስላል። ውግዘቱና ጫናው ሲበዛ ጉዳዩን ለማቆም ምክንያት ለመፍጠርም ያመቻል።
አለም አቀፉ ህብረተሰብ በ’ሕዳሴው ግድብ’ ጉዳይ ላይ ዝምታን ነው የመረጠው። ለዚህም ምክንያት አለው። ኢትዮጵያ ጨለማ ውስጥ ሆና ሌሎች ሃብትዋን ያላግባብ ሲጠቀሙ፤ ድልድሉ ትክክል እነዳልሆነ አለም ሳይረዳው ቀርቶ አይደለም። የመለስና ሙባረክ ፊርማ ሳይቀደድ የተጀመረው የአንድዮሽ ውሳኔም የት ተጀምሮ የት ላይ እንደሚያልቅ ያውቁታል። ለዚህም ይመስላል ለግድቡ የገንዘብም ሆነ የሞራል ድጋፋቸውን ሊነፍጉ የቻሉት። የግድቡ ጅማሮ አንደኛ አመት ሲከበር የመንግስት ባለስልጣናት እና የውጭ ዲፕሎማቶች የእግር ኳስ ግጥሚያ እንደሚያደርጉ ፕሮግራም ወጥቶ ነበር። ዲፕሎማቶቹ ግን በስፍራው ሳይገኙ ቀሩ። ለ’ሕዳሴው’ ግድብ እውቅና በመስጠት የፖለቲካ ስህተት ላለመስራት የመከሩ ይመስላል።
ክንፉ አሰፋ
ፕራግ፣ ቼክ ሪፐብሊክ

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar